Thursday, September 21, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአፍሪካ ኅብረት ከፍተኛ ተወካይ የሰላም ውይይቱ በአስቸኳይ እንዲጀመር አሳሰቡ

የአፍሪካ ኅብረት ከፍተኛ ተወካይ የሰላም ውይይቱ በአስቸኳይ እንዲጀመር አሳሰቡ

ቀን:

በአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ኅብረት ከፍተኛ ተወካይ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሉሴጎን ኦባሳንጆኧ የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭትን ለመፍታት አስቸኳይ የሰላም ውይይት መጀመር እንዳለበትና በግጭቱ ሳቢያ ከፍተኛ የሰብዓዊ ዕርዳታ ቀውስ ውስጥ ለወደቁ ማኅበረሰቦች ፈጣን ምላሽ እንደሚያስፈልግ አሳሰቡ።

የአፍሪካ ኅብረት ከፍተኛ ተወካይ የሆኑት የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ ይህንን የተናገሩት፣ ባለፈው ሐሙስ ለአፍሪካ ኅብረት የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤት (PSC) በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታና በአገሪቱ ሰላምን ለመመለስ ስለጀመሩት ጥረት ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።

ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ በአዲስ አበባ የተካሄደው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ከተጠናቀቀ በኋላ፣ ግጭቱ የሚካሄድባቸውን የሰሜን ኢትዮጵያ አካቢዎች የጎበኙ ሲሆን፣ በሳምንቱ መጀመሪያ ከጎበኟቸው አካባቢዎች መካከልም ኮምቦልቻና መቀሌ ተጠቃሽ ናቸው።

ኦባሳንጆከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምክትል ጸሐፊና የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር በመሆን ባለፈው ዓረብ የካቲት 4 ቀን 2014 ዓ.ም. ወደ አፋር ክልል ተጉዘው ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በማግስቱ ሐሙስ ዕለት ለአፍሪካ ኅብረት የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤት ሪፖርት አቅርበዋል።

ዓርብ የካቲት 4 ቀን 2014 ዓ.ም. ደግሞ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ዲፕሎማቶች ተመሳሳይ ገለጻ መስጠታቸውን የኅብረቱ የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤት አስታውቋል።

መንግሥት የጦር ኃይሉ ወደ ትግራይ ክልል እንዳይገባ ማዘዙ፣ በቅርቡም እስረኞችን መፍታቱ እንዲሁም የሕወሓት ኃይልም ጦሩን ወደ ትግራይ ክልል መመለሱ የሰላም ውይይትን ለማስጀመር ምቹ ሁኔታን እንደፈጠሩ ኦባሳንጆ ለምክር ቤቱ ማስረዳታቸውን ገለጻውን በቅርበት የተከታተሉ ምንጮች ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶችን ማግኘት አለመቻል በትግራይ ያለውን የሰብዓዊ ሁኔታ እያባባሰ እንደሆነመጥቀስ፣ መንግሥት አገልግሎቶችን ወደነበሩበት እንዲመለሱ በማድረግ ተጨማሪ የመተማመኛ ዕርምጃ መውስድ አለበት ብለው እንደሚያምኑ መናገራቸውን ምንጮቹ ገልጸዋል።

የአፍሪካ ኅብረት ከፍተኛ ተወካዩ ኦባሳንጆ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ዲፕሎማቶች በሰጡት ማብራሪያ ደግሞ፣ ስለፖለቲካዊ መፍትሔው አጣዳፊነት አጽንኦት መስጠታቸውን የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤቱ አስታውቋል።

አስቸኳይ የሰላም ውይይት በማድረግ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ወደ ነበረበት መመለስ እንደሚያስፈልግ መግለጻቸውን ምክር ቤቱ አስታውቋል።

ምክር ቤቱ የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ በተካሄደበት ወቅት በሰጠው መግለጫ የኦሉሴጎን ጥረት ስኬታማ ለማድረግ ጽሕፈት ቤታቸውን በባለሙያዎች እንደሚያደራጅ አስታውቋል።

 

የኢትዮጵያ መንግሥት ሁሉን አቀፍ አገራዊ ምክክር ለማድረግ የወሰደውን ተነሳሽነትና የጀመረውን ጥረት የአፍሪካ ኅብረት ሙሉ በሙሉ ይደግፋል ያሉት የምክር ቤቱ ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዴዮዬየኅብረቱ ከፍተኛ ተወካይ የሆኑት የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንትም የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ አባላት ከተሰየሙ በኋላ ተሳትፎ እንደሚኖራቸው ገልጸዋል።

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...