Monday, July 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊአምስት ከተሞችን የሚያሳትፍ የወጣቶች የሥራ ፈጠራ ውድድር ሊካሄድ ነው

አምስት ከተሞችን የሚያሳትፍ የወጣቶች የሥራ ፈጠራ ውድድር ሊካሄድ ነው

ቀን:

ጀነሬሽን አንሊሚትድ የተሰኘ ድርጅት ከኢትዮጵያ የሥራ ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር፣ አምስት ከተሞችን የሚያሳትፍ የሥራ ፈጠራ ውድድር ሊያካሂድ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የወጣቶች የሥራ ፈጠራ ውድድር በአዲስ አበባ፣ በአዳማ፣ በባህር ዳር፣ በሐዋሳና በጅግጅጋ ከተሞች ውድድሩ እንደሚደረግ ድርጅቱ ማክሰኞ ጥር 17 ቀን 2014 ዓ.ም. በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግሯል፡፡

የወጣቶች የሥራ ፈጠራ ውድድር የክህሎት ማዳበሪያ፣ የሥልጠና ጊዜያት ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የቅርብ ክትትል እንደሚደረግለትና በስምንት ሳምንታት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ፣ የጀነሬሽን አንሊሚትድ ድርጅት የቴክኒክ ዳይሬክተር አቶ ሚካኤል አዲሱ ተናግረዋል፡፡

ዳይሬክተሩ እንደተናገሩት፣ ውድድሩ ኢትዮጵያዊ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ዘላቂ የልማት ግቦች (SDGS) የሚኖራቸውን ስኬታማነት የሚያሰፉና መፍትሔ አምጪ ሐሳቦች ላይ ዕድል እንዲያገኙ እንደሚረዳ ጠቁመዋል፡፡

የሥራ ፈጠራዎችን ወደ እውነታ ለመቀየር ክህሎታቸውን የሚያዳብሩበት፣ የቅርብ ድጋፍና ክትትል የሚያገኙበት፣ ሐሳባቸውን ወደ ተግባር ለመቀየር የሚያስችላቸውን መነሻ ገንዘብ እንደሚመደብላቸው ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

የመጀመርያው ዙር ውድድር በአምስት ከተሞች ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን፣ የውድድሩ ሁለት አሸናፊ ቡድኖች በዓለም አቀፍ የወጣቶች ውድድር የመሳተፍ ዕድል ይኖራቸዋል ተብሏል፡፡

የውድድሩ ማመልከቻ መቀበያ ከጥር 17 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ሳምንት ክፍት መሆኑንና የካቲት 1 ቀን 2014 ዓ.ም. እንደሚዘጋ ተገልጿል፡፡ ለውድድሩ ካመለከቱት ውስጥ የሚመረጡ አሥር ስኬታማ ቡድኖች በቢሾፍቱ ከተማ በሚደረገው የክህሎት ማዳበሪያ፣ የንድፍ ዓውደ ጥናት ላይ እንዲሳተፉ ይደረጋል ተብሏል፡፡

የሚቀርቡ ሐሳቦች ማኅበራዊ ችግሮችን በቀላሉ የሚፈቱ ሊሆኑ እንደሚገባ፣ ከሦስት እስከ አምስት ወጣቶች አንድ ላይ መሆን እንዳለባቸው፣ ከ18 እስከ 29 የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች በውድድሩ መሳተፍ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

የጀነሬሽን አንሊሚትድ ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ሚስ ኢቭ ኤስ ዋንጃለ እንደተናገሩት፣ ተቋማቸው በመንግሥት፣ በግል አካላትና በወጣቶች ቅንጅት የሚንቀሳቀስ ዓለም አቀፍ ጥምረት ነው፡፡

ጥምረቱ በዓለም 1.8 ቢሊዮን የሚሆኑ ወጣቶች የፈጠራ ሥራዎች የሚያዳብሩበት ክህሎታቸውን በመገንባት፣ ከተለያዩ የሥራ ዕድሎች ጋር በማገናኘት ሥራ ፈጣሪ እንዲሆኑ ማድረግ ትልቁ ዕቅዱ መሆኑን ሚስ ኢቭ ተናግረዋል፡፡

የተለያዩ የንግድ ሥራ ሐሳብ ላላቸው ወጣቶች ከውድድሩ በኋላ ሥራ ማስጀመሪያ የገንዘብ ድጋፍ እስከ 100,000 ብር ይሰጣቸዋል ተብሏል፡፡

ውድድሩ በአለም አቀፍ ደረጃ መሆኑን፣ 35 በላይ በሚሆኑ አገሮች እንደሚካሄድ፣ በኢትዮጵያ ወጣት ፈጣሪዎች ዘላቂ የልማት ግቦችን ስኬታማነት የሚያፋጥኑሳቦችን ወደ ተግባር መቀየር የሚያስችላቸው ነው ተብሏል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሕፃናት ፈንድ፣ የተባበሩት መንግሥታት  ድርጅት የልማት ፕሮግራም፣ዓለም የሠራተኞች ድርጅት፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትነ ሕዝብ ፈንድ፣ እንዲሁም የአገር ውስጥ አስተባባሪ ቢሮ ለውድድሩ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

አሸናፊዎች የሥራ ማስጀመሪያ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚደረግላቸውና በዓለም አቀፍ የወጣቶች ውድድር ላይ እንደሚሳተፉም ተነግሯል። አመልካቾች ከአዲስ አበባ፣አዳማ፣ባህር ዳር፣ ከሐዋሳናጅግጅጋ ከተሞች መሆን እንዳለባቸውም ተነግሯል፡፡

የውድድሩ ለሁለት ሳምንታት የሚቆይ መሆኑንና https://cutt.ly/zlACXul በኩል ወይም በከተሞቻቸው ባሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አደረጃጀት ማመልከት እንደሚቻል ተገልጿል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሚዲያው በሕዝብ የህሊና ችሎት ከተዳኘ በቂ ነው!

መሰንበቻውን ድንገት ሳይታሰብ ያለ ማስጠንቀቂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

የባህር በር ጉዳይ

በታምሩ ወንድም አገኘሁ ድሮ ድሮ ገና ልጅ ሆኜ ፊደል እንደቆጠርኩ...

አገሩ ፖለቲካዊ ስክነትና መደማማጥ ያስፈልገዋል

በንጉሥ ወዳጀነው    ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ቤት ነች፡፡ ‹‹ጥያቄዬ ተመለሰልኝ››፣...

የመንግሥት የሰብዓዊ መብት ተቋም ለምን የመንግሥት ሚዲያን ማስተማር አቃተው

በገነት ዓለሙ የአገራችን የ2016 የበጀት ዓመት መሰናበቻና የአዲሱ የ2017 በጀት...