Sunday, June 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልለቱሪስት መዳረሻነት የታሰበው ኔልሰን ማንዴላ የሠለጠኑበት ማዕከል

ለቱሪስት መዳረሻነት የታሰበው ኔልሰን ማንዴላ የሠለጠኑበት ማዕከል

ቀን:

‹‹የኢትዮጵያ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ የሚሠለጥነው እዚህ ኮልፌ የሚባለው ሠፈር ነው። ወታደራዊ የሳይንስ ጥበብ እንድማር የተመደብኩበትምፍራ እዚህ ነው። እስካሁን ባለኝ ልምድ ጀማሪ ቦክሰኛ ከመሆን ውጪ ስለጦር ሜዳ ፍልሚያ የረባ ዕውቀትም የለኝም። አሠልጣኜ መቶ አለቃ ወንድሙ በፍቃዱ ይባላል። በጣልያን ወረራ ጊዜ የደፈጣ ተዋጊ የነበሩ ልምድ ያላቸው ወታደር ናቸው።

‹‹በአዲስ አበባ መውሰድ የጀመርነው የሥልጠና ፕሮግራም ጥብቅ ነው። ከጠዋቱ 200 ሰዓት እስከ 700 ሰዓት ድረስ ሥልጠና ላይ እንቆያለን። ከዚያ የምሳ ሰዓት ነው። ከዚያ ከሰዓት 800 እስከ 1000 ሰዓት ሥልጠናው ይቀጥላል። 1000 ሰዓት በኋላ እስከ ምሽቱ ድረስ ስለወታደራዊ ሳይንስ የንድፈ ሐሳብ ገለጻ ይደረግልናል። ይህንን ሥልጠና የሚያደርጉልን ኮሎኔል የፖሊስ ረዳት ኮሚሽነር ናቸው። …በሥልጠናው የአውቶማቲክ መሣሪያዎችና የሽጉጥ አጠቃቀምን ተማርኩ።››

እነዚህ ከላይ የተገለጹት አንቀጾች ደቡብ አፍሪካዊው የፀረ አፓርታይድ ቁርጠኛ ታጋይ፣ ከሦስት አሠርታት ግድም የእስር ቆይታ በኋላ የመጀመርያ ጥቁር ፕሬዚዳንት በመሆን አገራቸውን የመሩት ኔልሰን ማንዴላ “Long Walk To Freedom” በተሰኘው ግለ ታሪካቸው ላይ ያሠፈሩት ነው፡፡

‹‹ኢትዮጵያ በእኔ ውስጥ ሁልጊዜ ልዩ ሥፍራ አላት። የአፍሪካዊነት የዘር ሐረግ ግንዴ የተተከለባት አገር ትመስለኛለች፤›› ያሉት ኔልሰን ማንዴላ፣ ፀረ አፓርታይድ ተጋድሏቸውን በነፍጥ ለማጀብ የሚረዳቸውን ወታደራዊ ትምህርትና ሥልጠና ለመቅሰም የቻሉበትን የኢትዮጵያ ቆይታቸውን በመጽሐፋቸው ዘርዝረውታል፡፡

ለቱሪስት መዳረሻነት የታሰበው ኔልሰን ማንዴላ የሠለጠኑበት ማዕከል

 

‹‹መጀመሪያ ኮልፌ ከዚያም ከኮልፌ 50 ማይልስ የምትርቅ ቦታ ከወታደሮቹና ከክብር ዘበኛ አባላት ጋር ሄጄ የዒላማ ተኩስ ተለማመድኩ። የሞርታር ተኩስና እንዲሁም የቦንብ አሠራሮችን፣ ፈንጂዎችን የማክሸፍ ዘዴንም ተማርኩ። አሁን እያደር ወታደር እየሆንኩ ስሄድ ይታወቀኛል። እንደ ወታደር ማሰብ ለመድኩኝ። ወታደር መሆን እንደ ፖለቲከኛ ከማሰብ የሚለይበት የራሱ መንገድ አለው።….››

ይህ በ1954 ዓ.ም. መጀመርያ ኔልሰን ማንዴላ የሠለጠኑበት የቀድሞው የፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ማሠልጠኛ የአሁኑ የኮልፌ ፖሊስ ማሠልጠኛ ማዕከልን የቱሪስት መስህብ ለማድረግ ከቅርብ ወራት ወዲህ በአዲስ አበባ የባህል የኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ (ባኪቱ) የተጀመረው እንቅስቃሴ መልክ መያዝ ጀምሯል፡፡

የአዲስ አበባ ባኪቱ ቢሮ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንደገለጸው፣ ወደ ኢትዮጵያ 1954 ዓ.ም.  መጥተው ወታደራዊ ሥልጠና የወሰዱበት የኮልፌው በአሁኑ አጠራሩ የፖሊስ ሙያ ቴክኒክ ግቢ ውስጥ የሚገኝ ታሪካዊ ቦታ ለውጭ ቱሪስትም ሆነ ለአገር ውስጥ ጎብኚ በሚሆን መልኩ ታሪካዊ ዳራውን ሳይለቅ ለማልማት ስምምነት ላይ ተደርሷል። ስምምነቱን የቢሮ ኃላፊዋ ሒሩት ካሳው (ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ ፖሊሲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ክትል ዋና ኮሚሽነር መስፍን አበበ በጋራ ተፈራርመዋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት እንዳመለከቱት ታሪካዊው ቦታ ሙዚየም መሆኑ፣ የፖሊስ ቀደምት ታሪክ የሚዘከርበትና ኢትዮጵያ በአፍሪካ የነፃነት ታሪክ ትልቅ ድርሻ እንደነበራት ማሳያ ይሆናል፡፡

የባኪቱ ቢሮ ኃላፊዋ በበኩላቸው እንዳስገነዘቡት፣ የቱሪዝም ሀብቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲታወቁ፣ የቱሪስት ፍሰቱንና ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ እንዲጨምር ከማድረጉም በላይ በአፍሪካውያን የነፃነት ትግል ውስጥ የኢትዮጵያን ሚናን አጉልቶ ለማሳየት ይረዳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...