ቅኔ ቀጥተኛ ትርጉሙ ‹‹መግዛት›› ማለት ነው፡፡ ምሥጢሩ እያንዳንዱ ሰው አዲስ አዲስ ምሥጋና እየደረሰ ለማቅረብ ለፈጣሪው መገዛቱን የሚገልጥበትን ሁኔታ ይገልጣል፡፡
አንድም ሕዋሳተ አፍአን፣ ሕዋሳተ ውስጥን ለሕሊና አስገዝቶ በተወሰነ ቁጥር ሐሳብ የሚታሰብ ስለኾነ በቅኔ ምሥጢር ልቡ የተነካ ሰው ቅኔ በሚያስብበት (በሚቈጥርበት) ጊዜ በፊቱ የሚያየውን ነገር እያየ አያይምና፤ እየሰማ አይሰማምና የሰውን ስሜት በመግዛቱ ‹‹ቅኔ›› ተብሏል፡፡
- መልአከ ብርሃን አድማሱ ‹‹መጽሐፈ ቅኔ›› (1961 ዓ.ም.)