Wednesday, June 12, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየጤናውን ዘርፍ እየፈተኑ ያሉ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ምግቦች

የጤናውን ዘርፍ እየፈተኑ ያሉ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ምግቦች

ቀን:

በኢትዮጵያ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ምግብ ነክ ነገሮችና መጠጦችን በሕገወጥ መልኩ ለገበያ ማቅረብ ከተለመደ ቆይቷል፡፡ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ምርቶችን በስፋት በማዘጋጀት ለገበያ እያዋሉ የሚገኙ የዘርፉ ተዋናዮች ከተማዋ ላይ ተበራክተዋል፡፡

እነዚህም ተዋናዮች የራሳቸውን ጥቅም በማስቀደም የማኅበረሰቡ ጤና ላይ ቁማር እየተጫወቱ ይገኛል፡፡ ይህም የጤና ዘርፉ ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳደረ በመሆኑ ያሉትን ችግሮች ለመቀልበስ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና መድኃኒት የጤና እንክብካቤ ቁጥጥር ባለሥልጣን እየሠራ ይገኛል፡፡

በባለሥልጣኑ የምግብና ጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ምሬሳ ሚደቅሳ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የተለያዩ ምርቶችን የሚያመርቱ የዘርፉ ተዋናዮች ላይ በዓመት ሁለት ጊዜ ወደ ተቋማቱ በመሄድ የብቃት ማረጋገጥ ይሠራል፡፡ ዘንድሮም ደረጃቸውን ያልጠበቁ ምርቶችን ሲያመርቱ የተገኙ ተቋማት በመገኘታቸው ዕርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡

- Advertisement -

የምግብና የመጠጥ አገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸውን ምርቶች ለገበያ በማቅረብ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አምራቾችም መቀጣታቸውን የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ በ2014 በጀት ዓመት ከ188 በላይ ለሚሆኑ የዘርፉ ተዋናዮች የቃል ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠ አሳውቀዋል፡፡

98 ለሚሆኑ ተቋማት የጽሑፍ ማስንቀቂያ እንደተሰጣቸው፣ ከንፅህና አንፃር ክፍተት የታየባቸው 71 ተቋማት እንዲታሸጉ መደረጉን አቶ ምሬሳ ገልጸዋል፡፡

የአገልግሎት ዘመናቸው ያለፈባቸው 3,729.4 ኪሎ ግራም ያህል የምግብ ነክና ከ396 ሊትር በላይ የመጠጥ ምርቶች መወገዳቸውንም አክለዋል፡፡

አገልግሎታቸው ያለፈባቸውን ምርቶች የሚያመርቱ ተቋማት ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድረግ ከአንድም ሁለት ጊዜ ከዘርፉ ተዋናዮች ጋር የውይይት መድረክ ማካሄዳቸውንና በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን በመጠቀም የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም መካሄዱንም ተናግረዋል፡፡

በክፍለ ከተማና በወረዳ ላይ የሚገኙ ተቋማት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን ቢሠሩም፣ አብዛኛውን ጊዜ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ምግቦችንና መጠጦችን በገበያ ላይ እንደሚገኙ በኮልፌ፣ በአዲስ ከተማ፣ በንፋስ ስልክና በአራዳ ክፍለ ከተሞች ላይ ችግሩ ይበልጥ እንደሚታይ ገልጸዋል፡፡

ደረጃቸውን የጠበቁ ምርቶችን አምርተው ለገበያ ለሚያቀርቡ የዘርፉ ተዋናዮች ዕውቅናና የተለያዩ ሽልማት እንደሚሰጣቸው፣ በቁጥጥር ጊዜም እነዚህ ተቋማቶች ላይ ምንም ዓይነት ችግር እንዳልታየባቸው ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ በፊት ደረጃቸውን ያልጠበቁ ምርቶችን ሲያመርቱ የተገኙ ተቋሞችን ሙሉ ለሙሉ የንግድ ፈቃዱ እንዲሰረዝ መደረጉን፣ በተለይም የበዓል ወቅት ላይ እንደዚህ ዓይነት ችግሮች እንደሚታይና ይህንንም በመገንዘብ ማኅበረሰቡ ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ምርቶችን መገበያየት አለበት ብለዋል፡፡

ከአምራቹ ጋር በመቀናጀት ሕገወጥ በሆነ መንገድ ምርቶች እንዲሠራጩ የሚያደርጉ የባለሥልጣኑ ሠራተኞች ላይ ዕርምጃ እንደሚወሰድ፣ ከዚህ በፊትም በዚህ ተግባር ላይ ሲንቀሳቀሱ የተያዙ ሠራተኞች ከሥራ መሰናበታቸውን አስታውቀዋል፡፡

በ2013 ሒሳብ ዓመትም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የዘርፉ ተዋናዮች ደረጃቸውን ያልጠበቁ ምርቶችን ሲያመርቱ መገኘታቸውን፣ ለድርጅቶቹም ማስጠንቀቂያ ጽሑፍ ከመስጠት ባለፈ ተቋማቸው እንዲታሸግ ተደርጓል ብለዋል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...