ዓመታዊው የእግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል ጥቅምት 11 ቀን 2014 ዓ.ም. ከተከበረባቸው ባህረ ጥምቀቶች አንዱ የአዲስ አበባው ጃንሜዳ ነው፡፡ ከዘውዳዊው ሥርዓት ጀምሮ በዓሉ የሚከበርበት ጃንሜዳ ዘንድሮ አዲስ ገጽታን ያላበሰው ባሕረ ጥምቀቱ በዘመናዊ መልኩ መገንባቱ ነው፡፡ የታቦታቱ ማረፊያ የክብር እንግዶች ስፍራ ጭምር ከወትሮው በተለየ መልኩ ተገንብተዋል፡፡ በክብረ በዓሉ በርካታ ምዕመናን፣ ታዳሚዎችና ቱሪስቶች ተገኝተውበታል፡፡ ፎቶዎቹ የበዓላዊ ውሎውን ከፊል ገጽታ ያሳያሉ፡፡