Friday, December 8, 2023
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ በዴሞክራሲ ጉዳዮች ላይ እንዲሠሩ የተመደቡ ከፍተኛ ካድሬዎችን ሰብስበው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው]

  • ይህ ኮሚቴ የሰሜኑ ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ ለበርካታ ወራት መደበኛ ስብሰባዎችን ሳያደርግ በመቆየቱ ልንገነባው በምንፈልገው የዴሞክራሲ ሥርዓት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚኖረው በመሆኑ፣ ኮሚቴው ከዚህ በኋላ ወደ መደበኛ ሥራው እንዲመለስ ማሳሰቢያ ለመስጠት ነው የዛሬው ስብሰባ የተጠራው። 
  • ጥሩ ነው ክቡር ሚኒስትር፣ ተገቢ ነው።
  • አዎ፣ ምክንያቱም የሰሜኑ ግጭት መጠናቀቁ አይቀርም፣ ይህ ግጭት ሲያበቃ ማኅበረሰቡ የዴሞክራሲ ጥያቄዎቹን ማንሳቱ ግልጽ ነው፣ ዝም አይለንም፣ አሁን ሥራችንን ካልሠራን ያኔ ምን ልንመልስ ነው?
  • ልክ ነው ክቡር ሚኒስትር፣ ሥራችንን ከወዲሁ መጀመርና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የመትከል ኃላፊነታችንን መወጣት መጀመር አለብን።
  • በጣም ጥሩ፣ በዚህ ከተግባባን ለዛሬው ውይይት ከተመረጡ አጀንዳዎች ውጪ መነሳት አለበት የምትሉት ጉዳይ ካለ ማስያዝ ትችላላችሁ፣ ከሌለ ወደ ተያዙት አጀንዳዎች ማለፍ እንችላለን።
  • ኧረ አለ… ከጀርባ አካባቢ እጅ ይታየኛል ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እሺ… ከጀርባ… ሐሳብህን መቀጠል ትችላለህ…!
  • አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር… ለማንሳት የፈለግኩት አንዳንድ ተፎካካሪ ፖርቲዎች ካቢኔ እየመሠረቱ ይገኛሉ፣ ይህ እንቅስቃሴ ለመትከል ከምንፈልገው ዴሞክራሲያዊ ባህልና ሥርዓት አንፃር እንዴት ይታያል የሚለውን ብንመለከት ለማለት ነው፡፡
  • ካቢኔ እየመሠረቱ ነው ያልከው? 
  • አዎ ክቡር ሚኒስትር አንዳንድ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ትይዩ ካቢኔ ማቋቋም ጀምረዋል።
  • ትይዩ ማለት?
  • የመንግሥት ካቢኔ ትይዩ የሚሆን የእነርሱ ካቢኔ እንደ ማለት ቢሆንም ዓላማው ግን መንግሥት ለመሆን ሳይሆን፣ የመንግሥትን የሥራ አፈጻጸም በመተቸት የዳበረ ዴሞክራሲን ለመገንባት፣ እንዲሁም የእነሱ ካቢኔ ቢሆን ምን ሊያደርግ እንደሚችል፣ አማራጭ ፖሊሲው ምን እንደሆነ ለማስተዋወቅ በማለት ትይዩ ካቢኔ ማቋቋማቸውን ነው የገለጹት። 
  • ካቢኔው እንደኛ ካቢኔ ሚኒስትሮች አሉት? 
  • አሉት ክቡር ሚኒስትር፣ እያንዳንዱ የትይዩ ካቢኔው አባል የሆነ ሚኒስትር የእኛን ትይዩ ሚኒስትር ይከታተላል። 
  • ፓርላማስ አላቸው?
  • ፓርላማ እንኳን የላቸውም፣ ግን የፓርቲውን ጠቅላላ ጉባዔ እንደ ፓርላማ ሊቆጥሩት ይችላሉ። 
  • እህ… ይህች ባቄላ ያደረች እንደሆነ… አለ የአገሬ ሰው፣ ሌሎቻችሁ ምን ትላላችሁ? …ጥግ ላይ ቀጥል 
  • ክቡር ሚኒስትር እኔም እርስዎ እንዳሉት ነው ማለት የምችለው…
  • እኔ ምንድነው ያልኩት?
  • ይህች ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም እንዳሉት…
  • እኔ አትቆረጠምም አላልኩም… ወጣኝ እንደዚያ?
  • በእርግጥ አልጨረሱትም… ግን…
  • ግን እኔም ያለኝ ሥጋት ተመሳሳይ ነው ለማለት ነው።
  • እኮ ሥጋትህን ማቅረብ ትችላለህ፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር በእኛ ካቢኔ ውስጥ አባል እንዲሆኑ ካደረግናቸው በኋላ ትይዩ ካቢኔ ማቋቋም ምን ማለት እንደሆነ መጠናት አለበት፣ የእኛን ካቢኔ አይመጥንም ማለተቻው ነው? ይህ ጉዳይ በፍጥንት ተጠንቶ ዕርምጃ መወሰድ አለበት የሚል አስተያየት ለመስጠት ነው፡፡
  • ምን ዓይነት ዕርምጃ መውሰድ ይቻላል ብለህ ታምናለህ?
  • አንዱን ምረጡ መባል አለባቸው፡፡
  • አንዱን ምረጡ ማለት?
  • ወይ የእኛን ካቢኔ ወይ ትይዩ ካቢኔውን፡፡
  • እሺ እዚያ መካከል ላይ ያለኸው… አዎ አንተ…
  • ክቡር ሚኒስትር ይምረጡ ብቻ ሳይሆን የሕግ ተጠያቂነትም መከተል አለበት።
  • እንዴት አድርገን?
  • ክቡር ሚኒስትር ስም ቀይረው ትይዩ ይበሉ እንጂ ያደረጉት ነገር አዲስ አይደለም፣ ቀደም ሲልም በሌላ ስያሜ ሞክረውታል፡፡
  • ምን ብለው?
  • ባለ አደራ አስተዳደር፡፡
  • እህ…?
  • ስለዚህ በሕግ ተጠያቂ መሆን አለባቸው፣ አለበለዚያ…
  • አለበለዚያ በተመሳሳይ ምክንያት የከሰስናቸውን መልቀቅ አለብን፣ ይህ ካልሆነ ግን የፍትሕ ሥርዓታችን መዘባበቻ ይሆናል፡፡
  • እስቲ አትቸኩል፣ ለማንኛውም ሌሎች ጉዳዮችን በይደር እናቆይና ከሚመለከተው አመራር ጋር ተወያይተን አቋም እንይዘበታለን።
  • እስከዚያስ?
  • እስከዚያማ ስለትይዩ ካቢኔ የዓለምን ልምድ እናጠናለን!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...

ኦሮሚያ ኢንሹራንስ በግሉ ኢንሹራንስ ዘርፍ ሁለተኛውን የገበያ ድርሻ ለመያዝ ያስቻለውን ውጤት ማስመዝገቡን ገለጸ

ኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ የባንኮች የጥሬ ገንዘብ እጥረት፣ የመለዋወጫ ዕቃዎች...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ ነው? እንዴት? አለቃዬ ዕረፍት የለው፣ እኔንም አላፈናፍን ብሎኛል። ታድለሽ። ታድለሽ? ሥራ ገደለኝ ዕረፍት አጣሁ እኮ ነው ያልኩሽ? ገብቶኛል። ምነው እኔንም...

[ክቡር ሚኒስትሩ የሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸማቸውን ለተከበረው ምክር ቤት ካቀረቡ በኋላ ከምክር ቤቱ አባላት የሚነሱ ጥያቄዎችን እየተቀበሉ ማብራሪያ በመስጠት ላይ ናቸው]

ክቡር ሚኒስትር መንግሥት ለሕዝብ ይፋ ያደረገው ነገር ከምን እንደደረሰ ቢያብራሩልን? ምንድነው ይፋ ያደረገው? ጥያቄውን ትንሽ ቢያብራሩት? ከአራት ዓመት በፊት በኦጋዴን አካባቢ ነዳጅ መገኘቱን ለሕዝብ በቴሌቪዥን አብስሮ...

[ክቡር ሚኒስትሩ አንድ የካቢኔና የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ አባል የሆኑ ከፍተኛ አመራር የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያደመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል አግኝቼ ላነጋግርዎት የፈለግኩት። ጥሩ አደረግህ፣ ምን አሳሳቢ ነገር ገጥሞህ ነው? ክቡር ሚኒስትር ተወያይተንና ተግባብተን ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች፣ በተለይም...