Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልለበዓላት ባህላዊ ክዋኔዎች ቀጣይነት የቆመው የ‹‹ፍለጋ›› ፕሮጀክት

ለበዓላት ባህላዊ ክዋኔዎች ቀጣይነት የቆመው የ‹‹ፍለጋ›› ፕሮጀክት

ቀን:

በወርኃ ጥር የሚውሉትን የጥምቀትና ተያያዥ ክብረ በዓላትን ከሚያደምቁት ውስጥ ባህላዊ ክዋኔዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱና ያሬዳዊ ዝማሬዎቹ እንዳሉ ሆነው ኅብረተሰቡ የከተራ፣ ጥምቀት፣ ቃና ዘገሊላ/ቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓላትን  እንደየአጥቢያው በባህላዊ ክዋኔዎች ያጅባቸዋል፡፡ በጥምቀት ክብረ በዓል ላይ ሃይማኖታዊ ክንውኖቹ እንደነበሩ ቢዘልቁም፣ ባህላዊ ገጽታው በተለይ በዋና ዋና ከተሞች እየተቀዛቀዘ መምጣቱ ይወሳል፡፡

የበዓለ ጥምቀት ባህላዊ ክዋኔዎች እንዳይደበዝዙ ብሎም እንዳይጠፉ  ከትውልድ ወደ ትውልድ ተሸጋግረው እንዲቀጥሉ ለማድረግ ‹‹ፍለጋ›› የተሰኘ ፕሮጀክት ይዞ እየተንቀሳቀሰ ያለው የኢትዮጵያን ባህላዊ ውዝዋዜዎች ለዓለም በማስተዋወቅ የሚታወቀው የባህል ተወዛዋዥ መላኩ በላይ (ፈንድቃ) ነው፡፡

ይኸው ከያኒ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዴሚ ሥር የሚገኘው የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነ ጥበብ ማዕከል ባለፈው ሳምንት ‹‹ጥምቀት፣ ባህልና ኪነት›› በሚል ርዕስ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ስለፍለጋ ፕሮጀክቱ ገለጻ አቅርቦ ነበር፡፡

ከያኒው መላኩ ተወልዶ ያደገው የካ ሚካኤል አካባቢ እንደሆነና አሁን ለደረሰበት ለውዝዋዜ የላቀ ኪነታዊ ደረጃ መንደርደርያው የጥምቀት በዓል ሲከበር ያየውና እየጨፈረ ያደገበት ባህላዊ ክዋኔ መሆኑን ገልጿል፡፡

‹‹በጥምቀት በዓል የሚደረጉ ባህላዊ ውዝዋዜዎች ለአሁን ሥራዬ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርገውልኛል፤›› የሚለው መላኩ፣ በልጅነቱ የየካ ሚካኤል ጥምቀት ወደ ሚከበርበት የባልደራስ ባሕረ ጥምቀት  የዋሻ ተክለ ሃይማኖት ታቦትን አጅበው ሲጓዙ የተለያዩ አካባቢዎችን የጎጃም፣ የጎንደር፣ የወሎ፣ የትግራይ፣ የራያ፣ የምንጃር፣ የኦሮሞና የጉራጌ ጭፈራዎችን አብሮ ይጨፍር እንደነበር ያስታውሳል፡፡

ሃይማኖታዊ ከበራው እንዳለ ሆኖ፣ በየሥፍራው የባህል ጭፈራዎችና የልብስ ፋሽኖች እንደሚታዩ፣ ሁሉም ክብ ክብ ሠርቶ የመጣበትን አካባቢ ባህላዊ ጭፈራዎችን ያሳይ እንደነበር ያስረዳል፡፡

ካዛንቺስ የሚገኘው የፈንድቃ ባህል ማዕከል መሥራቹ መላኩ በላይ፣ የጥምቀት በዓል በድምቀቱና በውበቱ ከሃይማኖታዊ በዓልነት ባሻገር፣ በተለያዩ ብሔረሰቦች ባህላዊና ትውፊታዊ ክዋኔዎች የተዋበ ክብረ በዓል መሆኑን አስታውሷል።

ፍለጋ የተሰኘው ፕሮጀክቱ በባህላዊ ገጽታዎች የሚታጀበውን ክብረ በዓል በተጠናከረ መልኩ በዘላቂነት ለማስኬድ ያለመ መሆኑን፣ የተለያዩ ብሔረሰቦች የባህል ጨዋታዎች እንዲካተቱበት ለማድረግ መንቀሳቀሱን፣ የጋሞና የዳውሮ ባህላዊ ውዝዋዜንና ጭፈራ ከፈንዲቃ ጋር በየካ ሚካኤል ማቅረቡን ገልጿል፡፡

በተለያዩ የክልል ከተሞች እየዞረ ባህላዊ ውዝዋዜዎችን ከአንድ ዓመት በላይ ማጥናቱን የሚገልጸው መላኩ፣ በፍለጋ ፕሮጀክቱ አማካይነት ለአዲስ አበባ ቅርብ የሆኑ አካባቢዎች የሚገኙ ባህላዊ ጭፈራዎችን በተጨማሪም አቅም ሲፈቅድ ደግሞ የሌሎችንም ውዝዋዜዎችና ጭፈራዎች የጥምቀቱ በዓል አካል ለማድረግ ትልም እንዳለው ገልጿል፡፡

በከያኒ መላኩ አገላለጽ፣ የጥምቀት በዓል በድምቀቱናውበቱ ከሃይማኖታዊ በዓልነት ባሻገር በተለያዩ ብሔረሰቦች ባህላዊና ትውፊታዊ ክዋኔዎች የተዋበ ክብረ በዓል በመሆኑ፣ ለኢትዮጵያ ቱሪዝም ዕድገት ትልቅ ድርሻ ካላቸው ሁነቶች አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ ስለሆነም የተባበሩት መንግሥታ የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በማይዳሰስ ህያው ቅርስነት ጥምቀትን መመዝገቡ ድንበር ተሻጋሪ በዓል አድርጎታል ብለዋል።

የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነ ጥበባት ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ጌትነት ባደረጉት ንግግርም፣ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ቅርሶች የማኅበረሰቡ መገለጫዎች በመሆናቸው በማጥናት፣ በመጠበቅ፣ በማሳደግና ለዓለም በማስተዋወቅ ለኢትዮጵያ ልማት እንዲውሉ እናድርግ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ጥምቀት የሃይማኖት ክብረ በዓል ብቻ አለመሆኑን፣ የአክብሮቱን መጠን ለማላቅ ጭፈራዎችና ዝማሬዎች ይቀላቀላሉ ያሉት አቶ ይታገሱ፣ ባህል የሚገዝፈውና ለሌሎች መሸጋገር የሚችለው በስፋት ሕዝቡ ውስጥ ሲሠርፅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በውይይት መድረኩም ላይ የጋሞ ብሔረሰብ አባላት ባህላዊ ልብሶችን በመልበስ የባህሉን ጭፈራ ለታዳሚው አቅርበዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...