ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከአንድ ሳምንት በፊት ሙሉ የጀነራልነት ማዕረግ የተሰጣቸው ጀነራል ባጫ ደበሌንና ስለሽ በቀለ(ዶ/ር)ን ጨምሮ 16 በተለያየ ስልጣን ላይ የነበሩ ግለሰቦችን ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አድርገው ሾሙ።
ፕሬዚደንቷ በሰጡት ሹመት አቶ ተፈራ ደርበው፣አቶ ደሴ ዳልኬ፣ዶክተር ስለሺ በቀለ፣ጄኔራል ባጫ ደበሌ፣ጄኔራል ሀሰን ኢበራሂም፣ ወ/ሮ ሽትዬ ምናለ፣ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ፣አቶ ረሻድ መሀመድ፣ አምባሳደር ጀማል በከር፣አቶ ፈይሰል ኦሊይ፣አቶ ኢሳያስ ጎታ፣አቶ ፀጋአብ ክበበው፣ አቶ ጣፋ ቱሉ፣ገነት ተሾመ(ዶ/ር)፣አቶ ዳባ ደበሌና አቶ ፍቃዱ በየነ ባሉሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው ተሾመዋል።
አቶ አሳየ አለማየሁ፣አቶ ኃይላይ ብርሃነ አቶ አወል ወግሪስ፣ወ/ሮ ብዙነሽ መሠረት፣አቶ አንተነህ ታሪኩ፣አቶ አክሊሉ ከበደ፣አቶ ሰይድ መሐመድ፣አቶ ዮሴፍ ካሳዬ፣አቶ ዘላለም ብርሃን፣ወ/ሮ ፍርቱና ዲባኮና አቶ ወርቃለማሁ ደሰታ አምባሳደር ሆነው መሾማቸውን የፕሬዝዳንት ፅሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡
- Advertisement -
- Advertisement -