ሊቁ [መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ] አንዳንድ በፍቅረ ንዋይ ተሸንፈው ከእውነት መንገድ የሚወጡ ሰዎችን የገለጹበት ምሳሌ ቀልብ የሚስብ ነው፡፡ እንዲህ ይላሉ፡- ‹‹ነገር ግን አንዳንድ ዛቅ [የእኽል ጥራጊ] የለመዱ ከብቶች ቀን ሲበሉት የዋሉት አልበቃቸው ብሎ ሌሊት አጥር ሰብረው ወጥተው ላውሬ እንደሚሆኑ ኹሉ፣ አንዳንድ ሰዎችም በፍቅረ ንዋይ ተሸንፈው ጌታውን የሸጠ ይሁዳን አብነት አድርገው ለሆዳቸው ሲሉ ከሕገ ወንጌል ቅጽር ወጥተው ሲገኙ የዲያብሎስ ፈንታ መሆናቸው አይቀርም፡፡››
በፍቅረ ንዋይ ተይዘው ንዑድ ክቡር የሆነውን ውድ መንፈሳዊ ሀብት ሁሉ አቃልለው ለሚሄዱ ወይም በሌላ አነጋገር ከመና በኋላ ሽንኩር ለሚናፍቁ ሁሉ ይህ የእነሱ ምሳሌ ነው፡፡
- መምህር በአማን ነጸረ እና ሌሎች ‹‹አድማሱ ጀንበሬ ሕይወቱ፣ ወሐተታ መጻሕፍቱ›› (2011 ዓ.ም.)