Saturday, November 26, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየጤና ሚኒስቴር ከቀናት በኋላ የኮቪድ-19 የክትባት ዘመቻ ለሁለተኛ ጊዜ እንደሚያካሂድ አስታወቀ

  የጤና ሚኒስቴር ከቀናት በኋላ የኮቪድ-19 የክትባት ዘመቻ ለሁለተኛ ጊዜ እንደሚያካሂድ አስታወቀ

  ቀን:

  የጤና ሚኒስቴር በኅዳር ወር 2014 ዓ.ም. ላይ ያካሄደው ዓይነት የኮቪድ-19 የክትባት ዘመቻ፣ ከተያዘው ጥር ወር መጨረሻ አንስቶ ለሁለተኛ ጊዜ እንደሚያካሂድ ገለጸ፡፡

  ሚኒስቴሩ የኮቪድ-19 ክተባ በተፈለገው መጠን እየሄደ አለመሆኑን በመጥቀስ ከኅዳር 6 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ከሁለት ሳምንት በላይ የዘለቀ አገር አቀፍ የክትባት ዘመቻ አካሂዶ ነበር፡፡ በጎዳናዎች ጭምር ሲያካሂደው በሰነበተው የመጀመርያው የክትባት ዘመቻ፣ በ15 ቀናት ውስጥ 5.5 ሚሊዮን ሰዎችን መከተብ መቻሉን የሚኒስትሩ የብሔራዊ ክተባ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዮሐንስ ላቀው ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

  እንደ አስተባባሪው ገለጻ በጤና ተቋማት ውስጥ ተገድቦ የነበረውን የክተባ ሒደት በዘመቻ መልክ ማስቀጠሉ እንደ ‹‹መልካም ተሞክሮ›› የታየ ሲሆን፣ ለዚህም ሲባል ይህንን ዘመቻ ከቀናት በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ለማድረግ ዕቅድ ተይዟል፡፡ አቶ ዮሐንስ ‹‹እጃችን ላይ በቅርቡ ያገኘነው ወደ አሥር ሚሊዮን ዶዝ አለ፡፡ ይህንን በዘመቻ ካልሰጠን በጤና ተቋማት ብቻ እየተሰጠ አይቀጥልም፤›› ብለዋል፡፡

  እንዲህ ዓይነት ዘመቻዎች የሚካሄዱት ብዛት ያላቸው ሰዎችን በማንቀሳቀስ መሆኑን ያስታወሱት አቶ ዮሐንስ፣ ዘመቻ ማድረግ ቀላል የማይባል ጊዜና ወጪን እንደሚጠይቅ ተናግረዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ለሁለተኛ ጊዜ የሚደረገው የክትባት ዘመቻ በአማካይ ከአሥር ቀናት ለማይበልጥ ጊዜ እንደሚቆይ አስታውቀዋል፡፡

  የጤና ሚኒስቴር የኮቪድ-19 ክትባትን መስጠት በጀመረበት ጊዜ ክትባቶቹን ማግኘት ፈተና ሆኖበት መቆየቱ የተገለጸ ሲሆን፣ አሁን ላይ ደግሞ ከአመለካከትና ሌሎች ችግሮች የተነሳ የክተባ ሒደቱ እንደሚፈለገው እንዳልሆነ ተነግሯል፡፡ የአውሮፓውያኑ 2022 ከመግባቱ በፊት 20 ሚሊዮን ሰዎችን የመከተብ ዕቅድ ይዞ የነበረው የጤና ሚኒስቴር፣ እስካሁን መከተብ የቻለው 9.4 ሚሊዮን ሰዎችን ነው፡፡ ከእነዚህ ውስጥም ክትባቱን ሙሉ ለሙሉ የወሰዱት አራት ሚሊዮን ያህሉ ብቻ ናቸው ተብሏል፡፡

  ጤና ሚኒስቴር አገር አቀፍ የክትባት ዘመቻዎችን ማካሄድ ክትባቱን በስፋት ለሕዝቡ ለመስጠት ካለው ጥቅም ባሻገር፣ ክትባቶቹ የአገልግሎት ጊዜያቸው እንዳያልፍ እየተጠቀመበት መሆኑን አቶ ዮሐንስ አስታውቀዋል፡፡ ከዚህ በፊት አዲስ አበባ ውሰጥ የክትባት ዘመቻ የተደረገው ሁለት ጊዜ መሆኑን አስታውሰው፣ በከተማዋ ዘመቻው ለሁለተኛ ጊዜ የተካሄደው በከተማ አስተዳደሩ እጅ ያሉ ክትባቶች ‹‹ሊበላሹ ይችሉ›› እንደነበር አስረድተዋል፡፡

  ከዚህ በፊት በነበረው አሠራር ወደ ኢትዮጵያ ሲላኩ የነበሩት የኮቪድ-19 ክትባቶች የአገልግሎት መጠቀሚያ ጊዜያቸው ሁለትና ሦስት ወራት እንደነበር ያሰረዱት አስተባባሪው፣ በዚህ የተነሳ ክትባቶቹ የአገልግሎት ጊዜያቸው ሊያልፍ ይችላል የሚል ሥጋት ተፈጥሮ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ይሁንና ከአራት ወራት ወዲህ መንግሥት የአገልግሎት ጊዜያቸው ከስድስት ወራት ያነሰ ክትባቶችን ላለመቀበል ወስኖ፣ በእዚያ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

  እንደ አስተባባሪው ገለጻ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ የኮቪድ-19 ክትባቶች ውስጥ ዝቅተኛ የመጠቀሚያ ማብቂያ ቀነ ገደብ ያለው ፋይዘር ክትባት ሲሆን፣ ይህ ክትባት በቀሩት የሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ አገልግሎት ላይ እንደሚውል ገልጸዋል፡፡ ይሁንና የፋይዘር ክትባት መቀመጥ ያለበት ከኔጌቲቭ 60 እስከ ከኔጌቲቭ 80 ባለው የቅዝቃዜ መጠን ውስጥ እንደሆነ አስረድተው፣ ከዚያ ወጥቶ ከሁት እስከ ስድስት ዲግሪ ሴንቲግሬድ ውስጥ ከሆነ የመጠቀሚያ ጊዜው ወደ አንድ ወር እንደሚያጥር ተናግረዋል፡፡

  የጤና ሚኒስቴር ከተቀበላቸው የኮቪድ-19 ክትባቶች ውስጥ እስካሁን የመጠቀሚያ ጊዜው ተጠናቆ የተወገደ እንደሌለ የተናገሩት አስተባባሪው፣ እንደ በአቀማመጥ ብልሽትና በመሳሰሉ ችግሮች የባከኑና የተወገዱ ክትባቶች መኖራቸውን አስታውቀዋል፡፡ በየክልሎቹ ያለውን መረጃ እየሰበሰበ በመሆኑ ምን ያህል ክትባቶች እንደተወገዱ መናገር አዳጋች እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

  አቶ ዮሐንስ ማንኛውም ክትባት ተጠባቂ የሆነ ብክነት እንደሚያጋጥመው አስረድተው፣ ሌሎች ክትባቶችም ሲመጡ ከ15 እከ 20 በመቶ ብክነት ይኖራል ተብሎ እንደሚጠበቅ አብራርተዋል፡፡ አሁን ባክነው የተወገዱት የኮቪድ-19 ክትባቶች ብዛትም በዚህ ወሰን ውስጥ ይሆናል የሚል ግምታቸውን አስረድተዋል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የትርፍ መጠኑን በ127 በመቶ ያሳደገው አቢሲኒያ ባንክ ካፒታሉን በ2.5 ቢሊዮን ብር እንዲያድግ ወሰነ

  የአቢሲኒያ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩ  ካፒታል በ2.5 ቢሊዮን ብር...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን 55 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ወሰነ

  የአዋሽ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ ዛሬ ህዳር 17 ቀን 2015...

  ከብሔራዊ ባንክ እውቅና ያገኘው ፔይሊንክ አክሲዮን ማህበር ምሥረታውን አካሄደ

  ከገንዘብ ንክኪ ነፃ የሆነ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ለመተግበር ያቀደው...