በአርባምንጭ ከተማ ዛሬ ታህሣሥ 23 ቀን 2014 ዓም 13ኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ ተጓድሎ የነበረውን የምክትል ፕርዜዳንት ምትክና የሴቶች ጉዳይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሸሙት አፀደቀ።
የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሲያከናውናቸው በነበረው ሰብሰባ ላይ ለአንድ አመት ሳይገኙ የቆዩትን የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕረዚዳንት ኮሎኔል አወል አብዱራሂም ምትክ፣ የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑትን አቶ አበበ ገላጋይን ሾመ።
በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሜቴ መደበኛ ጉባዔ ላይ ያለ ፌዴሬሽኑ እውቅና ተሳትፈዋል ተብለው በጊዜያዊነት ታግደው የነበሩትን ወይዘሮ ሶፍያ አልማሙን ዕገዳ አንስቷል።
የቅድሞ ደደቢት እግር ኳስ ክለብ መስራችና የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕረዚዳንት ኮሎኔል አወል
በ1983 ዓ.ም ህወሓት አገሪቷን መቆጣጠሩን ተከትሎ፣ የአገር መከላከያ ስራዊት የሎጄስቲክና የንብረት ክፍል ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል። ደደቢት የወንዶች እግር ኳስ ክለብን አቋቁመው ለ16 ዓመታት መምራት የቻሉት ኮሎኔል አወል፣ በ2005 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ለመጀመሪያ ጊዜ ከክለቡ ጋር ማንሳት ችለዋል።
ከታህሳስ 23 እሰከ 24 ቀን 2013 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባሄውን በአርባ ምንጭ ያካሄደው ፌዴሬሽኑ፣ የቀጣዩን ጠቅላላ ጉባዔ በጎንደር ከተማ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
- Advertisement -
- Advertisement -