Saturday, September 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየበጎ ሰው ሽልማት 10ኛው መርሐ ግብር ይፋ ሆነ

የበጎ ሰው ሽልማት 10ኛው መርሐ ግብር ይፋ ሆነ

ቀን:

ከአሥር ዓመታት በፊት ‹‹በጎ ሰዎች በመሸለምና ዕውቅና በመስጠት ሌሎች በጎ ሰዎችን እናፍራ›› በሚል መርሕ ተቋቁሞ፣ ለአገርና ለሕዝብ አርዓያነት ያለው ታላቅ ተግባር ላከናወኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በየዓመቱ ዕውቅና የሚሰጠው የበጎ ሰው ሽልማት ነው፡፡

የበጎ ሰው ሽልማት ለአሥረኛው መርሐ ግብሩ የዕጩዎችን ጥቆማ የካቲት 4 ቀን 2014 ዓ.ም. ከሕዝብ መቀበል ጀምሯል፡፡ ለዚህ የሽልማት መርሐ ግብር ከዚህ በታች በተገለጹት አሥር ዘርፎች እስከ መጋቢት 3 ቀን ድረስ የዕጩዎች ጥቆማ ከሕዝብ እንደሚቀበል አስታውቋል፡፡

በመምህርነት፣ በሳይንስ (ሕክምና፣ ቴክኖሎጂ፣ ፊዚክስ፣ ምሕንድስና፣ ኬሚስትሪ፣ አርክቴክቸር ወዘተ)፣ በኪነ ጥበብ (በፊልም ዳይሬክተርነት)፣ በቢዝነስና ሥራ ፈጠራ፣ መንግሥታዊ ተቋማት ኃላፊነት፣ በቅርስና ባህል፣ ማኅበራዊ ጥናት፣ ሚዲያና ጋዜጠኝነት ለኢትዮጵያ ዕድገት አስተዋጽኦ ያበረከቱ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሚያበረታታ ነው፡፡

ዘንድሮ በኪነ ጥበብ ዘርፍ፣ ከፊልም ጥበብ ውስጥ አንዱ በሆነው የፊልም ዳይሬክተርነት ላይ ትኩረት ይደረጋል ተብሏል፡፡ በሲኒማ ጥበብ ውስጥ ትልቁ ሚና የዳይሬክተሩ መሆኑን፣ ፊልም የአዘጋጁ የምናብ ልህቀት እንደሚታይበት ተወስቷል፡፡

በጋዜጣዊ መግለጫው እንደተብራራው የድምፅና ምስልን፣ የተጻፈ ታሪክና ምናብ፣ በተለያዩና ረቂቅ ቴክኒኮች፣ የቴክኖሎጂን ከፍታ በራሱ ልክ የሚሸምንበት የላቀ ጥበብ ነው፡፡ ለዚህም በፊልም ውስጥ ደራሲው፣ ተዋናዮች፣ የተለያዩ የቴክኒክ ክፍሎችና ተሳታፊዎች ቢኖሩም በአዘጋጁ ስም የሚጠራው፡፡

በኢትዮጵያ የሲኒማ ኢንዱስትሪ ውስጥ የተለያዩ ሙያውን መሠረት ያደረጉ ሽልማቶች እንደሚካሄዱና ሽልማቶቹ ሙያውን ከጥራት አንፃር የሚመዝኑ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ የበጎ ሰው ሽልማት ዋና ማንፀባረቂያውን የሚያደርገው በጎነት ላይ ስለሆነ፣ በዘንድሮው በፊልም አዘገጃጀት ሥራቸው፣ ስኬታቸው ባሻገር፣ ለአገር፣ ለሰው ልጅና ለሙያው ጭምር  ያተረፉትን በጎነት መሠረት አድርጎ እንደሚካሄድ ተነግሯል፡፡

በየዓመቱ በሚቀርቡ ጥሪዎች መሠረት ከሕዝብ በሚቀርቡ ጥቆማዎች ኢትዮጵያ የምትኮራባቸውና የላቀ አርዓያነት ያለው ተግባር ያከናወኑ ሰዎችን ዕውቅና መስጠታቸውን አዘጋጆቹ አስታውሰዋል፡፡ የበጎ ሰው ሽልማትን ለዚህ ያበቃውም በሽልማቱ ሒደት በውጭ አገሮች የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የሕዝብ ተሳትፎ በመኖሩና ይህም ከዓመት ዓመት እያደገ በመሄዱ የተሳትፎው አስፈላጊነት ተገልጿል፡፡ 

ጠቋሚዎች ዕጩዎችን በሚጠቁሙበት ጊዜ ዕጩው ግለሰብ ለአገርና ለሕዝብ ያከናወኑትን ተግባር በዝርዝር እንዲገልጹልንና የሚገኙበትንም አዳራሽ በግልጽ እንዲጠቁሙም በጎ ሰው ሽልማት አሳስቧል፡፡

ተቋሙ ጥቆማውን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የሚቀበለው በስልክ፣ በቫይበር፣ በቴሌግራም፣ በኋትስአፕ፣ በኢሜይልና በፖስታ መሆኑንም አዘጋጆቹ ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...