Thursday, February 29, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምሱዳናውያን ችግራቸውን ያለማንም ጣልቃ ገብነት በውይይት  እንዲፈቱ ግብፅ ጥሪ አቀረበች

ሱዳናውያን ችግራቸውን ያለማንም ጣልቃ ገብነት በውይይት  እንዲፈቱ ግብፅ ጥሪ አቀረበች

ቀን:

የግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ሱዳንን ከገባችበት ቀውስ ለማውጣት የሱዳን ባለሥልጣናት ያለማንም ጣልቃገብነት ውይይት ማድረግ እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡ ሱዳንን ከገባችበት ቀውስ ለማውጣትም ውይይት ያስፈልጋል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዘ ኢስት አፍሪካን እንደዘገበው፣ ፕሬዚዳንት አልሲሲ ባለፈው ሳምንት በግብፅ ከተካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ፎረም ጎን ለጎን በነበረ ውይይት፣ ግብፅ በሱዳን ጉዳይ ጣልቃ ላለመግባት መርጣለች ብለዋል፡፡

በጎረቤት ሱዳን የፖለቲካ ብጥብጥ ግብፅ ጣልቃ አትገባም ያሉት አልሲሲ፣ ሁሉም ወገኖች ችግሮቻቸው ላይ ለመምክር የሚያደርጉትን ጥረት እንደምትደግፍ አስታውቀዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

‹‹እኛ በሌሎች አገሮች የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ላለመግባት ፖሊሲ አለን፡፡ በሱዳን አሁን ለተከሰተው ፖለቲካዊ ቀውስም መፍትሔው ውይይት ብቻ ነው፤›› ብለዋል፡፡

ዘንድሮ ግብፅ ያስተናገደችውንና በየዓመቱ የሚካሄደውን የዓለም ወጣቶች ፎረም የከፈቱት አልሲሲ፣ ብዝኃነትን መቀበል፣ በልማት ጉዳዮች መወያየትና በቀጣናው ያለው ብጥብጥ በሚያከትምበት ዙሪያ ሐሳብ ሰንዝረዋል፡፡

በግብፅ እ.ኤ.አ. በ2014 የነበረውን የፖለቲካ ቀውስ ምስክር ሆነው ያዩት እኝህ ሰው፣ ግብፅ በሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት የሚመራውን የሽግግር ሒደትና ወደፊት ሱዳናውያን በመረጡት እንዲመሩ ካውንስሉ የሚከተለውን መንገድ ትደግፋለች ብለዋል፡፡

እ.ኤ.አ. በ2019 ሚያዝያ ላይ አገሪቷን ለሦስት አሥር የመሩትን ኦማር አል በሽር ከሥልጣን ያወረደው አብዮት፣ አሁን ላይም ሱዳንን ወደ ዴሞክራሲያዊ ሽግግር ለማምጣት ትግል ላይ ነው፡፡ የባለሙያዎችና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችም በየቀኑ ተቃውሞ እየወጡ ይገኛሉ፡፡

በሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሥር የሚገኘው የሱዳን መከላከያ በ2019 የሥልጣን መጋራት ስምምነት ቢያደርግም፣ በ2021 ላይ የሽግግር መንግሥቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ላይ መፈንቅለ መንግሥት ካደረገ በኋላ ሱዳን ለፖለቲካዊ፣ ለማኅበራዊና ለኢኮኖሚያዊ ቀውስ ተጋልጣለች፡፡

መፈንቅለ መንግሥት የተካሄደባቸው ሃምዶክ ከመከላከያው ጋር ተደራድረው ከወር የቁም እስር በኋላ ወደ ሥልጣን ቢመጡም፣ በአገሪቱ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ምክንያት ከሥልጣን ለቀዋል፡፡

መፈንቅለ መንግሥቱ ከተካሄደ ከሁለት ወራት በፊት ጀምሮ ሱዳናውያን የጎዳና  ተቃውሞ እያሰሙ ይገኛሉ፡፡ በዚህም ከፀጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት                   ከ60 በላይ ሰዎች መገደላቸውን  ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡

እንደ አልሲሲ፣ በሱዳን እየተከሰተ ያለው ቀውስ በሙሉ ከውይይት ማነስና ስምምነት ላይ ካለመድረስ የመነጨ ነው፡፡ ይህም አገሪቷን በእጅጉ ጎድቷታል፡፡

‹‹ውይይትና ዕርቅ ካለመረጋጋት በጣም የተሻሉ ናቸው፡፡ ምክንያቱም ተቃውሞ ይቀጥላል የአሁኗና የወደፊቷ ሱዳንም ያጣች ትሆናለች›› ብለዋል፡፡

ግብፅ በሱዳን ብቻ ሳይሆን በቀጣናው በሊቢያ፣ በደቡብ ሱዳንና በየመን መረጋጋት እንዲሰፍን ትሠራለችም ብለዋል፡፡

የሱዳን ፖለቲከኞችና ምሁራን ባለፈው ሳምንት መጀመርያ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አማካይነት ውይይት መጀመራቸው ይታወሳል፡፡

ሱዳን የገጠማትን የፖለቲካ ቀውስ በውይይት ለመቀልበስ ባለፈው ሳምንት ካርቱም የገቡት የተመድ ልዩ መልዕክተኛ ቮልከር ፐርትስ፣ ውይይቱ በተናጠል ውይይት ተጀምሮ በቀጣይ በአገሪቱ የሚገኙ የተለያዩ አካላት ወደ ስምምነት የሚወስዳቸውን ውይይት የሚያደርጉበት እንደነበር መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

ጥቃትን ይቀንሳል፣ በተለያዩ አካላት መካከል መተማመንን ይገነባል ተብሎ የታመነበትን ውይይት አስመልክተው፣ ከወታደራዊ ክፍሉ በኩል ምንም ተቃውሞ እንዳልገጠማቸው፣ ነገር ግን በሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች በኩል ተቃውሞ እንዳለ ጠቁመውም ነበር፡፡

በሱዳን ታዋቂው የዴሞክራሲ አቀንቃኝ የነፃነትና የለውጥ ኃይሎች (ፎርስስ ፎር ፍሪደም ኤንድ ቼንጅ) ቃል አቀባዩ ጃዕፈር ሐሰን በወቅቱ በተመድ ኢንሺየቲቭ ዙሪያ ዝርዝር መረጃ እንዳላገኙ ተናግረው የነበረ ሲሆን፣ እሑድ ጥር 8 ቀን 2014 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ በተመድ የቀረበውን የውይይት መድረክ መቀበላቸውን አስታውቀል፡፡

ኦማር አል በሽርን ከሥልጣን ለማውረድ ግንባር ቀደም ሚና የነበረው የሱዳን የባለሙያዎች ማኅበር (ፕሮፌሽናል አሶሲየሽን) ተመድ ያመቻቸውን ውይይት ለኅትመት እስከገባንበት እስከ ጥር 10 ቀን 2014 ዓ.ም. እንዳልተቀበለው ታውቋል፡፡

(ጥንቅር በምሕረት ሞገስ)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...