Wednesday, February 28, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ሥጋ ላኪዎች ለምርታቸው ዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲወጣለት ጠየቁ

ተዛማጅ ፅሁፎች

ሥጋ ላኪዎች የገበያ መዳረሻቸውን ለማሳደግ ለኢትዮጵያ የሥጋ ምርት ዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲወጣለት ጠየቁ።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮያ የሚገኙ ሥጋ ላኪዎች ምርታቸውን በስፋት የሚልኩት ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሲሆን፣ ወደ ሌሎች አገሮች ምርታቸውን ለመላክ የሚያስችል የጥራት ደረጃ ባለመኖሩ መቸገራቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል።

በኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ የቢሾፍቱ ኤክስፖርት ቄራ ዳይሬክተር ሳለአምላክ አብነው (ዶ/)፣ በቂ የገበያ መዳረሻ ባለመኖሩ ከማምረት አቅማቸው 15 በመቶ በታች እየሠሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

ሥጋ ምርት ወደ እስያና አውሮፓ አገሮች ለመላክ ሲፈለግ የሚጠየቀውን ደረጃ ስለማያሟላ በዋናነት ወደ ተባበሩትረብምሬትስ እየላኩ እንደሚገኙ የገለጹት ሳለአምላክ (ዶ/)፣ የሥጋው ጥራት በዓለም አቀፍ ደረጃ በወጣ መሥፈርት መሠረት መገለጽ አለበት ብለዋል።

በተጨማሪም ለዕርድ የሚቀርቡ ከብቶች መገኛ፣ ዓይነትና፣ የጥራት ደረጃ የሚገለጽበት አሠራር ባለመኖሩ፣ መሥፈርቱን ለሚጠይቁ አገሮች ለመላክ አልተቻለም ሲሉ አስረድተዋል።

የገበያ መዳረሻው ሰፊ ባለመሆኑ፣ ተወዳዳሪው በመብዛቱና በዋጋውም ላይ ተፅዕኖ እየፈጠረ እንደሚገኝ ገልጸው፣ ምንም እንኳን ብሔራዊ ባንክ የአንድ ቶን ሥጋ ዋጋ ከ5,600 እስከ 5,800 ዶላር እንዲሆን ቢወስንም በሕገወጥ መንገድ የሚሸጡ መኖራቸውን አክለዋል።

የእንስሳትርባታ እጥረት ከዋና ዋና ተግዳሮቶች መካከል አንዱ መሆኑን ገልጸው፣ አሁን ያሉት የቁም እንስሳት ሥጋ የኤክስፖርት ጥራቱን ያልጠበቀ መሆኑንም አስረድዋል። ‹‹በርካታ ከብቶች አሉን፣ ነገር ግን ወደ ሥጋ ስንመጣ በቂ መጠን የለም፡፡ ምክንያቱም ወደ ውጭ የሚላክ ሥጋ የሚገኝባቸው የከብት ዝርያዎች ቁጥር አነስተኛ ነው፤›› ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሥጋ አምራቾችና ላኪዎች ማኅበር ዋና ጸሐፊ አቶ አበባው መኮንን፣ ሥጋ ወደ ውጭ የሚልኩ ቄራዎችመታዊ የማምረት አቅማቸው 200,000 ቶን በላይ ቢሆንም፣ አሁን እየተመረተ የሚገኘው 20,000 ቶን በታች መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ የሆነበት ምክንያት በተለይ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ሥጋ የሚገኝበት የከብት አቅርቦት ባለመኖሩ መሆኑን አብራርተዋል። በኢትዮጵያ ካለው አጠቃላይ የእንስሳት ቁጥር አንፃር ሲታይ ወደ ውጭ ለመላክ የሚችል ሥጋ የሚገኝባቸው እንስሳት ቁጥር እጅግ በጣም አነስተኛ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።

‹‹እንደ እስያና አውሮፓ ያሉ አገሮች የሥጋ ምርት ሲቀበሉ በተለይ የእንስሳቱን መገኛ፣ እንዲሁም የጤና ሁኔታ ማስቀመጥ እንደ ግዴታ ስለሚጠይቁ ምርቶቻችንን ወደ እነዚህ አገሮች መላክ አልቻልንም፤›› ያሉት አቶ አበባው፣ ለዚህም አገራዊ የሆነ ደረጃ የሚሰጥበት አሠራርና የእንስሳት ጤና አጠባበቅ ሥርዓት ያስፈልጋል ሲሉ አክለዋል።

በተጨማሪም በአብዛኛው ወደ ውጭ የሚላከው የፍየል ሥጋ መሆኑን ጠቅሰው፣ የበሬ ሥጋ የአገር ውስጥ ዋጋ ከዓለም አቀፍ ገበያው ዋጋ ስለሚበልጥ አዋጭ አይደለም ብለዋል። ወደ ውጭ ከሚላከው የሥጋ ምርት ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነውፍየል ሥጋ መሆኑን፣ የበሬ ሥጋ ከአንድ በመቶ እንደማይበልጥ ተናግረዋል። ‹‹ይህም በበሬ ሥጋ በኩል ያለውን አቅም እንዳንጠቀም አድርጎናል፤›› ሲሉ አክለዋል።

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2020 በእንስሳት ብዛት ከአፍሪካ ቀዳሚ ስትሆን 65 ሚሊዮን ከብቶች፣ 40 ሚሊዮን በጎች፣ 51 ሚሊዮን ፍየሎች፣ ስምንት ሚሊዮን ግመሎችና 49 ሚሊዮን ዶሮዎች እንዳሏት የማዕከላዊ ስታትስቲክስ አገልግሎት መረጃ ያሳያል።

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ ዮሐንስ ግርማ (ዶ/ር)፣ ኢትዮጵያ የሥጋ ምርት ለዓለም አቀፍ ገበያ ለማቅረብ ዓለም አቀፍ መሥፈርቶችን ማሟላት አለመቻሏን ይገልጻሉ። ለዚህም እንደ ዋና ምክንያት የሚነሳውን የእንስሳት በሽታ ከኢትዮጵያ ማጥፋት አለመቻሉ መሆኑን አስረድተዋል።

‹‹እንደ አውሮፓና እስያ ያሉ አገሮች ትልቁ ሥጋታቸው የእንስሳት በሽታ በመሆኑ፣ ካስቀመጧቸው መሥፈርቶች መካከል ሥጋው በሽታ ከሌለበት ቦታ የተገኘ መሆኑን ማረጋገጥ ነው፤›› ሲሉ አብራርተዋል። ‹‹ነገር ግን ያንን ለማድረግ በርካታ የእንስሳት በሽታዎች በመኖራቸው፣ የትኛውም የአገራችን ክፍል ከበሽታ ነፃ መሆኑን ማረጋገጥ አልቻልንም፤›› ብለዋል።

በተጨማሪም ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የእንስሳት ክትባት መስጠት አለመቻሉ የዘርፉ ፈተና መሆኑን ዮሐንስ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

የሥጋ ጥራት ደረጃን ለማውጣትና የእንስሳት መገኛና ዓይነትን ለማስቀመጥ የሚችል ሥርዓት ለመዘርጋት ቢሞከርም፣ በአቅም ማነስ ምክንያት እስካሁን ተግባራዊ ለማድረግ አለመቻሉንም ተናግረዋል።

ለውጭ ገበያ የሚሆን ሥጋ የሚገኝባቸው ከብቶችን ቁጥር ለማሳደግ ግብርና ሚኒስቴር ዘመናዊ የእንስሳትርባታ ማዕከላትን በተለይም በጉጂ፣ በሶማሌናቦረና አካባቢዎች እያስፋፋ እንደሚገኝ ዮሐንስ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

በተጨማሪም ሚኒስቴሩ የሥጋ ጥራት፣ እንዲሁም የእንስሳት ጤናና ምዝገባ ሥርዓትን ለማሳደግ ስትራቴጂ በማዘጋጀት ለዓለም የእንስሳት ጤና ድርጅት አቅርቦ ምክረ ሐሳቦችን መቀበሉን፣ እንዲሁም የእንስሳት ጤና ሥርዓትን ማሻሻል ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ውስጥ 10,000 ቶን የሥጋ ምርት ወደ ውጭ መላኩን፣ 50 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱን የሥጋና የወተት ልማት ኢንስቲትዩት መረጃ ያመለክታል።

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች