የጌታችን የልደት ቀን መቃረብ ምክንያት በማድረግ በሃምሳዎቹ ዓ.ም. የነበርን የአዲስ አበባ ልጆች የገና መጫወቻ ዱላ በአካባቢያችን ከሚገኙት ጫካዎች በመሄድ እናዘጋጅ ነበር፡፡ በተፈጥሮ ቆልመም ያለችውን የባህር ዛፍ ከግንዱ ላይ በማለያየትና ወደቤት ይዘን በመሄድ በልካችን ቆርጠን፣ ከላጥን በኋላ እገናው ዱላ ላይ በመጠቅለል እናስራለን፡፡ ከዚያም ከጋገራ ያለቀ ሙቅ አመድ ውስጥ ቀብረን ካቆየን በኋላ አውጥተን የተጠቀለለውን ስንፈታው ሙቀት ያገኘው ሲጠቁር፣ በልጥ የተጠቀለለው መልኩን ሳይቀየር ይቀራል፡፡ ባጠቃላይ ዥጉርጉር መልክ ይላበሳል፡፡ ከዚያ (የኮሚዶሮ ቆርቆሮ በማጣመም ድብልቡል እንዲሆን በማድረግ ባካባቢያችን ባለው ሜዳ ላይ ተቧድነን እንጫወት ነበር፡፡
ፎቶ ከማኅበራዊ ገጽ
- ክንፈሚካኤል ሀብተማርያም