Thursday, July 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትለአፍሪካ ዋንጫ የተቋረጠው ፕሪሚየር ሊግ ዓርብ በድሬዳዋ ይጀምራል

ለአፍሪካ ዋንጫ የተቋረጠው ፕሪሚየር ሊግ ዓርብ በድሬዳዋ ይጀምራል

ቀን:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊነቱ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዓርብ ጥር 20 ቀን 2014 .. በድሬዳዋ ከተማ እንደሚቀጥል የሊጉ አክሲዮን ማኅበር አስታወቀ፡፡
በድሬዳዋ የሚካሄደው 10 እስከ 15 ሳምንት ያለው የጨዋታ መርሐ ግብር ሲሆን፣ በአሥረኛው ሳምንት ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ከሀዋሳ ከተማ እንዲሁም ሲዳማ ቡና ከባህር ዳር ከተማ ይጫወታሉ፡፡ በማግስቱ ቅዳሜ የሊጉ  መሪ ፋሲል ከተማና በተከታዩ ቅዱስ ጊዮርጊስ መካከል የሚኖረው ጨዋታ ይጠበቃል፡፡ ከሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ቀደም ብሎ የሚጫወቱት ወልቂጤ ከተማና ሀድያ ሆሳዕና ናቸው።

እሑድ ጥር 22 ቀን በአንድ ነጥብ ብቻ በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ የሚገኘው ጅማ አባ ጅፋር ከአዲስ አበባ ከተማ፣ እንዲሁም ሰበታ ከተማ ከአዳማ ከተማ ሲጫወቱ፣ የሳምንቱ የመጨረሻ ጨዋታ ደግሞ ሰኞ ጥር 23 አስተናጋጁ ድሬዳዋ ከተማ ከመከላከያ እንዲሁም ወላይታ ድቻ ከአርባ ምንጭ ከተማ የሚጫወቱ ይሆናል፡፡
ፕሪሚየር ሊጉን የዓምናው አሸናፊ ፋሲል ከተማ 18 ነጥብ ሲመራ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ 17 ነጥብ ይከተለዋል፡፡ ወልቂጤ ከተማ 15 ነጥብ፣ ባህር ዳር ከተማ፣ ሀዋሳ ከተማና ኢትዮጵያ ቡና በጎል ክፍያ ተበላልጠው 14 ነጥብ እስከ ስድስተኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ ይከታተላሉ፡፡

ሰባተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው 13 ነጥብ ወላይታ ድቻ ሲሆን፣ አዳማ ከተማና ሀድያ ሆሳዕና በጎል ክፍያ ተበላልጠው 12 ነጥብ ይከተላሉ፡፡ 10 እስከ 14 ያለውን ደረጃ ይዘው የሚገኙት ቡድኖች ደግሞ ሲዳማ ቡና፣ አርባ ምንጭ ከተማ፣ አዲስ አበባ ከተማ፣ ድሬዳዋ ከተማና መከላከያ ሲሆኑ በጎል ክፍያ ተበላልጠው እኩል 11 ነጥብ ቀጣዩን ጨዋታ ይጠብቃሉ፡፡ በወራጅ ቀጣና ውስጥ የሚገኙት ሰበታ ከተማ በሰባት ነጥብ እና ጅማ አባ ጅፋር በአንድ ነጥብ 15 እና 16 ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...