Tuesday, May 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ኪንና ባህልበአዲስ አበባ ከተማ የቻይና ባህል ማዕከል ሊገነባ መሆኑ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ከተማ የቻይና ባህል ማዕከል ሊገነባ መሆኑ ተገለጸ

ቀን:

ቻይና በአዲስ አበባ ከተማ የባህል ማዕከል ግንባታ የምታከናውንበትን ስድስት ሺሕ ካሬ ሜትር ከከተማ አስተዳደሩ ተረከበች፡፡

ማዕከሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ከቻይና መንግሥት ጋር ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከርና የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊም ሆነ ማኅበራዊ ዕድገትን ለማፋጠን ያለመ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ጥር 30 ቀን 2014 ዓ.ም. በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡

ለባህል ማዕከል ግንባታ የሚውለው ቦታ እንዲሰጥ ውሳኔ የተላለፈው ጥር 22 ቀን በተደረገው የካቢኔ ስብሰባ ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡

- Advertisement -

የከተማ አስተዳደሩ የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ዮናስ ዘውዴ እንደገለጹት፣ የባህል ማዕከሉን ግንባታ አስመልክቶ ከዚህ ቀደም የቻይና መንግሥት በተደጋጋሚ ጊዜ የቦታ ይዞታ ሲጠይቅ እንደነበርና ጥያቄውም አግባብነት ያለው በመሆኑ ፈቃዱ ሊሰጥ ተችሏል፡፡

የባህል ማዕከሉ በከተማዋ መገንባቱ አንድም የሁለቱ አገሮችን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያጠናክራል ያሉት ኃላፊው፣ በሌላ በኩል ደግሞ የባህል እሴቶቻችን ላይ የልምድ ልውውጥ እንዲኖረን ትልቅ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡

ለማዕከሉ ግንባታም ስድስት ሺሕ ካሬ ሜትር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አካባቢ መሰጠቱን ገልጸው፣ ግንባታውም በምን ያህል በጀትና በምን ያህል ጊዜ ይጠናቀቃል የሚለውን ጥያቄ በተለያዩ ጊዜያት የሚያሳውቁ መሆኑን አቶ ዮናስ ጠቁመዋል፡፡

በኢትዮጵያና በቻይና በኩል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር፣ የባህል ማዕከሉ የጎላ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው፣ ማዕከሉም በከተማዋ ላይ ተገንብተው የተለያዩ አገልግሎቶችን እየሰጡ ያሉ ሌሎች የባህል ማዕከሎች ጋር ተያያዥነት እንደሚኖረው ኃላፊው አስረድተዋል፡፡  

ከዚሁ ጎን ለጎን የቻይና መንግሥት በሚሰጠው የፋይናንስ ድጋፍ የአፍሪካ የቀርክሃ ሠርቶ ማሳያ የሥልጠና ማዕከል እንደሚገነባ፣ ለግንባታው የሚውል የቦታ ይዞታ ከከተማ አስተዳደሩ በኩል መስጠቱን አብራርተዋል፡፡

ሪፖርተር የቀርክሃ ማዕከሉ በየት አካባቢ ይገነባል? ምን ህል ካሬ ሜትር ነው? በምን ያህል በጀት ይፈጸማል? የሚሉ ጥያቄዎችን ለከተማ አስተዳደሩ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዮናስ ጥያቄ ቢያቀርብም ምላሹም ማግኘት  አልቻለም፡፡

ኃላፊው የ35ኛውን የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ በስኬት እንዲጠናቀቅ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች፣ አመራሮች፣ የጤና ባለሙያዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ በመወጣታቸው ምሥጋና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የከተማ አስተዳደሩ የስድስት ወራት አፈጻጸም ግምገማ የተሻለ ውጤት መገኘቱንና በቀጣይም የተሻለ ሥራ ለማከናወን የከተማ አስተዳደሩ ቀዳሚ ሥራው እንደሚሆን አቶ ዮናስ ተናግረዋል፡፡

በጊዜ ባለመልማቱ ከ13 የአፍሪካ አገሮች ኤምባሲዎች ተነጥቆ የነበረው መሬት ለየኤምባሲዎቹ እንዲመለስላቸው መወሰኑንም ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የተቋቋሙት የጣሊያን፣ የፈረንሣይ፣ የጀርመንና የሩሲያ የባህል ማዕከላት የተለያዩ አገልግሎቶችን እየሰጡ ይገኛል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ለውጭ ባንኮች መከፈት አገር በቀል ባንኮችን ለምን አስፈራቸው?

የማይረጥቡ ዓሳዎች የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች ሙግት ሲሞገት! - በአመሐ...

የምርጫ 97 ትውስታ!

በበቀለ ሹሜ      መሰናዶ ኢሕአዴግ ተሰነጣጥቆ ከመወገድ ከተረፈ በኋላ፣ አገዛዙን ከማሻሻልና...

ሸማቾች የሚሰቃዩት በዋጋ ንረት ብቻ አይደለም!

የሸማች ችግር ብዙ ነው፡፡ ሸማቾች የሚፈተኑት ባልተገባ የዋጋ ጭማሪ...

መንግሥት ከለጋሽ አካላት ሀብት ለማግኘት የጀመረውን ድርድር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፓርላማው አሳሰበ

የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገልጿል አዲስ አበባ...