Friday, December 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትኢትዮጵያውያን አትሌቶች የደመቁበት የውድድር ሳምንት

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የደመቁበት የውድድር ሳምንት

ቀን:

በተለያዩ የአውሮፓ አገሮች በተከናወኑ የአትሌቲክስ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል አድርገዋል፡፡ በጀርመን፣ ስፔን እንዲሁም ጣሊያን በተደረጉ ውድድሮች በርካታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተሳትፈዋል፡፡

በጀርመን ካርልስሩሄ የጀመረው የዓለም የቤት ውስጥ የዙር ውድድር በሪሁ አረጋዊና አክሱማዊት እምባየ በድል ጀምረዋል፡፡ በሪሁ 3,000 ሜትርን 7፡26.20 በመግባት ውድድሩን በበላይነት አጠናቋል፡፡ አትሌቱ የገባበት ሰዓትም የቤት ውስጥ አምስተኛው ምርጥ ሰዓት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በሪሁ የገባበት ሰዓት እ.ኤ.አ. 1998 በኬንያዊው ዳንኤል ኩመን ተይዞ የነበረውን 7፡24.90 ክብረ ወሰን ሊያሻሽል ቢጥርም የዓለም ሁለተኛውን የቤት ውስጥ ምርጥ ክብረ ወሰን ባለቤት መሆን ግን ችሏል፡፡ በሪሁ ከመወለዱ ሦስት ዓመት በፊት በ1998 ቡዳፔስት በኬንያዊ አትሌት የተመዘገበው ክብረ ወሰኑ፣ ለ24 ዓመት የደፈረው የለም፡፡

በ1998 በጀርመን ካርልስሩሄ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ 7፡26.15 ክብረ ወሰን የያዘበት ጊዜም እንደነበር ይታወሳል፡፡

በቶኪዮ ኦሊምፒክ በ10,000 ሜትር አራተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው በሪሁ ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ ተስፋ ከተጣለባቸው አትሌቶች መካከል ቀዳሚው ነው፡፡

አትሌቱ በዘንድሮ የፈረንጆች አዲስ ዓመት ዋዜማ ላይ ባርሴሎና ላይ በተደረገው አምስት ኪሎ ሜትር ውድድር 12፡49 በማጠናቀቅ የርቀቱን ክብረ ወሰን መጨበጥ የቻለ ሲሆን፣ በተለይ በ2021 የነበረውን ችሎታ ተመልክተው ለመጀመሪያ ጊዜ በተካፈለበት የቤት ውስጥ ውድድር ከፍተኛ ግምት እንዲሰጠው አስችሎት ነበር፡፡

እንደ የዓለም አትሌቲክስ ዘገባ መሠረት በሪሁ ከመጀመሪያው አሯሯጩ አማካይነት የመጀመሪያው 1,000 ሜትር 2፡27.20 መሮጡን ተከትሎ፣ ክብረ ወሰኑን ሊሰብር የሚችልበትን ዕድል ይኖራል የሚል ግምት ተሰጥቶት ነበር፡፡

ሆኖም አሯሯጩ ከተለየው በኋላ ግን መጀመሪያ በመጣበት ፍጥነት መቀጠል ባለመቻሉ፣ 2000 ሜትር ርቀቱን 4፡56.87 በሆነ ሰዓት እንደሮጠው ያነሳል፡፡

በሪሁ እ.ኤ.አ. 2021 በፈረንሣይ ሊቪን ከተማ በተደረገ 3,000 ሜትር ውድድር 7፡29.24 በመግባት በታዳጊ አትሌት የተመዘገበ ፈጣን ሰዓት ማስመዝገብ ችሏል፡፡ የ20 ዓመት ዕድሜ ላይ የሚገኘው አትሌቱ፣ በ2022 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ከሚጠበቁ አትሌቶች መካከል ቀዳሚው ነው፡፡

በሴቶች 1,500 ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያቱ አክሱማዊት እምባየ፣ ሒሩት መሸሻና ፍሬወይኒ ኃይሉ ባደረጉት ፉክክር፣ ተከታትለው መግባት ችለዋል፡፡ እንደ ወንዶቹ 3,000 ሜትር ውድድር፣ የሴቶቹም 1,500 ሜትር ውድድሩ በፍጥነት የጀመረ ቢሆንም አሯሯጮች ተቆርጠው ከቀሩ በኋላ በጀመሩበት ፍጥነት መቀጠል አልቻሉም ነበር፡፡

በዚህም አክሱማዊት 4፡02.12 በሆነ ሰዓት አንደኛ፣ ሒሩት መሻሻ 4፡02.14 ሁለተኛ፣ እንዲሁም በቶኪዮ ኦሊምፒክ አራተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ የቻለችው ፍሬወይኒ ኃይሉ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ ተከታትለው በመግባት በበላይነት አጠናቀዋል፡፡

በጀርመን የጀመረው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በአምስት ከተሞች በዙር ይቀጥላል፡፡ ከጀርመን ቀጥሎ፣ አሜሪካ፣ ፈረንሣይ፣ እንግሊዝ፣ ፖላንድና ስፔን ይከናወናል፡፡

በሌላ በኩል በሳምንቱ መጨረሻ በስፔን ሲቪላ በተደረገ የግማሽ ማራቶን ውድድር በወንዶች ገብሬ እርቅይሁን 1፡00.26 ሦስተኛ ደረጃ አጠናቋል፡፡ በሌላኛዋ ስፔን ከተማ ጌታፊ በተደረገ የግማሽ ማራቶን ሀብታሙ ብርሌው 1፡02.16 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ፣ ስንታየሁ ድንቄሳ 1፡02.37 ሦስተኛ በመሆን አጠናቋል፡፡

በሴቶች ቤተልሔም አፈንጉሥ ይመር 1፡08.22 በሆነ ጊዜ አንደኛ እንዲሁም ብርቱካን ወርቅነህ 1፡09.11 ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችለዋል፡፡

ሌላኛው በጣሊያን ሺቶሬ ኦሎና በተደረገ አገር አቋራጭ ውድድር ንብረት መላክ 28፡33 በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ፣ ታደሰ ወርቁ 28፡36 በመግባት ሦስተኛ  እንዲሁም ቢቂላ ታደሰ 28፡36 አራተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅ ችሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...