በኮቪድ-19 ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ምክንያት ዓምናና ሃቻምና በይፋ ያልተካሄደው የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ በአዲስ አበባ ከተማ ከጥር 28 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ እየተካሄደ ነው፡፡ ጉባዔውን ምክንያት በማድረግ የኅብረቱ መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ፣ በተለያዩ ቦታዎች ከዋዜማው ቀናት ጀምሮ አፍሪካዊ አሻራን በሚያሳዩ ምልክቶች ተሞልታለች፡፡ ከነዚህ መካከል በመስቀል አደባባይ የእግረኛ መተላለፊያዎች በተጣለው ዳስ የየአገሮቹ ሰንደቅ ዓላማዎችን የሚያሳዩ ሠሌዳዎች፣ በቦሌ አካባቢ ደግሞ ከ60 ፈሪ ዓመት በፊት (59) የአፍሪካ አንድነትን የመሠረቱ አባት መሪዎችን ፎቶ በከፊል የሚያሳዩ ይገኙባቸዋል፡፡
ፎቶ መስፍን ሰሎሞን