Friday, July 12, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልኪነጠቢብ ዓለምዬ መብሬ (1939-2014)

ኪነጠቢብ ዓለምዬ መብሬ (1939-2014)

ቀን:

ከሦስት አሠርታት በላይ በኢትዮጵያ ባህላዊ ሙዚቃ ዓውድ ውስጥ ይበልታን ተቀዳጅቷል፡፡ ከመጀመርያው የቴአትር ተቋም ሀገር ፍቅር እስከ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ባገለገለባቸው ሠላሳ ሦስት ዓመታት ከማሲንቆ ተጫዋችነት እስከ ድምፃዊነት፣ ከባህል ቡድን ኃላፊነት እስከ አሠልጣኝነት፣ ከመድረክ እስከ ፊልም ተዋናይነት አገልግሏል፡፡ ማን ቢሉ አንጋፋው ኪነጠቢብ ዓለሜ መብሬ፡፡

ገጸ ታሪኩ እንደሚያሳየው፣ ዓለሜ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በተዋናይነት የተሳተፈባቸው «አምታታው በከተማ» ‹‹1929›› እና ‹‹የባላገር ፍቅር›› ቴአትሮች በተመልካች ዘንድ ታላቅ አድናቆትን ያተረፈባቸው ነበሩ፡፡

በተጨማሪም የባህል ቡድን ኃላፊ ሆኖ ለረጅም ዓመታት ሲያገለግል በነበረበት ጊዜ በአሠልጣኝነት፣ በመሲንቆ ተጫዋችነትና በድምፃዊነት ለአገር ባህል ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከት መቻሉን እናት መሥርያ ቤቱ ይመሰክርለታል፡፡

ከያኒ ዓለምዬ ጥበባዊ ጉዞው አሐዱ ብሎ የሚጀምረው በትውልድ አካባቢው፣ በ1958 ዓ.ም. በላሊበላ ቱሪስት ድርጅት ውስጥ በባህል ሙዚቃ ተጫዋችነት ለሦስት ዓመት በማገልገል ነው፡፡ በ1961 ዓ.ም. አጋማሽ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ሀገር ፍቅር ቴአትር ቤትን ተቀላቅሏል፡፡

ከስድስት ዓመታት ቆይታ በኋላ በየካቲት 1976 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ባልደረባ በመሆን ጡረታ እስከወጣበት 1994 ዓ.ም. ድረስ 33 ዓመታት በባህል ቡድን ኃላፊነት በማሲንቆ ተጫዋችነት፣ በድምፃዊነትና በተዋናይነት በርካታ ሥራዎች ላይ የተሳተፈ አንጋፋ ከያኒ ነበረ፡፡

ኪነጠቢቡ ዓለምዬ መብሬ ከጥበባዊ ተግባሩ ባሻገር በሀገር ፍቅርና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ሲቀርቡ በነበሩት የተለያዩ አገራዊ የበዓል ኘሮግራሞች ላይ በአዘጋጅ ኮሚቴ አባልነት፣ የባህል ቡድኑን በመምራት በውጭ አገርና በአገር ውስጥ በርካታ ዝግጅቶችን ለሕዝብ ያቀረበ መሆኑንና የላቀ አስተዋጽኦ ማድረጉን የሥራ ባልደረቦቹና የግል ማህደሩ ይመሰክራሉ፡፡

በሥራው በርካታ ሽልማቶችንና የምስክር ወረቀቶችን የተቀበለ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥም የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤትን ለዓለም አቀፍ የጎልድ ሜርኩሪ ሽልማት አሸናፊነት እንዲበቃ ላበረከተው አስተዋጽኦና ለረጅም ጊዜ ቅን አገልግሎቱ የምስጋና የምስክር ወረቀቱ ይጠቀሳል፡፡

በኃላፊነቱውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ ሥራዎችን ለማቅረብ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ ለሙያተኞቹ አርዓያ በመሆን የተሰጠውን ተልዕኮ ከግብ የሚያደርስ መሆኑን የሚገልጽ የምስክር ወረቀትም ተበርክቶለታል፡፡

በባህልና ስፖርት ኒስቴ ትዕዛዝ ለየትኖራ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማኅበር ላበረከተው አስተዋጽኦ፣ኅበሩ ከሽልማት በተጨማሪ በማኅበሩ የታሪክ መዝገብ ውስጥ ስሙ እንዲመዘገብ አድርጎለታል፡፡

ከያኒውለምዬ መብሬ 1994 .ም. ጡረታ የወጣ ቢሆንም በግሉ በርካታ ፊልሞችና ማስታወቂያዎችን መሥራት ችሏል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ‹‹ፈንጂ ወረዳ›› በተሰኘው ፊልም ውስጥ የንሥሐ አባት /የቄሱን/ ገጸ ባህርይ በብቃት በመተወን አድናቆትን ማትረፍ የቻለ ድንቅ ከያኒ እንደነበር ገጸ ታሪኩ ዘግቦታል፡፡

ከአባቱ ከአቶ መብሬ ነበበና ከእናቱ ከወ/ ጣይቱ አስረሴ የካቲት 1 ቀን 1939 ., በወሎ ጠቅላይ ግዛት ላስታ አውራጃ የተወለደው ዓለምዬ መብሬ፣ ዕድሜው ለትምህርት ሲደርስ በዚያው በላስታ አካባቢ በሚገኝ ላስታ አውራጃ ትምህርት ቤትና በአዲስ አበባ ውስጥ  እስከ ስምንተኛ ክፍል ድረስ መማር ችሏል፡፡

ኪነጠቢብ ዓለምዬ ባደረበት ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ጥር 1 ቀን 214 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት የተለየ ሲሆን፣ በማግስቱ በዓለም ባንክ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ቀብሩ ተፈጽሟል፡፡

ነፍስ ኄር ዓለምዬ መብሬ ባለትዳርና የሁለት ወንድና ሦስት ሴት አባት የነበረ ሲሆን ስድስት የልጅ ልጆችንም አይቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የሰብዓዊ መብት ጉዳይና የመንግሥት አቋም

ሰኔ ወር አጋማሽ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ከፍተኛ የሰብዓዊ...

ከሰሜኑ ጦርነት አገግሞ በሁለት እግሩ ለመቆምና ወደ ባንክነት ለመሸጋገር የተለመው ደደቢት ማክሮ ፋይናንስ

በኢትዮጵያ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ በቀዳሚነት ስማቸው ከሚጠቀሱት ውስጥ ደደቢት...