Sunday, December 4, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየኮቪድ ክትባት ወስደው ስድስት ወራት የሞላቸው ተጨማሪ የማጠናከሪያ ክትባት እንዲወስዱ ተጠየቀ

  የኮቪድ ክትባት ወስደው ስድስት ወራት የሞላቸው ተጨማሪ የማጠናከሪያ ክትባት እንዲወስዱ ተጠየቀ

  ቀን:

  በኮሮና ቫይረስ በቀላሉ ላለመያዝ የመከላከል አቅምን የሚያጠናክረውና ለረዥም ጊዜ ሳይያዙ ለመቆየት የሚረዳውን የመጀመሪያና ሁለተኛ ዙር ክትባት ከወሰዱ ስድስት ወር የሞላቸው ዜጎች፣ ተጨማሪ የማጠናከሪያ ክትባት እንዲወስዱ የጤና ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡

  ከመጋቢት 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በመላው ኢትዮጵያ መሰጠት የጀመረውን የኮቪድ-19 ክትባት የወሰዱ ሰዎች ቁጥር ወደ አሥር ሚሊዮን መድረሱን፣ ክትባቱ መሰጠት ከጀመረ አንስቶ የተከተቡና ስድስት ወራት የሞላቸው ሰዎች ሦስተኛ ዙር ማጠናከሪያ ክትባት እንዲወስዱ በጤና ሚኒስቴር የኮቪድ-19 ምላሽ አስተባባሪ መብራቱ ማሴቦ (ዶ/ር) ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡

  የጤና ሚኒስትሯ ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) ከጥቂት ቀናት በፊት፣ ‹‹እንደ እኔ ከተከተባችሁ ስድስት ወራት ያለፋችሁ ተጨማሪ ክትባቱን ውሰዱ፤›› የሚል መልዕክት በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ማስተላለፋቸው ይታወሳል፡፡

  በርካታ አገሮች የሦስተኛ ዙር ማጠናከሪያ ክትባት መስጠት ከጀመሩ ሰንበትበት ያሉ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ዙር ክትባቱን እየወሰዱ ያሉ ዜጎች ቁጥር ዝቅተኛ በመሆኑ ምክንያት ዜጎች የመጀመሪያና ሁለተኛ ዙር ክትባት እንዲወስዱ ዘመቻ እየተደረገ እንደነበረ አስተባባሪው ተናግረዋል፡፡

  በመሆኑም ክትባቱን ቀደም ብለው የወሰዱ ሰዎች የመከላከል አቅም እየቀነሰ ከመምጣቱም በላይ፣ አዳዲስ የኮሮና ቫይረስ ዝርያዎች ሲፈጠሩ የመጀመሪያውና የሁለተኛው ዙር ክትባት ዝርያዎቹን የመከላከል አቅማቸው ውስን እንደሚሆን መብራቱ (ዶ/ር) አክለዋል፡፡  

  በጤና ተቋማት በርካታ የኮቪድ ክትባት ዓይነቶች እንደሚገኙ የገለጹት አስተባባሪው፣ መከተብ የሚፈልጉ ሰዎች መጀመሪያ የተከተቡትንም ሆነ ሌላ ዓይነት ክትባት መውሰድ እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡

  ምንም እንኳ አስገዳጅ ባይሆንም መከተብ ለሚፈልጉ ሰዎች የሚመከረው በመጀመሪያውና በሁለተኛው ዙር ሌላ ክትባት ከወሰዱ፣ በሦስተኛው ዙር የፋይዘር ክትባትን ቢወስዱ ይመረጣል ብለዋል፡፡

  በኢትዮጵያ ከጥቂት ወራት በፊት የክትባት እጥረት የነበረ ቢሆንም አሁን ግን በርካታ ሰዎችን መከተብ የሚያስችል ክምችት መኖሩን፣ ስድስት ወራ የሞላቸው ሰዎች በየትኛውም የጤና ተቋም ሄደው እንዲከተቡ አስተባባሪው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

  ከወራት በፊት በተደረገው የኪቪድ-19 ክትባት ዘመቻ ጥሩ ውጤት የተገኘበት ቢሆንም፣ በየጊዜው የክትባት ዘመቻ ለማድረግ ብዙ ሥራ ስለሚጠይቅ በጥር 2014 ዓ.ም. ሁለተኛ ዙር የክትባት ዘመቻ ለማካሄድ ዕቅድ መያዙን ተናግረዋል፡፡

  ኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ክትባት መስጠት በጀመረችበት ወቅት ተጋላጭ ለሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ብቻ ተለይቶ ሲሰጥ በኅብረተሰቡ ዘንድ ኩርፊያ እንደነበር፣ ነገር ግን የክትባቱ አቅርቦት እየጨመረ በዚያው ልክ ደግሞ የመከተብ ፍላጎት መጠኑ እየቀነሰ መምጣቱን መብራቱ (ዶ/ር) አስታውሰዋል፡፡

  ከኮቪድ-19 በሽታ ጋር በቀላሉ ለመላቀቅ እንደማይቻል ኅብረተሰቡ ሊረዳ እንደሚገባ የጠቆሙት አስተባበሪው፣ አሁን በቫይረሱ ተይዘው የሚሞቱት ያልተከተቡ በመሆናቸው ሁሉም ሰዎች ቢከተቡ ከወረርሽኝ ራስን ማዳን ይቻላል ብለዋል፡፡

  የኢትዮጵያ መንግሥት ከአጠቃላይ ሕዝቡ 14 በመቶ አካባቢውን ለመከተብ የሚያስችል ክትባት ለመግዛት ገንዘብ የመደበ ቢሆንም አሁን ግን በዕርዳታና በስጦታ የሚገኝ ክትባት በመኖሩ በመንግሥት በኩል የተመደበውን ገንዘብ ለመጠቀም አስገዳጅ ሁኔታ አለመኖሩን ገልጸዋል፡፡

   

   

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ዳግም ነፍስ የዘራው የተማሪዎች ማርች ባንድ

  የሙያው ፍቅር ያደረባቸው ገና በልጅነታቸው ነው፡፡ በ1970ዎቹ መጀመርያ፣ ለቀለም...

  በስንደዶና ሰበዝ የተቃኘው ጥበብ

  በአንዋር አባቢ ተወልዳ ያደገችው መሀል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ነው፡፡...

  አዲስ ጥረት የሚጠይቀው  ኤችአይቪ  ኤድስን  የመግታት  ንቅናቄ

  ‹‹ኤችአይቪ በመላው ዓለም  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ዋነኛ የሕዝብ...

  የኅትመት ብርሃን ያየው ‹‹የቃቄ ወርድዎት›› ቴአትር

  ከአራት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ይታይ...