Thursday, June 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየጡረታ ፈንድ ለኢንቨስትመንት እንዲውል የሚነደግግ አዋጅ ፀደቀ

የጡረታ ፈንድ ለኢንቨስትመንት እንዲውል የሚነደግግ አዋጅ ፀደቀ

ቀን:

የግልና የመንግሥት ሠራተኞች የጡረታ ፈንዶች አትራፊና አስተማማኝ በሆኑ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ላይ ፈሰስ እንዲደረጉ የሚፈቅዱ ሁለት የተለያዩ አዋጆችን፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማክሰኞ የካቲት 8 ቀን 2014 ዓ.ም. አፀደቀ፡፡

በዚህም መሠረት ‹‹የግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 715/2003›› እና ‹‹የመንግሥት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ ቁጥር 714/2003›› ተሽረዋል፡፡

በአዲሶቹ አዋጆች የሚቋቋሙት የጡረታ ፈንድ አስተዳደር ሥራ አመራር ቦርዶች አዋጭ የሆኑ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችንና ዘርፎችን ያፀድቃሉ፡፡ ነባሮቹ አዋጆች የጡረታ ፈንድ በግምጃ ቤት ሰነድ ግዥ ላይ ብቻ ፈሰስ እንዲደረጉ የሚፈቅዱ ሲሆን፣ ይህ ደግሞ ወለዱ ከሦስት በመቶ የማያልፍ በመሆኑ አመርቂ ገቢ ሊያስገኝ አልቻለም ነበር፡፡

በአዲሱ አዋጆች ድንጋጌ መሠረት የማኅበራዊ ዋስትና ይግባኝ ጉባዔ አባላት አሰያየም በብሔራዊ ባንክ አቅራቢነት በጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲሰየሙ ይደረጋል፡፡

ከሐምሌ 2007 ዓ.ም. ወዲህ የጡረታ መዋጮ ባልከፈሉ ላይ ቅጣት ተፈጻሚ የሚሆን ሲሆን፣ የጡረታ ዕድሜ ጣሪያም ወደ 60 ዓመት ከፍ ተደርጓል፡፡

ቢያንስ አሥር ዓመት ያገለገለ የግል ድርጅት ሠራተኛ አገልግሎት ካቋረጠ፣ ዕድሜው ሲደርስ የጡረታ አበል እስከ ዕድሜ ልክ ይከፈለዋል፡፡ ይህም በበፊቱ አዋጅ ውስጥ ካለው ሃያ ዓመት ዝቅ ተደርጓል፡፡ አዋጆቹን ለማስፈጸም የሚቋቋመው የግልና የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና ፈንድ አስተዳደር መረጃዎችን በሙሉ በዘመናዊ መንገድ (Digitalization) እንዲያስቀመጥ ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡

የተሻሻሉት አዋጆች በአጠቃላይ የነበሩ ችግሮችን ይቀርፋሉ ተብለው የሚጠበቁ ሲሆን፣ በተለይ የሠራተኞቻቸውን ጡረታ በጊዜ ገቢ በማያደርጉ ድርጀቶች ላይ የንግድ ፈቃድ ማደስን እስከ መከልከል ይደርሳል፡፡

ይሁን እንጂ ከፈንዶቹ ኢንቨስትመንት የሚገኘው ተጨማሪ ገቢ ለጡረተኞች የሚደርስበት መንገድ በአዲሱ አዋጅ አልተመለከተም፡፡ ለጡረተኞች የሚከፈለው ገንዘብ በጥቅሉ ከሚሰበሰበው እጅግ ያነሰ መሆኑ አጨቃጫቂ ሆኖ ቢቆይም፣ በአዲሱም አዋጅ ትኩረት አልተደረገበትም፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...