Friday, December 1, 2023

በሚዲያ ሪፎርም ውስጥ የነገሠው የጋዜጠኞች እስር

- Advertisement -spot_img

በብዛት የተነበቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (/) 2010 ዓ.ም. ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በሚመሩት ማኅበረሰብ ላይ የተስፋ ስንቅ ሊፈጥሩ የቻሉት፣ ከእሳቸው በፊት በሥልጣን ላይ የነበረው የመንግሥት አካል ያወጣቸው አፋኝጎችን በማሻሻል ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን በአገሪቱ ለመትከል በገቡት ቃልና ባሳዩት ቁርጠኝነት ነው።

ቃላቸውን ወደ ተግባር ለመለወጥም ቅድሚያ ከሰጧቸው ጉዳዮች አንዱ የመገናኛ ብዙኃን ዘርፉን አላንቀሳቅስ ያሉና ጋዜጠኞችን ማሳደጃ የነበሩጎችን በማሻሻል፣ ዘርፉ በአገሪቱ የዴሞክራሲ ግንባታ ውስጥ መጫወት የሚገባውን ሚና በነፃነትና በኃላፊነት እንዲወጣ የሚችልበት ሜዳ ማመቻቸት ነው። 

ይህንን ወደ ተግባር በመለወጥ ረገድ ጠቅላይ ሚኒስትሩና መንግሥታቸው የተጓዙበት ፍጥነት ቀርፋፋ ቢሆንምበሥልጣን በቆዩባቸው ዓመታት ግን ከዚህ አኳያ ምንም አላከናወኑም ማለት አይቻልም። 

ይህንን ለማለት የሚያስደፍረውም ቢያንስ የተሻሻለ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ እንዲወጣ ያደረጉ ሲሆንየቀድሞው የፀረ ሽብር አዋጅ ላይ ጋዜጠኞችን ለማሰርና ለማሳደድ፣ በውጤቱም የሚዲያ ዘርፉን ለማሰናከል ጥቅም ላይ ይውሉ የነበሩ ድንጋጌዎች ከዚህ አዋጅ እንዲወጡ ተደርጓል። 

የሚዲያ ዘርፉ ሪፎርም በአዝጋሚደት ውስጥ ጊዜውን ሲፈጅ የአገሪቱን የዴሞክራሲ ግንባታ ጅምርደት ረዥም ርቀት ወደኋላ ሊወስድ እንደሚችል የሚነገርለት፣ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በጥቅምት ወር 2013 ዓ.ም. ተቀሰቀሰ፡፡

በትግራይ ክልል ከከተመው የሕወሓት ኃይል ጋር የተጀመረው ይህ ውጊያ ውስብስብ የሆኑ ማኅበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ቀውሶችን ያስከተለና እያስከተለ ሲሆንይህ ውጊያ የወለዳቸው ፖለቲካዊ ቀውሶች ካረፈባቸው ዘርፎችና ሙያዎች መካከል ደግሞ የሚዲያ ዘርፉና ጋዜጠኝነት ነው። 

ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ 14 በላይ ጋዜጠኞች ለእስር ሲዳረጉ፣ በርካታ የሚዲያ ተቋማትም በዘርፉ መቀጠል እንዳይችሉ ተገደው ለመዘጋት በቅተዋል።

በጋዜጠኞች ላይ የተሰነዘረው እስርና እንግልት ከገጠማቸው በርካታ የሚዲያ ባለሙያዎች መካከል አንዱ የሆነውና ለረዥም ዓመታት በጋዜጠኝነት ያገለገለው ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው፣ ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ወደ ሥልጣን ሲመጡ በርካታ ተስፋ ነበር፡፡ አሁን ግን ጋዜጠኞች ይታሰሩና የት እንዳሉ አይታወቅም፤›› ሲል ሁኔታውን ይገልጻል፡፡ 

‹‹ፍርድ ቤት ሳልቀርብ 42 ቀናት ታስሬ ነበር፤›› የሚለው ጋዜጠኛ በቃሉ፣ ባለፈው አንድ ዓመትና በላይ በሚዲያ ባለሙያዎች ላይ የተፈጠረውን፣ ‹‹ጋዜጠኝነትን ወደኋላ የመለሰ ብቻ ሳይሆን በፍጥነት የተፈጠፈጥንበት ነው፤›› ሲል ይገልጸዋል።

እሱ ከእስር ከተፈታ በኋላ ይሠራበት የነበረውን የሚዲያ ተቋምለቤቶቹ ዳግም ወደ እንቅስቃሴ ማስገባት ባለመቻላቸው ሳቢያ፣ በአሁኑ ወቅት የራሱን የጋዜጠኝነት ሚና ለመቀጠል አዲስ የሚዲያ ተቋም መሥርቶ እንቅስቃሴ መጀመሩን ይናገራል፡፡ 

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በታኅሳስ ወር 2014 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫም ይህንኑ ሁኔታ ገልጿል። 

በእስር ላይ የሚገኙ የሚዲያ ባለሙያዎችን በተመለከተ ከመንግሥት አካላት ጋር በመነጋገር ቅሬታውንናጋቱን በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል።

የታሰሩት ጋዜጠኞች ለእስር የዳረጋቸውን ምክንያት ለማወቅ ከመቸገራቸውም በላይ፣ ፍርድ ቤት ቀርበው የዋስትና መብት የተፈቀደላቸው ጋዜጠኞችም መብታቸው ሳይከበር በሕግ ባላተፈቀደ እስር ሲማቅቁ ከርመዋል። 

ይህንንም እውነታ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በታኅሳስ ወር መግለጫው አመልክቷል። ‹‹በተለይም ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ በፖሊስ ከተያዘበት ከታኅሳስ 1 ቀን 2014 .. ጀምሮ፣ እንዲሁም  ከጥቅምት 16 ቀን 2014 .. ጀምሮ በእስር የቆየው ጋዜጠኛ ክብሮም ወርቁ በኅዳር 9 ቀን 2014 .. በፍርድ ቤት የዋስትና መብት ከተፈቀደላቸው ጊዜ ጀምሮ ኢሰመኮ ይህን መግለጫ እስካወጣበት ጊዜ ድረስ፣ የተያዙበት ቦታ ለቤተሰቦቻቸው ባለመነገሩ የቤተሰብ ጥየቃ መብታቸው ያልተከበረላቸው ከመሆኑም በላይ፣ ያሉበት ሁኔታ አለመታወቁ ኮሚሽኑን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያሳስበው ነው፤›› ብሏል። 

አንዳንድ የመንግሥት አመራሮች ጋዜጠኞቹ የታሰሩት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመተላለፍ እንደሆነ ቢገልጹም፣ ኮሚሽኑ ግን በአስቸኳይ ሁኔታም ውስጥ ቢሆን ታሳሪዎች ያሉበት ሁኔታ ሊታወቅ፣ በቤተሰብና በሕግ አማካሪ የመጎብኘት መብቶቻቸው ሊጣሱ እንደማይገባ ተከራክሯል። 

የአስቸኳይ አዋጅ የሰብዓዊ መብቶችን መርሆዎች ባከበረ መንገድ መተግበር እንዳለበትም በተደጋጋሚ አሳስቧል።

መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማንሳት ባቀደበት ወቅት  የት እንደታሰሩ የማይታወቁትና የቤተሰቦቻቸውን ጉብኝት የተነፈጉ የተወሰኑ ጋዜጠኞች፣ ከሰሞኑ በመታወቂያ ዋስ ብቻ እየተፈቱ ቤተሰቦቻቸውን ተቀላቅለዋል። ይሁን እንጂ አሁንም ቁጥራቸው ቀላል ያልሆነ ጋዜጠኞች ጥፋታቸውን ሳያውቁና ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በእስር ቤቶች እየማቀቁ ናቸው፡፡ ከነዚህም መካከል ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ተጠቃሽ ነው። 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ከፈነጠቁት የሚዲያ ዘርፍ ሪፎርም ተስፋ፣ ለዘርፉ ማበብና መጎልበት ሚና እንደሚኖራቸው የገመቱ ጋዜጠኞች በተቃራኒው በእስር ቤት ጨለማ ውስጥ ለወራት ማቀዋልእየማቀቁም ይገኛሉ። 

ከእስር የተለቀቁ አንዳንድ ጋዜጠኞችም በሚዲያ ሪፎርሙ ላይ ተስፋቸውን አጥተዋል። አንዳንዶቹ ጋዜጠኞች ሪፎርሙን እንዲመራና እንዲተገብር በአዋጅ የተቋቋመው የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዘርፉን ከመደገፍና ሪፎርሙን ከመምራት በተቃራኒ ተልዕኮ ተሠልፎ፣ በእስር እንዲቆዩ የሚጠቅም መረጃ ላሰራቸው አካል ሲያቀብልይተው ማዘናቸውን ይገለጻሉ። 

በሚዲያ ሪፎርሙ ትግበራና በጋዜጠኞች እስር ያለውን ተቃርኖ አስመልክቶ የሚናገረው ጋዜጠኛ በቃሉ፣ ‹‹ሪፎርሙ ከንቱ ሆኗል›› በማለት ይናገራል።

‹‹በሚዲያ ሪፎርሙ የመጣው የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ተግባራዊ ሆኖ ቢሆን አንድ ጋዜጤኛ ላይ ቅሬታ ሲቀርብና ክስ ሲመሠረትበት በሕጉ መሠረት ይተገበር ነበር። ስለዚህ ለሚዲያ ነፃነት ተብሎ የተደረገ ማሻሻያ አይደለም ማለት ነው፤›› ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡ 

በአዲሱ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ የሚዲያ ዘርፉ ራሱን በራሱ የሚቆጣጠርበት የሚዲያ ምክር ቤት ተመሥርቶ ራሱን እንደሚያስተዳድር ቢገለጽም፣ ይህንን ማየት እንዳልተቻለ ይናገራል። ‹‹በአጠቃላይ ገለልተኛ የሆነ አካል አይደለም የሚዲያውን ጉዳይ የሚያየው፤›› ብሏል፡፡

የሚዲያ ሪፎርሙን የሚያከናውነው ገለልተኛ የባለሙያዎች ቡድን ሰብሳቢና የሚዲያ ባለሙያው አቶ ሰለሞን ጎሹ፣ በሚዲያ ተቋም የሕግ ጥሰት ተፈጽሟል ከተባለ በቀጥታ ወደ ክስ የሚሄድበት አሠራር ቢኖርምበሪፎርሙ ግን ትኩረት የተሰጠው በአስተዳደራዊርዓት እንዲታይ መሆኑን ይገልጻል። 

ይህም ማለት በሚዲያ የተፈጸመ ስህተትን ወይም ጥፋትን የቃል ማስጠንቀቂያ ወይም የደብዳቤ ማስጠንቀቂያ፣ እንዲሁም በምክክር ጥፋቱ እንዳይደገም ማድረግ የሚቻልበት አስተዳደራዊ አሠራር እንደሆነ አስረድቷል።

ነገር ግን የሕግ ማዕቀፉ ብቻ መቀመጡ ዋጋ እንደሌለው የሚናገረው ባለሙያው፣ ይህንን ወሳኝርዓት ለማስጀመር የሚቻለው በአዲሱ አዋጅ እንዲቋቋም የተባለው ገለልተኛ ቦርድ ተቋቁሞ ወደ ትግበራ ሲገባ እንደሆነ ገልጿል።

‹‹ይህ ተከናውኖ ቢሆን ኖሮ ቦርዱ ገለልተኛ በመሆኑ ሚዲያው ላይ የሚታዩ ክፍተቶች ካሉ ወደ ክስ ከመሄዱ በፊት፣ ገንቢ በሆነ መንገድ ስህተቶቹ እንዲታረሙ ማድረግ ይቻል ነበር፤›› ብሏል።

የሚዳያ ባለሥልጣኑ የራሱ የሚዲያ ክትትል (ሞኒተሪንግ) ክፍል እንዳለው፣ በዚህ ክፍል አማካይነትም የሚዲያ ተቋም ይዘቶችን ባለማቋረጥ በመከታተል የሕግ ጥሰት አለው የለውም የሚለውን እንደሚተነትን ያስረዳል፡፡

በተጨማሪም ባለሥልጣኑ በማንኛውም የመንግሥት አካል ሲጠየቅም ሙያዊ ትንታኔ የመስጠት ኃላፊነት እንዳለበት ተናግሯል።

በቅርቡ የታሰሩ ጋዜጠኞች ጉዳይ ለብቻው ተነጥሎ ከታየ ከባለሥልጣኑ ጋር በቀጥታ ግንኙነት አለው ብለው እንደማያምን የሚናገረው አቶ ሰለሞን፣ እስር ወይም ክስ የፖሊስና የዓቃቤ ሕግ ወይም የፍትሕ ሚኒስቴር እንደሆነ ያስረዳል።

ባለሥልጣኑ የሚዲያ ሞኒተሪንግ (ክትትል) ሥ ስለሚሠራ የታሰሩት ጋዜጠኞችን በተመለከተ የተጠየቀውን መረጃ ወይም አስተያየት የመስጠት ግዴታ እንዳለበት፣ ይህንን በማድረጉም በሰዎች ሊጠረጠር ይችላል ነገር ግን ባለሥልጣኑ የማሰር ሥልጣን የለውም ብሏል።

ነገር ግን የባለሥልጣኑ አመራሮች ይህንን ሲያደርጉም ሆነ ዘርፉን ሲመሩ ከፖለቲካ ነፃ ሆነው መሆን እንደሚገባ ጠቁሟል።

‹‹ነገር ግን አንዳንድ የባለሥልጣኑ አመራሮች በሚሰጡት አስተያየት፣ እንዲያውም ከእስሩ ጀርባ አሉበት ብለህ ልትጠረጥር ትችላለህ። ከመጠርጠር ውጪ ግን እስሩን የፈጸመው ከባለሥልጣኑ ውጪ ያለ አካል ነው፣ ባለሥልጣኑም የማሰር ሥልጣን የለውም፤›› ብሏል። 

አንድ ጋዜጠኛ ምን ሲያደርግ ነው የሚከሰሰው ወይም የሚቀጣው የሚለው በተሻሻለው አዋጅ ላይ በግልጽ መደንገጉን አቶ ሰለሞን ያስረዳል፡፡

‹‹አሁን አብዛኞቹ ጋዜጠኞች የታሰሩበት ምክንያት ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተገናኘ ነው ሲባል ነው የሚሰማው። አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ደግሞ ለብሔራዊ ፀጥታና ደህንነት ያደላ ነው። በኢትዮጵያ ደግሞ የብሔራዊ ፀጥታና ደኅንነት ትርጓሜ አከራካሪና አሻሚ ጉዳይ ነው፤›› ብሏል።

ችግሩን አሳሳቢ የሚያደርገው ደግሞ በአዲሱ አዋጅ እንዲቋቋም የተባለውን ገለልተኛ ቦርድ በፍጥነት አቋቁሞ ወደ ማስገባት እየተቻለ ይህ መሆን ባለመቻሉ፣ ስህተት የፈጸሙ የሚዲያ ተቋማትና ጋዜጠኞችን ባስቀመጠው በአስተዳደራዊርዓት እንዳይዳኙ ማድረጉን ገልጿል።

በሚዲያ ሪፎርም ላይ የሚኖረው ተፅዕኖ 

የሚዲያ ሪፎርም ሥራው የመጀመሪያው ዓመት ዕቅዶች እንደተጠናቀቁ አሁን ያለው አገራዊ የፖለቲካ ቀውስ መፈጠሩን የሚገልጸው አቶ ሰለሞን፣ ‹‹የሚዲያ ሪፎርምራው ተጀመረ እንጂ አልተጠናቀቀም፤›› ብሏል። 

የመረጃ ነፃነት ሕግን ማፀደቅ፣ የመገናኛ ብዙኃን ፖሊሲ ማስፈጸሚያ ዶክመንት የማስታወቂያ አዋጅ፣ የወንጀል ላይ ያሉ ሚዲያን የሚመለከቱ ድንጋጌዎችን ማሻሻልና ሌሎችራዎች ይቀራሉ ነገር ግን በተፈጠረው አገራዊ ሁኔታራውን መሥራት እንዳልተቻለ ጠቁሟል።

‹‹ማየት ያልቻልነው የሕግ ሪፎርምራውን የሚሠራው ፈቃደኛ የባለሙያዎች ቡድን እንደ መሆኑ መጠን፣ አንዳንዶቹ አገራዊ ሁኔታውን ተከትሎ የወጣው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅና መንግሥት የወሰዳቸው ዕርምጃዎች የመንግሥትን የሚዲያ ረፎርም ፍላጉት እንዲጠራጠሩና ከልቡ አልነበረም እንዲሉ አድርጓቸዋል፤›› ሲልም አክሏል፡፡ 

ከወቅታዊ ሁኔታዎች ጋር በተገናኘ በሚዲያ ተቋማትና ጋዜጠኞች ላይ የተፈጠሩት ነገሮች ቀሪ የሪፎርምራዎችን ለማከናውን እንቅፋት እንደሆኑም በግልጽ አስረድቷል።

‹‹የሪፎርምራው የመጀመሪያው ዓመት እንቅስቃሴ ላይ በርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት የሚዲያ ሪፎርሙን የሚያግዙ ባለሙያዎችን በመቅጠር፣ የጥናት ሥራዎችን በማገዝና በመሳሰሉት ሰፊ ድጋፍ ያደርጉ ነበር፡፡ አሁን ግን ጥርጣሬ አላቸው። አንዳንዶቹ እንዲያውም ትርጉም አጥቷል እስከ ማለት ደርሰዋል፤›› ብሏል።

የሚዲያ ሪፎርሙ የተጀመሪው ሰፊ የሆነ የማኅበረሰብና የሲቪክ ተቋማት ተሳትፎን ይዞ እንደነበረ፣ ነገር ግን ወቅታዊ ሁኔታዎችን ምክንያት በማድረግ ከመንግሥት ወገን በመጡ የተለያዩ ዕርምጃዎች ሪፎርሙ የሚጠበቀውን ውጤት ማግኘት እንዳልተቻለም አስረድቷል።

ጋዜጠኛ በቃሉ በበኩሉ በቀጣይ የሚዲያ ዘርፉ ይሻሻላል የሚል ተስፋ እንደሌለው ይገልጻል፡፡ 

በነባሩ ሚዲያ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ስለተደረገም አዲስ የሚዲያ ተቋም ከመጣ ሊሳካለት ይችል ይሆናል እንጂ፣ ነባሮቹ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ለመቀጠል ከባድ እንደሚሆንባቸው ተናግሯል።

‹‹የሚዲያ ዘርፉ የአገሪቱ የፖለቲካ ምስቅልቅል አካል ስለሆነ ምናልባት በአገራዊ ውይይቶች ሊሻሻል ከቻለ፣ ከሰባትናስምንት ዓመታት በኋላ ሊሻሻል ይችላል፤›› ሲል አስተያየቱን ገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ትኩስ ጽሑፎች

ተዛማጅ ጽሑፎች

- Advertisement -
- Advertisement -