Sunday, July 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትለዓለም የሴቶች ዋንጫ ለመብቃት አንድ ወሳኝ ጨዋታ የሚጠብቃት ኢትዮጵያ

ለዓለም የሴቶች ዋንጫ ለመብቃት አንድ ወሳኝ ጨዋታ የሚጠብቃት ኢትዮጵያ

ቀን:

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን፣ ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት በታች ሴቶች የዓለም ዋንጫ ሁለተኛ ማጣሪያ የታንዛኒያ አቻውን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ባለፈው ዓርብ ጥር 27 ቀን 2014 ዓ.ም. አስተናግዶ 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ በመጀመርያው ግጥሚያ 1 ለ 0 ቢሸነፍም በመልሱ ጨዋታ ባስመዘገበው የአንድ ግብ ብልጫ ለመጨረሻው ምዕራፍ ተሸጋግሯል፡፡ ሁለቱን ግቦች ያስቆጠረችው ረድዔት አስረሳኸኝ ናት፡፡ ቡድኑ ቅድመ ማጣሪያውን ሳይሳተፍ በቀጥታ በአንደኛው ዙር ጨዋታ  ሩዋንዳን በደርሶ መልስ 8 ለ 0፣ በሁለተኛው ዙር ቦትስዋናን በደርሶ መልስ 8 ለ 2 በማሸነፉ ነበር ለሦስተኛው ዙር የበቃው፡፡ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በመጪው ነሐሴ ለሚካሄደው የኮስታሪካ የዓለም ዋንጫ ትኬት ለመቁረጥ በቀጣይ ከዑጋንዳና ጋና አሸናፊ ጋር የመጨረሻ ወሳኝ የማጣሪያ ጨዋታ ይጠብቀዋል፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ ከሁለት ወራት በፊት በዑጋንዳ በተዘጋጀው የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ (ሴካፋ) ዋንጫ ሻምፒዮን መሆኑ ይታወሳል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሚዲያው በሕዝብ የህሊና ችሎት ከተዳኘ በቂ ነው!

መሰንበቻውን ድንገት ሳይታሰብ ያለ ማስጠንቀቂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

የባህር በር ጉዳይ

በታምሩ ወንድም አገኘሁ ድሮ ድሮ ገና ልጅ ሆኜ ፊደል እንደቆጠርኩ...

አገሩ ፖለቲካዊ ስክነትና መደማማጥ ያስፈልገዋል

በንጉሥ ወዳጀነው    ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ቤት ነች፡፡ ‹‹ጥያቄዬ ተመለሰልኝ››፣...

የመንግሥት የሰብዓዊ መብት ተቋም ለምን የመንግሥት ሚዲያን ማስተማር አቃተው

በገነት ዓለሙ የአገራችን የ2016 የበጀት ዓመት መሰናበቻና የአዲሱ የ2017 በጀት...