ኢትዮጵያና የምሥራቅ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች በምሥራቃዊው የኒቅያ ካሌንደር (ግብፅ፣ ኢትዮጵያ፣ ጁሊያን) መሠረት የገና በዓልን ታኅሣሥ 29 ቀን 2014 ዓ.ም. እንደየትውፊታቸው አክብረዋል፡፡ ካሌንደሩ በ325 ዓ.ም. የኒቅያ ቅዱስ ጉባዔ ላይ ይፋዊ የቤተ ክርስቲያን ካሌንደርነትን የተቀዳጀ ነው፡፡ በዓሉን ያከበሩት ምሥራቃውያን አብያተ ክርስቲያናት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፣ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፣ የእስክንድርያ ኮፕቲክ፣ የአርመን ሐዋርያት ኦርቶዶክስ (ኢችሚዚን)፣ የአርመን ኦርቶዶክስ (ግሬት ሲሊሲያ፣ አንቴሊያስ)፣ የኢየሩሳሌም ሮማን ኦርቶዶክስ፣ የሩሲያ ኦርቶዶክስ፣ የጆርጂያ ኦርቶዶክስ፣ የሰርቢያ ኦርቶዶክስ፣ የዩክሬን ኦርቶዶክስ፣ የዩክሬን ግሪክ ካቶሊክ፣ የዩክሬን ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ናቸው፡፡ ፎቶዎቹ የየአገሮቹን ትውፊታዊ አከባበር ያሳያሉ፡፡
ፎቶ ኦሬንታል ኦርቶዶክስ