Wednesday, April 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየእንግሊዝ የማዕድን ኩባንያ ለመንግሥት ያቀረበው የጊዜ ማራዘሚያ ጥያቄ ውድቅ ተደረገ

የእንግሊዝ የማዕድን ኩባንያ ለመንግሥት ያቀረበው የጊዜ ማራዘሚያ ጥያቄ ውድቅ ተደረገ

ቀን:

ኒው ኤጅ የተባለው የእንግሊዝ የማዕድን ኩባንያ የኢትዮጵያ ፈቃዱ እንዲራዘምለት ያቀረበውን ጥያቄ፣ የማዕድን ሚኒስቴር ውድቅ አድርጎ ፈቃዱ እንዲመለስ ወሰነ።

የኒው ኤጅ ኩባንያ ምክትል ፕሬዚዳንትና የኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ ዴቪድ ፒል ሰሞኑን በጻፉት ደብዳቤ፣ በማዕድን ሚኒስቴር ውሳኔ ማዘናቸውን፣ ነገር ግን ውሳኔውን ተቀብለው ፈቃዱን ለመመለስና ርክክብ ለመፈጸም መስማማታቸውን እንደገለጹ  ለማወቅችሏል።

ኩባንያው በሶማሌ ክልል በኦጋዴን አካባቢ ያለውን የተፈጥሮ ጋዝና ነዳጅ ክምችት ለማውጣት ... 2007 ፈቃድ ያገኘ ሲሆንበዚሁ አካባቢ 1.6 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ የተረጋገጠ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ማግኘቱን ... 2014 ይፋ አድርጎ ነበር። 

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ይሁን እንጂ ኩባንያው የተገኘውን ክምችት በማምረት ለገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ፋይናንስ የሌለው በመሆኑ፣ የተፈጥሮ ሀብቱን ለማልማት በቂ ጥረት ሳያደርግ የፈቃድ ዘመኑ ከሁለት ዓመት በፊት የተጠናቀቀ ቢሆንምበፈቃድ ውሉ ላይ ያለውን ከአቅም በላይ የሆነ አስገዳጅ ሁኔታ በመጥቀሱ የጊዜ ማራዘሚያ ተሰጥቶታል።

ኩባንያው ከአቅም በላይ የሆነ አስገዳጅ ሁኔታ ብሎ ያቀረበው ምክንያት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የኮቪድ ወረርሽኝ እንደሆነ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የማዕድን ሚኒስትሩ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ለኩባንያው በጥቅምት ወር 2014 ዓ.ም. በጻፉት ደብዳቤ፣ በምክንያትነት የቀረበውን የአስገዳጅ ሁኔታ ከግምት በማስገባት የአንድ ዓመት ማራዘሚያ ለኩባንያው ቢፈቀድም፣ በተሰጠው የአንድ ዓመት ማራዘሚያም ሆነ በጥቅሉ ባለፉት 14 ዓመታት ውስጥ የተፈጥሮ ሀብቱን ለማልማት ያደረገው ጥረት ከሚጠበቀው በታች በመሆኑ የፈቃድ ጊዜው ማብቃቱን አስታውቀዋል።

ይሁን እንጂ ኩባንያው የሚኒስቴሩን ውሳኔ ተገቢ እንዳልሆነና በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ውይይት በማድረግ ለማስረዳት እንዲፈቀድለት መጠየቁን ተከትሎ፣ ከአቅም በላይ የተባለው አስገዳጅ ሁኔታ መቀጠልን ማዕከል ባደረገው የኩባንያው መከራከሪያ አጀንዳ ላይ ተጨማሪ ውይይት መደረጉ ታውቋል፡፡

ተጨማሪ ውይይቱን ተከትሎም የማዕድን ሚኒስትሩ የመጨረሻ ያሉትን ደብዳቤ ... ጃንዋሪ 4 ቀን 2022 በመጻፍ፣ ተጨማሪ የጊዜ ማራዘሚያ ለኩባንያው እንደማይሰጥ አስታውቀዋል።

የኩባንያው ምክትል ፕሬዚዳንት ፒል ... ጃንዋሪ 28 ቀን 2022 በጻፉት ምላሽ ደብዳቤ፣ ‹‹ለረዥም ዓመታት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ከነበረን መልካም ገንኙነት አኳያ በማዕድን ሚኒስቴር ውሳኔ እናዝናለን፤›› ብለዋል።

ከአቅም በላይ በሆነ አስገዳጅ ሁኔታ ምክንያት ፈቃድ ሊራዘም እንደሚችል በውል ስምምነቱ ላይ መጠቀሱንና የኮቪድ ወረርሽኝም አንዱ አስገደጅ ሁኔታ እንደሆነ የጠቀሱት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፣ ይህ አስገዳጅ ሁኔታም እየቀጠለ መሆኑን ገልጸዋል። 

ነገር ግንማዕድን ሚኒስቴር የመጨረሻ ውሳኔውን በማሳወቁ ኩባንያው (ኒው ኤጅ) ኦጋዴን በሚገኘው የማዕድን ፍለጋ ቦታ ያሉትን ንብረቶች፣ ለማዕድን ሚኒስቴር አስረክቦ ከኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ እንደሚወጣ አስታውቀዋል። 

በኦጋዴን የሚገኘውን የኩባንያው ንብረቶች ለማዕድን ሚኒስቴር ለማስረከብም፣ በኢትዮጵያ የሚገኘው የኩባንያው ቢሮው የሥራ ኃላፊዎችን እንደወከለ ለማወቅ ተችሏል። 

የአገሪቱን የማዕድን ሀብት ለማልማት የአሥር ዓመትና ከዚያ በላይ ፈቃድ የወሰዱ በርካታ ኩባንያዎች የማዕድን ሀብቱን ከማልማት ይልቅያገኙትን የማዕድን ልማት ፈቃድ ለጥቂት ዓመታት በይዞታቸው አቆይተው ለሌላ ኩባንያ በመሸጥ ኪራይ እንደሚሰበስቡ ይታወቃል። 

ታከለ (ኢንጂነር) የማዕድን ሚኒስትር ሆነው ከተሾሙ በኋላ በእነዚህ ኩባንያዎች ላይ ትኩረት አድርገው እየተንቀሳቀሱ ሲሆንበኦጋዴን የተገኘውን የተፈጥሮ ጋዝና ነዳጅ ለማምረት ፈቃድ የወሰደው የቻይናው ፖሊ ሲኤል ኩባንያም የተፈጥሮ ሀብቱን ለበርካታ ዓመታት ሳያለማ በመቅረቱ፣ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠው መዘገባችን ይታወሳል። 

ኒው ኤጅ የተባለው የእንግሊዝ ኩባንያም በኦጋዴን የተገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ ለማምረት ያገኘውን ፈቃድ 50 በመቶ ድርሻ ለመሸጥ እየተንቀሳቀሰ ሳለ፣ ፈቃዱን እንዲመልስ፣ በማዕድን ሚኒስቴር እንደተወሰነበት መረጃዎች ያመለክታሉ።

የማዕድን ሚኒስቴር በፖሊ ጂሲ ኤል ኩባንያ የመጨረሻ ዕጣ ፈንታ ላይ ከመወሰኑ በፊት፣ ውልን የተመለከቱ የሕግ ጉዳዮች ላይ የፍትሕ ሚኒስቴር አስተያየት እየተጠበቀ እንደሆነ ሪፖርተር ከምንጮቹ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። 

በተጨማሪም በወለጋ የቱሉ ካፒ ወርቅን ለማምረት ፈቃድ የወሰደው የእንግሊዙ ከፊ ሚነራልና በአፋር የፖታሽ ማዕድን ለማልማት ፈቃድ የወሰደው ያራ የተባሉት ኩባንያዎች፣ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ከደረሳቸው ታዋቂ ኩባንያዎች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...