Monday, April 15, 2024

በአንድ ሳምንት ውስጥ በዓለም 6.52 ሚሊዮን የኮቪድ ታማሚ ተመዘገበ

- Advertisement -spot_img

በብዛት የተነበቡ

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሥርጭት በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተስፋፋ ሲሆን፣ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥርም ከዚህ ቀደም ከነበረው ፍጥነት በተለየ እያሻቀበ ነው፡፡ በተለይ በአውሮፓና አሜሪካ የሚመረመሩ ሰዎች ቁጥርም ሆነ በቫይረሱ የሚያዙት እየጨመረ መጥቷል፡፡

በአንድ ቀን ብቻ በአማካይ ከ930 ሺሕ በላይ የኮቪድ ታማሚ እየተመዘገበ ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት ብቻ 6.51 ሚሊዮን የኮቪድ-19 ታማሚ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመዝግቧል፡፡

የጆን ሆፕኪንስ የኮሮና ቫይረስ ሪሶርስ ሴንተር እንደሚያሳየው፣ በአሜሪካ ብቻ በታኅሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም. 377,014 የኮቪድ ታማሚ ሲመዘገብ 2,337 ሰው ሞቷል፡፡ በብሪታኒያ ደግሞ 128,883 በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡ 18 ሞተዋል፡፡

በተለይ የኦሚክሮን ዝርያ በፍጥነት እየተሠራጨ መሆኑ ለታማሚዎች ቁጥር መጨመር ምክንያት ሆኗል፡፡

የኦሚክሮን ዝርያ የመግደል ዕድሉ አነስተኛ ሊሆን ይችላል የሚሉ የመነሻ ጥናቶች ቢኖሩም፣ በርካታ ሰው እየታመመ መሆኑ ከዚህ ቀደም በኮቪድ-19 የተዳሙ ሆስፒታሎች፣ የጤና ሥርዓትና ባለሙያዎችን ለባሰ ችግር ያጋጥማል ተብሏል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት እንዳለውም፣ ዴልታና አሚክሮን የኮቪድ ዝርያዎች ሰዎች ሆስፒታል እንዲገቡ አሊያም እንዲሞቱ የሚያደርጉ መንታ ሥጋት ናቸው ብሏል፡፡

በኢትዮጵያም ቁጥሩ ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ቫይረሱ ኢትዮጵያ ከገባበት መጋቢት 2012 ዓ.ም. አንስቶ እስከ ታኅሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ 410,445 በቫይረሱ የተጠቁ ሲሆን፣ 6,916 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል፡፡ በታኅሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ከተመረመሩት ብቻ 12,713 ሰዎች ውስጥ 4,700 ቫይረሱ ሲገኝባቸው በፅኑ የታመሙ ደግሞ 247 መሆናቸውን ሚኒስቴሩ በዕለታዊ መረጃው አስታውቋል፡፡

እስካሁን 9,344,003 ሰዎች ክትባቱን ወስደዋል ያለው ጤና ሚኒስቴር፣ በጥንቃቄ ላይ የሚታየው ቸልተኝነት ግን ዋጋ እያስከፈለ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ ከታኅሳስ 15 ቀን እስከ ታኅሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም. የተመዘገቡ ኬዞችን አስመልክቶ በተከታታይ ቀናት ባሰፈረው መረጃ መሠረት፣ በአምስቱ ቀናት 56,854 ሰዎች ምርመራ ያደረጉ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 19,708 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡ 28 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል፡፡

ሰሞኑን ደግሞ በርካታ ሰዎች በጉንፋን ተይዘዋል፡፡ ጉንፋኑ ከሕፃን እስከ አዋቂ እያጠቃ ሲሆን፣ ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ የሕመም ምልክቶች እንዳሉትም የጤና ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡ ምክንያቱንና ምን መደረግ እንዳለበትም ይመክራሉ፡፡

ምክንያቱ ምን ሊሆን ይችላል?

የጉንፋንዋናመንስዔዎቹበትንፋሽበሳልናበማስነጠስየሚተላለፉቫይረሶችናቸውየሚሉትበቅዱስጳውሎስሆስፒታልሚሊኒየምሕክምናኮሌጅረዳትፕሮፌሰርናየሕፃናትስፔሻሊስትሐኪም  ፋሲልመንበረ (ዶ/ር)  ኮሮናቫይረስ፣ ራይኖቫይረስ፣ኢንፍሉዌንዛአዴኖቫይረስናየመሳሰሉትጉንፋንንሊያመጡይችላሉ፣ስለዚህየሰሞኑጉንፋንኮሮናይሁንአይሁንየሚታወቀውበምርመራብቻነውሲሉአታወቀዋል፡፡

ምን እናድርግ?

የመከላከያመንገዶቹንይተግብሩ፣የአፍናአፍንጫዎንይሽፍኑ፣ የእጅናአካልንክኪይቀንሱ፣ሰውየሚሰበሰብበትቦታአይገኙ፣ስያስሉናሲያስነጥሱአፍናአፍንጫዎንበክንድዎ/በጨርቅይሸፍኑ፣መንግሥትበነፃያቀረበውንየኮሮናክትባትንይውሰዱ፡፡

ለልጆችና ሕፃናት የቤት ውስጥ ሕክምናው ምንድነው?

 • ለብ ያለ ውኃ ውስጥ ትንሽ ጨው አድርጎ አፍንጫቸው ቀዳዳ ውስጥ 2 ጠብታ ማድረግ በመቀጠል የአፍንጫ ቀዳዳዎችን በመምጠጫ ማፅዳት
 • ትኩሳትን የሚቀንስ መድኃኒት መጠቀም፣
 • ትኩስ ትኩስ ነገሮችን ማጠጣት
 • ተጨማሪ ምግቦችን በደንብ መመገብ
 • የሕፃኑን ክፍል በደንብ ማፅዳት ማናፈስ
 • ቤቱን በውኃ እንፋሎት ማጠን
 • ንፍጥናትኩሳትበጣምአስፈላጊፈሳሾችንእናንጥረነገሮችንይዘውስለሚወጡተጨማሪፈሳሽነገሮችንማግኘትይኖርባቸዋል

ለታዳጊ ሕፃናትና ለአዋቂዎችስ የቤት ውስጥ ሕክምናው ምንድነው?

 • ከላይ ከተዘረዘሩት በተጨማሪ ራስን በአንድ ክፍል ማግለል
 • ትኩስ ፈሳሽ ነገሮችን ደጋግሞ መውሰድ
 • ነጭ ሽንኩርት ማር እና ዝንጅብል መጠቀም
 • በቂዕረፍትማድረግ
 • የትኩሳትና ራስ ምታት ማስታገሻ መውሰድ

ዶ/ር ፋሲል በኮሌጁ ማኅበራዊ ትስስር ገጽ እንዳሉት፣ እነዚህ መፍትሔዎች  ምንም ለውጥ ካለመጡና ሳሉ የመባስ፣ ትኩሳቱ የመጨመር ባህሪ ካለው ወይም ትንፋሽ የማጠር ምልክት በሕፃንም ሆነ በአዋቂ ላይ ካለ በአፋጣኝ ሆስፒታል መሄድ ያስፈልጋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ትኩስ ጽሑፎች

ተዛማጅ ጽሑፎች

- Advertisement -
- Advertisement -