Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊዓለም አቀፍ የሚል መጠሪያ ያላቸው ትምህርት ቤቶች ስያሜቸውን በአስቸኳይ እንዲቀይሩ ማሳሰቢያ ተሰጠ

ዓለም አቀፍ የሚል መጠሪያ ያላቸው ትምህርት ቤቶች ስያሜቸውን በአስቸኳይ እንዲቀይሩ ማሳሰቢያ ተሰጠ

ቀን:

በኢትዮጵያ ሥርዓተ ትምህርት እያስተማሩ ‹‹ዓለም አቀፍ›› የሚል ስያሜ ለራሳቸው ሰጥተው የሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች፣ በአስቸኳይ ስያሜያቸውን እንዲያስተካክሉ ማሳሰቢያ ተሰጠ፡፡

በኢትዮጵያ ተመዝግበው ሳይፈቀድላቸውና ሕጉ ከሚያዘው ውጪ በዓለም አቀፍ ስያሜ፣ የሌሎች አገሮችን የትምህርት ሥርዓት የሚተገብሩ፣ ስማቸውን ብቻ ዓለም አቀፍ ብለው የኢትዮጵያን ሥርዓተ ትምህርት የሚከተሉ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን፣ በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ዳይሬክተር ሙሉቀን ንጋቱ (ዶ/ር) ለሪፖርተር ተናረዋል፡፡

አሁን ባለው መመርያ መሠረት አንድ ትምህርት ቤት ራሱን ‹‹ዓለም አቀፍ›› ለማለት ከኢትዮጵያ ውጪ ከሆነ አገር ሥርዓተ ትምህርት ይዞ መምጣት እንዳለበት የጠቆሙት ዳይሬክተሩ፣ ከመጣበት አገር ዕውቅና ተሰጥቶ በዚያ አገር ሕግ መሠረት በትምህርት መዝጋቢው አካል የተመዘገበ መሆኑ ተገምግሞና ማረጋገጫ ተሠርቶ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ያለውን ጉዳይ በመጨረስ መቅረብ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ይሁን እንጂ ባለፉት ጥቂት ወራት በተጀመረው ማጣራት፣ የተወሰኑ የትምህርት ተቋማት ከሕግ ውጪ ሲንቀሳቀሱ በመገኘታቸው፣ ሦስት ትምህርት ቤቶች እንዲሰተካክሉ ማስጠንቀቂያ እንደተጻፈላቸው ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ፣ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የትምህርት ሚኒስቴርን የግል የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥርን በተመለከተ፣ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ በ2012/2013 በጀት ዓመት የተከናወነ የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

በውይይቱ በ1987 ዓ.ም. በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣው የግል ትምህርት ተቋማት ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር ደንብ ቁጥር 206፣ እስካሁን ድረስ ያልተሻሻለና ከወቅቱ ጋር አብሮ የማይሄድ መሆኑን ቋሚ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡

ደንቡን ተከትሎም በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ መቋቋም የነበረበትና የትምህርት ተቋም ለማቋቋም የሚያግዝ መመርያ በትምህርት ሚኒስቴር እንደሚወጣ  ቢደነገግም፣  የግል አንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ተምህርት ቤቶች ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳትን በተመለከተ በሚኒስቴሩ የተዘጋጀ መመርያ አለመኖሩ በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም በአዲስ አበባ ከተማ ለሚንቀሳቀሱ ዓለም አቀፍና የማኅበረሰብ ትምህርት ቤቶች የምዝገባና የፈቃድ መሥፈርት መመርያ የለም ተብሏል፡፡

ይሁን እንጂ ባለፉት ስድስት ወራት የተለያዩ መመርያዎች ወጥተው እየተሠራባቸው መሆኑን ሙሉቀን (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡ አራት ዓለም አቀፍና የማኅበረሰብ ትምህርት ቤቶች በመመርያዎቹ መሥራት አንችልም ማለታቸውን ተናግረዋል፡፡

ትምህርት ቤቶቹ ከትምህርት ሚኒስቴር የሚመጣውን ትዕዛዝ ከውጭ ግንኙነትና ከሁለትዮሽ ግንኙነታቸው ጋር የሚጋጭባቸው እንደሆነ፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ግንኙነት እንዳላቸውና የገቡት ስምምነት አለመኖሩን በመግለጽ፣ ትምህርት ሚኒስቴር በእነሱ ጉዳይ ጣልቃ ሊገባ አይችልም የሚል ቅሬታ እንዳቀረቡ አክለው ገልጸዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴርም ከትምህርት ቤቶቹ ጋር እየተነጋገረ መሆኑን፣ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት በሚባል ስያሜ በአገር ውስጥ የትምህርት ሥርዓት የሚያስተምሩትን፣ በትምህርት አሰጣጣቸው ቅሬታ የሚነሳባቸውን ጨምሮ የሚያስተዳድራቸውን 26 ዓለም አቀፍና የማኅበረሰብና ትምህርት ቤቶች በሚያወጣው መመርያ መሠረት እንዲሠሩ ማሳሰቢያ መሰጠቱን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ከአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ጋር በተገናኘ አስተያየታቸውን የሰጡት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)፣ በኢትዮጵያ ከ47 ሺሕ በላይ ትምህርት ቤቶች እንዳሉ ጠቅሰው፣ አገሪቱ ባላት የትምህርት መሠረት ልማት 90 በመቶ የሚሆኑት ትምህርት ቤቶች ከደረጃ በታች መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

በኢትዮጵያ መሠረታዊ የሆነ የትምህርት ችግር እንዳለ የጠቀሱት ብርሃኑ (ፕሮፌሰር)፣ በትምህርት ሚኒስቴር በተደረገ የአስተማሪዎች ምዘና በአገሪቱ ካሉ አጠቃላይ መምህራን ውስጥ የተሰጠውን የብቃት ምዘና ማለፍ የቻሉት ከ20 በመቶ በታች መሆናቸው፣ በርዕሰ መምህርነት እያገለግሉ ነገር ግን የተሰጣቸውን የርዕሳነ መምህራን ፈተና ማለፍ የቻሉት 70 በመቶዎቹ ብቻ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...