Wednesday, November 30, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊፍጥነት የሚጠይቀው የወደሙ ትምህርት ቤቶች ግንባታ

  ፍጥነት የሚጠይቀው የወደሙ ትምህርት ቤቶች ግንባታ

  ቀን:

  መንግሥት የትምህርት ጥራትን በተመለከተ የሚነሱ ክፍተቶቸን በመሙላትና ዘርፉን ወደ ተሻለ ደረጃ በማሳደግ ትልቅ ሚና እየተጫወተ ቢሆንም፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዘርፉ ላይ ከፍተኛ የሆነ ተፅዕኖ ፈጥሯል፡፡

  በዚህም መሠረት ትምህርት ሚኒስቴር ለተወሰነ ጊዜ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በቤታቸው ሆነው እንዲከታተሉ ውሳኔ አስተላልፎ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በአሁኑ ወቅት ደግሞ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የተፈረጀው ሕወሓት አማራና አፋር ክልሎችን ወርሮ በነበረበት ጊዜ በክልሎች የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን አውድሟል፡፡ የወደሙትንም ትምህርት ቤቶች መልሶ ለማቋቋም ትምህርት ሚኒስቴር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር እየሠራ ይገኛል፡፡

  በአማራ ክልል የወደሙ የትምህርት ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም ከ11 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

  በትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የተመራው ልዑክ በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ በአሸባሪነት በተፈረጀው ሕወሓት የወደሙና ጉዳት የደረሰባቸውን ትምህርት ቤቶች ጎብኝቷል፡፡

  የልዑካን ቡድኑም የትምህርት ቤቶቹ መሠረተ ልማቶች መውደሙን፣ የመማሪያ ፕላዝማዎች፣ ኮምፒዩተሮችና የተለያዩ የትምህርት ቁሳቁሶች መዘረፋቸውንና ውድመት ከመፈጸምም አልፎ በከባድ መሣሪያ መደብደባቸውን ትምህርት ሚኒስቴር በድረ ገጹ ላይ አስፍሮታል፡፡

  የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ (ፕሮፌሰር) ጉዳት የደረሰባቸውን የትምህርት ተቋማት ከጎበኙ በኋላ፣ ‹‹በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የተፈረጀው ሕወሓት ትምህርት ቤቶችን ከመዝረፍ ባለፈ ድጋሚ አገልግሎት እንዳይሰጡ በማሰብ ማውደሙ የጨካኝነትና የክፋተኝት ጥጉን ማሳያ ነው፤›› ብለዋል፡፡

  የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ደረጃቸውን ባሟላ መልኩ እንደገና መልሶ ለማቋቋም የፌዴራልና የክልል መንግሥት ከመላው ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባበር ትምህርት ቤቶቹን እንደሚገነቡ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

  የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ማተብ ታፈረ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ የሕወሓት ኃይል በአማራ ክልል ከአራት ሺሕ በላይ ትምህርት ቤቶች ላይ ሙሉ  በሙሉና በከፊል ውድመት አድርሷል፡፡

  የወደሙ ትምህርት ቤቶችንም መልሶ ለማቋቋም ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በጋራ እየተሠራ መሆኑን ገልጸው፣ ግንባታውንም በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማከናወን ሒደት ላይ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

  የሕወሓት ቡድን ባደረሰው ጥቃትና ውድመት በአፋር ክልል በአራት ዞኖችና በ21 ወረዳዎች 694 ትምህርት ቤቶችን፣ በከፊል 65 ትምህርት ቤቶች ሙሉ ለሙሉ በአጠቃላይ 759 ትምህርት ቤቶችን ማውደሙ ተገልጿል፡፡

  የአፋር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዓሊ መሐመድን የሕወሓት ቡድን ያወደማቸውን ትምህርት ቤቶች መልሶ ለመገንባትና የትምህርት ሥራውን ለማስቀጠል በክልሉ ከተለያዩ ዘርፎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም አመራሮች የተካተቱበት ቡድን ወደ ሥራ ገብቷል፡፡ ለመልሶ ጥገናውና ግንባታው የሚያስፈልገው አጠቃላይ ወጪ ተሠልቶ በቅርቡ ይፋ ይደረጋል፡፡

  የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ በመጠገንና በመገንባት የትምህርት አገልግሎቶችን ለማስቀጠል ማኅበረሰቡ ርብርብ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

  በአፈጻጸማቸው ሞዴል በሆኑትና በአንጋፋ ትምህርት ቤቶች ላይ የደረሰው ጉዳት የከፋ መሆኑን የገለጹት፣ የጭፍራ ወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ መሐመድ አብዱ ናቸው፡፡  

  የሕወሓት ቡድን ያወደማቸውን ትምህርት ቤቶች መልሶ ለመገንባት በሚቻልበት ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በባህር ዳር ከተማ ውይይት ተካሄዷል፡፡

  ከደረሰው ሰብዓዊ ጥፋት በተጨማሪ፣ የትምህርትና ሌሎች ማኅበረሰቡ የሚገለገልባቸውን ማኅበራዊ ተቋማት በአማራ ክልል ብቻ ወሯቸው በነበሩ አካባቢዎች ከአራት ሺሕ በላይ ትምህርት ቤቶች ማውደሙንና በዚህም ምክንያት ከ1.9 ሚሊዮን በላይ ሕፃናትና ታዳጊዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸው ታውቋል፡፡

  የወደሙትን ትምህርት ተቋማት መልሶ ለመገንባትና ትምህርት ለማስጀመር ከ11 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግም የክልሉ ትምህርት ቢሮ በጥናት አመላክቷል፡፡

  የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ (ፕሮፌሰር) የወደሙ ትምህርት ቤቶች መልሰው ሲገነቡ በነበሩበት ደረጃ ሳይሆን፣ በተሻለ ጥራት እንደሚሆን ገልጸው፣ ለዚህም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በችግር የተተበተበው የሲሚንቶ አቅርቦት

  ሲሚንቶን እንደ ግብዓት ተጠቅሞ ቤት ማደስ፣ መገንባት፣ የመቃብር ሐውልት...

  ‹‹የናይል ዓባይ መንፈስ›› በሜልቦርን

  አውስትራሊያ ስሟ ሲነሳ ቀድሞ የሚመጣው በተለይ በቀደመው ዘመን የባህር...

  ‹‹ልብሴን ለእህቴ››

  ለሰው ልጅ መኖር መሠረታዊ ፍላጎት ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ ልብስ...

  የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የምርመራ ውጤት እስከምን?

  በፍቅር አበበ የትምህርት ጥራትን፣ ውጤታማነትንና ሥነ ምግባርን ማረጋገጥ ዓላማ አድርጎ...