ከኦሮሚኛ ድምፃዊው ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ ከሰኔ 23 ቀን 2012 ዓም ጀምሮ በእስር ላይ የነበሩትና ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩት አቶ እስክንድር ነጋና አቶ ስንታየሁ ቸኮል ዛሬ ታህሣሥ 29 ቀን 2014 ዓም ማምሻውን ከእስር መለቀቃቸው ታውቋል።
አቶእስክንድርና አቶ ስንታየሁ የተለቀቁት ከቂሊንጦ እስረኛ ማቆያ ሲሆን አብረዋቸው የታሰሩትና ክስ የተመሰረተባቸው ወ/ሮ አስካለ ደምሌና ወ/ሮ ቀለም ስዩም በቃሊቲ ማረሚያቤት መሆናቸው ቢታወቅም ስለመለቀቃቸው የተባለ ነገር የለም።
የፌደራል ዓቃቤ ሕግ ስድስት ምስክሮቹን ካሰማ በኋላ ብይን እንዲሰጥለት ፍርድ ቤትን ጠይቆ ቀጠሮ ከመሰጠቱ ውጭ፣ የተፈቱበት ምክንያት አልተገለጸም።
ሁሉም ተከሳሾች የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፖርቲ አመራሮች መሆናቸው ይታወቃል።