ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ፣ የዘንድሮውን የጥምቀት በዓል በማስመልከት ካስተላለፉት መልዕክት የተገኘ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው መንደርደርያ ላይም ፈጣሪ ለሰው ልጅ ያለውን ፍቅር ካሳየባቸው ታሪኮች አንዱ በዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ወንዝ በተጠመቀ ጊዜ ነው ካሉ በኋላ፣ በዚህ ጊዜ ሦስት አስደናቂ ነገሮችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተግባር ማሳየቱን እነርሱም ፍቅሩን፣ ትኅትናውንና ክብሩን መሆኑን አውስተዋል።