Saturday, June 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅተጓዳኝ ፍለጋ

ተጓዳኝ ፍለጋ

ቀን:

የወፎች ዝማሬ በድንገት ትኩረትህን ስቦት ያውቃል? የተለያዩ ዜማዎችን በማሰማት ችሎታቸው አልተደነቅህም? ይሁን እንጂ ይህን ሁሉ ዝማሬ የሚያሰሙት አንተን ለማዝናናት ብለው እንዳልሆነ ታውቃለህ? መዝሙሮቻቸው አስፈላጊ የሆኑ መልእክቶችን የሚያስተላልፉባቸው ዘዴዎች ናቸው። ክልላቸውን ለማስከበር ሲሉ ዝማሬ የሚያሰሙበት ጊዜ ቢኖሩም አብዛኛውን ጊዜ ግን የሚዘምሩት ተጓዳኝ ለመሳብ ሲሉ ነው። ኒው ቡክ ኦቭ ኖውሌጅ እንደሚለው ወንዱና ሴቷ አንዴ ከተገናኙ በኋላየመዝሙሩ መጠን እስከ 90 በመቶ ድረስ ይቀንሳል።

ይሁን እንጂ ተጓዳኝ ለመማረክ ጥሩ መዝሙር ብቻ በቂ የማይሆንበት ጊዜ አለ። አንዳንድ እንስት ወፎች በተባዕቱ ከመሸነፋቸው በፊትጥሎሽእንዲጣልላቸው ይፈልጋሉ። ስለዚህ ዊቨርበርድ የተባለው ወፍ በጥያቄው ከመግፋቱ በፊት ጎጆ የመሥራት ችሎታውን ማስመስከር ይኖርበታል። ሌሎች ተባዕት የአዕዋፍ ዝርያዎች ደግሞ እንስቷን ቃል በቃል በመቀለብ ለቤተሰባቸው መተዳደሪያ የማቅረብ ችሎታቸውን ማስመስከር ይኖርባቸዋል።

እንስሳት ሐሳብ ለሐሳብ የሚግባቡባቸው መንገዶች አካላዊ ፍላጎቶቻቸውን ከማሟላት አልፈው ብዙ ጠብ እንዳይፈጠር በማድረግ በዱር ውስጥ ሰላም እንዲሰፍን ያደርጋሉ። በእንስሳት የሐሳብ ልውውጥ ላይ የሚደረገው ምርምር እየቀጠለ በሄደ መጠን ስለዱር አራዊት ጭውውትየምናውቀው ብዙ ነገር ይኖረናል።

– ዘ ኒው ቡክ ኦቭ ኖውሌጅ

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አያሌ የውኃ “ጠርሙሶች”ን በጫንቃ

መሰንበቻውን በአይቮሪ ኮስት መዲና አቢጃን የምትኖር አንዲት ሴት፣ በሚደንቅ...

ወልቃይትን ማዕከል ያደረገው የምዕራባዊያን ጫና

በትግራይ ክልል የተከሰተው የዕርዳታ እህል ዘረፋ የዓለም አቀፍ ተቋማት...

ከቀጣዩ ዓመት በጀት ውስጥ 281 ቢሊዮን ብሩ የበጀት ጉደለት ነው ተባለ

ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት...