Sunday, March 26, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ባንኮች ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ማድረግ ያለባቸው የውጭ ምንዛሪ ወደ 70 በመቶ ሊያድግ ነው

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

በሳምንት ከአምስት ጊዜ በላይ ገንዘብ ማንቀሳቀስ የሚከለክለው ሕግ ሊነሳ ነው

ባንኮች በተለያዩ መንገዶች ከሚያገኙት የውጭ ምንዛሪ በዕለታዊ የውጭ ምንዛሪ ዋጋ፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገቢ የሚያደርጉት መጠን ወደ 70 በመቶ ሊያድግ መሆኑ ታወቀ፡፡

የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ ካለፈው ነሐሴ 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ባንኮች ከሚያገኙት የውጭ ምንዛሪ 50 በመቶ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገቢ እንዲያደርጉ የሚያስገድደው ሕግ ተግባራዊ ሲደረግ ቆይቷል፡፡ ይህ መመርያ ግማሽ ዓመት ሳይሆነው እንደገና እንዲሻሻል ተደርጓል፡፡

ይህንን የመንግሥት ውሳኔ ባንኮች እንዲያውቁት ማድረጉን፣ ከዚህ በኋላ ባንኮች 70 በመቶ የውጭ ምንዛሪ ግኝታቸውን ገቢ እንዲያደርጉ የሚደነግገው መመርያ እንደሚደርሳቸው የምንጮች መረጃ ያመለክታል፡፡ ውሳኔው ለተወሰነ ጊዜ ተግባራዊ እንደሚደረግ ብሔራዊ ባንክ ለባንኮች ያስታወቃቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ባንኮች ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ማድረግ የሚገባቸው የውጭ ምንዛሪ መጠን ከዚህ ቀደም 30 በመቶ የነበረ ሲሆን፣ ባለፈው ነሐሴ ወር ይህ መጠን ወደ 50 በመቶ ከፍ እንዲል መወሰኑ አይዘነጋም፡፡ መንግሥት መጠኑን ወደ 70 በመቶ ከፍ ያደረገበት ምክንያት ለባንኮች የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም ከወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ የሚያስፈልገውን የውጭ ምንዛሪ በዚህ መልክ ለመሸፈን ታቅዶ ነው፡፡

የነዳጅ ዋጋ መጨመርና አስፈላጊ ለሚባሉ ምርቶች የመንግሥት የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት ከፍ እያለ በመምጣቱ፣ ባንኮች ከሚያሰባስቡት የውጭ ምንዛሪ ብልጫ ያለውን ለብሔራዊ ባንክ ገቢ እንዲያደርጉ አስገድዷል፡፡ ባንኮች ለብሔራዊ ባንክ ይህንን የውጭ ምንዛሪ ገቢ ሲያደርጉ፣ በዕለቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን ተመንዝሮ ተመላሽ ይደረግላቸዋል ተብሏል፡፡

ባንኮች ከውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት፣ ከዳያስፖስራ ሒሳብና ከሌሎች ምንጮች ከሚያገኙት የውጭ ምንዛሪ 70 በመቶ ለብሔራዊ ባንክ በቅርቡ ገቢ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር በሳምንት ከአንድ አካውንት ከአምስት ጊዜ በላይ ገንዘብ ማውጣትና መላክ የሚከለክለውን መመርያ፣ እንደሚያሻሽልና ገደቡን እንደሚያነሳ አስታውቋል፡፡ የዕገዳውን መነሳት በሚመለከት የወጣው መመርያ ለባንኮች ይደርሳል ተብሎ እየተጠበቀ ነው ተብሏል፡፡

ይህ መመርያ በቆየባቸው ጊዜያት ብዙ ኩባንያዎች ክፍያዎችን ለመፈጸምም ሆነ ለመቀበል አዳጋች እየሆነባቸው በሥራቸው ላይ ጫና ሲያሳርፍ መቆየቱን፣ በተለያዩ መንገዶች ሲገልጹ እንደነበር አይዘነጋም፡፡     

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች