Sunday, February 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየ ‹‹ዳጉ›› ሐሳብን በሥዕል

የ ‹‹ዳጉ›› ሐሳብን በሥዕል

ቀን:

በአፋር በቀላሉና በአጭር ጊዜ ውስጥ መረጃዎች ወደ ሁሉም ማኅበረሰብ ጆሮ እንዲደርስ የዳጉ አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው። በአካባቢው የተሰማችና የታየች ነገር አታመልጥም፡፡ ይህም በአፋር ባህላዊ የመረጃ ልውውጥ ሥርዓት ‹‹ዳጉ›› አማካይነት የሚፈጸም ነው፡፡

ዳጉ የመነጋገርና የመወያየት ማሳያ ከመሆን ባሻገር ከሁለት በኩል የሚመጡ መረጃዎችን አጣጥሞ ለሌላውማቀበል ባህላዊና ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡

ከወደ ጥበቡ መንደር ደግሞ ‹‹ዳጉ›› ጽንሰ ሐሳብ በሥዕል ለማንፀባረቅ ባለፈው ሳምንት ዓውደ ርዕይ ተከፍቷል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በሠዓሊያን ለይኩን ናሁሠናይ እና ዳንኤል ዓለማየሁ ‹‹ዳጉ›› የተሰኘ የሥዕል ዓውደ ርዕይ በጉራምዓይኔ የሥነ ጥበብ ማዕከል ጥር 6 ቀን 2014 .ም. ለሕዝብ ዕይታ ክፍት ሆኗል።

በዘመንኛ የሥነ ጥበብ ዓውድ በሰፊው እየተተገበሩ ካሉ ዘዬዎች (ስታይል) መካከልሠዓልያኑ ዳንኤል ዓለማየሁና ለይኩን ናሁሠናይ በዓውደ ርዕዩ ያቀረቧቸው ሙከራዎች (ኤክፐርሜንታል) ቅይጥ ቁስ (ሚክስድ ሚዲያ) እና በመደርደርና በመንኮልኮል (ኢንስታሌሽን) ላይ ያተኮሩ መሆናቸውን በዓውደ ርዕዩ መክፈቻ ተገልጿል፡፡

ለዓውደ ርዕዩ መግለጫ በተዘጋጀው ፖስተር ላይ የተጠቀሙት ሥዕል ሁለት ወንበሮችን ሲሆን በውስጣቸው የተለያዩ ጽንሰ ሐሳቦች ያሉበት መሆኑን ሠዓሊያኑ ይገልጻሉ፡፡

ከሁለቱ ወንበሮች በአንደኛው የተሣለበት ቅርፅናሌላኛው የለበሰው ጨርቅ ደግሞ ወደ ኋላ ዞሮ ማጤንን ማሰላሰልን የሚጋብዝ ነው። ምክንያቱ ደግሞ ወንበር መሪን ወይም ሥልጣንን የሚያሳይ መሆኑንና አገር እንዴት እንደተገነባችና ታንፃ የቆየችባቸው ምስጢሮች ሊያስረዳ ይሞክራል።

በሌላ በኩል ወንበሮቹ ልክ እንደ አፋር ባህላዊ የመረጃ ልውውጥ ዳጉ ውይይት፣ ማዳመጥና መናገር የሚታይባቸው ናቸው።

በወንበሮቹ ላይ የሚቀመጡት ማንም ይሁን ማን ይቀመጥባቸው የምክክርና የንግግር አስፈላጊነትን ለማስረዳት በአንፃሩ ደግሞ የሐሳብ ልውውጥን ለማንፀባረቅ መቅረባቸውንም አመልክተዋል፡፡  

የቀረቡት የሥዕል ሥራዎች ተመልካችን ‹‹ዳጉ›› እንዲያደርጉ ከመጋበዝ ባሻገር ሠዓሊያኑ በሥራቸው ወቅት ከራሳቸውና በአካባቢው ካሉ ጓደኞቻቸው ጋር ያደረጉትንም ያንፀባርቃል፡፡

እንደ ሠዓሊያኑ፣ የቀረቡት ሥራዎች ነገረ ሐሳቦቹ ሲታዩ፣ በማሰብና ሥዕል በመሥራት ሒደት ከሚገኘው ምስል በመነሳት ሐሳብን ዘወር የማድረግ አፍታ፣ የማበጀት፣ ጥያቄያቸውን በማንሳትማንሸራሸርናማፍታታት፣ ከተመልካችና ከሠዓሊዎቹ ጋር በሥዕሉ አማካይነት ማውራት ወይም ‹‹ዳጉ›› መቀመጥን የሚተነትኑ ናቸው።

‹‹ዳጉ›› በጉራምዓይኔ የሥነ ጥበብ ማዕከል ከቀረቡ ትርዒቶች 44ኛው ነው።

ማዕከሉ ከተከፈተ ስምንት ዓመታት ያስቆጠረ ሲሆን፣ 65 ሠዓሊያን ሥራዎቻቸውን አቅርበውበታል።

ማዕከሉ የውይይት መድረኮች የሚዘጋጁበት ሲሆን፣ ምድር ቤቱ ደግሞ ሠዓሊያን የሚሠሩበትና የሚኖሩበት ስቱዲዮ ጭምር በመሆን አገልግሎት ይሰጣል።

ከእነዚህ ሠዓሊያን መካከል ዳንኤል እና ለይኩን ይገኙበታል፡፡ ዓውደ ርዕዩ ከሁለቱ ሠዓሊያን ውይይት ከራስ ጋር መነጋገርን ከማንፀባረቅ በተጨማሪ የንግግር፣ የውይይት የምልልስና የሐሳብ ልውውጥ ኃያልነትን አጉልቶ አሳይቷል።

ሥራዎች በቁጥር 50 የሚደርሱ ሲሆን፣ ዋጋቸው ከፍተኛው 107,000 ብር እ ዝቅተኛው ደግሞ 16,000 ብር ሆነው ለሽያጭ ቀርበዋል።

ሁለት አሠርታት የዘለቀው የዳንኤልና ለይኩን አጋርነት ለሁለተኛ ጊዜ ካቀረቡት ከዚህ ዓውደ ርዕይ ሌላ ሦስተኛውን ሥራቸውን በቅርቡ በፈንድቃ ባህል ማዕከል ለማቅረብ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ነግረውናል።

‹‹ዳጉ›› የሥዕል ዓውደ ርዕይ ለአንድ ወር የሚቆይ ሲሆን፣ በሥራዎቻቸው ላይ ሥነ ጥበባዊ ውይይትም ይደረጋል ተብሏል።

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...