Sunday, June 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናየፌዴራል ፍርድ ቤቶች ተገልጋዮች ዕርካታን 75 በመቶ መድረሱን አረጋግጧል የተባለ ጥናት ይፋ...

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ተገልጋዮች ዕርካታን 75 በመቶ መድረሱን አረጋግጧል የተባለ ጥናት ይፋ ተደረገ

ቀን:

  • ጥናቱ ለዳኝነት ሥርዓቱ መሠረታዊ በሆኑ ነጥቦች ላይ አላተኮረም ተብሏል

በገለልተኛ አካል የተደረገ መሆኑ በተነገረለት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ተገልጋዮች ዕርካታን በሚመለከት የተሠራ ጥናት 75 በመቶ መድረሱ ተገለጸ፡፡ ጥናቱ ለዳኝነት ሥርዓቱ መሠረታዊ ነጥቦች ላይ ያገኘው ውጤት ዝቅተኛ ከመሆኑ አንፃር አርኪ ነው ሊባል እንደማይችልም ተነግሯል፡፡

የአሜሪካ ተራዕዶ ድርጅት በ‹‹ፍትሕ›› ፕሮጀክት ሥር አብኮን በተባለ የአገር ውስጥ የምርምር ተቋም አማካይነት፣ በአዲስ አበባና በድሬዳዋ ከተሞች የሚገኙ 17 የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ላይ፣ የተገልጋዮች ዕርካታን የተመለከተ ጥናት አድርጓል፡፡ ከጥቅምት 15 እስከ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. በተካሄደው ጥናት ከ1,139 መልስ ሰጪዎች መረጃ የተሰበሰበ ሲሆን፣ ውጤቱ የተገልጋዮች ዕርካታ በአማካይ ከ75 በመቶ በላይ እንደሆነ ማሳየቱ ተገልጿል፡፡

ጥናቱ የተካሄደው በፍርድ ቤቶች ግቢ ውስጥ በመገኘት ተገልጋዮች ጉዳያቸውን ፈጽመው ሲወጡ፣ በዕለቱ የነበራቸውን ቆይታ አስመልክቶ በሰጡት ምላሽ ላይ ተመሥርቶ መሆኑን አጥኚዎቹ አስታውቀዋል፡፡ መልስ ሰጪዎቹ ስለፍርድ ቤቶች አገልግሎት ያላቸው ጥቅል ዕይታ፣ የቀድሞ ትዝታና በግል ያዳበሩትን አመለካከት በምላሻቸው ውስጥ እንዳልገባ ተገልጾ፣ ይህም መዘንጋትን ለማስወገድ እንዳስቻለ ተነግሯል፡፡

- Advertisement -

ከጥናቱ ተሳታፊዎች ውስጥ 34 በመቶውን የሚይዙት ተከሳሾችና ከሳሾች ሲሆኑ፣ ጠበቃዎች፣ ምስክሮች፣ ዓቃቢያነ ሕግ፣ መረጃና ሰነድ ለማግኘት የመጡ ተገልጋዮችና ሌሎችም እንደተሳተፉበት ታውቋል፡፡

በአምስት ምድቦች የቀረበው የጥናቱ ግኝት ሥነ ምግባርና ገለልተኝነት፣ ተደራሽነትና ግልጽነት፣ የአገልግሎቱ ውጤታማነት፣ ቅልጥፍና፣ ተገማችነት፣ ባለፉት ሦስት ዓመታት የፍርድ ቤቶች አፈጻጸምና ፍርድ ቤት የመጡበት ጉዳይ የመሳካት ሁኔታን ተመልክቷል፡፡ አጥኚዎቹ እንደሚያስረዱት በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥቅም ላይ በሚውለው የዕርካታ ደረጃ ምደባ መሠረት፣ የዕርካታ ዝቅተኝነትን የሚያሳየው ትንሹ ገደብ 75 በመቶ ሲሆን፣ ከዚህ በታች የሆኑ ግኝቶች መሻሻል የሚገባቸው ናቸው፡፡

የተጠቃሚዎች በእኩልነት መስተናገድ፣ ዳኛ ወይም ችሎቱ ጉዳዩን በትህትና፣ በአክብሮትና በሚዛናዊነት የመስማት ደረጃ፣ የፍርድ ቤቶች የደኅንነት ደረጃ፣ እንዲሁም የፍርድ ቤት ሬጅስትራር በትህትና ማስተናገድ የሚሉት ዘርፎች ከ80 በመቶ በላይ የተገልጋይ ዕርካታ ከተገኘባቸው ዘርፎች መካከል መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ከ75 በመቶ በታች የሆነ የዕርካታ መጠን የተገኘባቸውና መሻሻል የሚፈልጉ ዘርፎች ተብለው ከተጠቀሱት መካከል ደግሞ፣ ማስረጃና ክርክሮችን መርምሮ ውሳኔ የመስጠት ሒደት፣ ማስረጃና ክርክርን የሚመጥን ውሳኔ ማግኘት፣ የአገልግሎት ቅልጥፍና፣ እንዲሁም የፍትሐ ብሔር ጉዳዮችን በዕርቅና በድርድር እንዲያልቅ ዕድል የመስጠት ይገኙበታል፡፡

በተጨማሪም በጥናቱ ላይ የተሳተፉ መልስ ሰጪዎች ባለፉት ሦስት ዓመታት በፍርድ ቤቶች ያለውን የአገልግሎት ሁኔታ እንዲመዝኑ የተጠየቁ ሲሆን፣ ከተሳታፊዎቹ ውስጥ 46 በመቶው ‹‹አሁን የሥነ ምግባር ጉድለት ቀንሷል›› የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ካለፉት ሦስት ዓመታት አንፃር ፍርድ ቤቶቹ አሁን ያላቸውን አፈጻጸም ውጤታማነት በተመለከተም 50 በመቶው ‹‹የተሻለ ነው›› ያሉ ሲሆን፣ አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተም 52 በመቶ ተሳታፊዎች የተሻለ አገልግሎት እንዳለ ተናግረዋል፡፡

የእነዚህ ግኝቶች አማካይ የተገልጋዮች ዕርካታ ከ75 በመቶ በላይ መሆኑን እንደሚያሳይ ተገልጿል፡፡ ጥናቱ ይፋ በተደረገበት ‹‹የፌዴራል ዳኝነት አሁናዊ ሁኔታና የወደፊት ዕይታ›› በተሰኘውና የካቲት 6 ቀን 2014 ዓ.ም. በተካሄደው ዓመታዊ መድረክ ላይ፣ የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን ክንውንና ዕቅድ ሪፖርት ያቀረቡት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ፣ በጥናቱ በተገኘው ውጤት ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል፡፡

ፕሬዚዳንቷ ባለፉት ሦስት ዓመታት በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ነፃነት፣ ገለልተኝነትና ተጠያቂነት እንዲኖር ጥቂት የማይባሉ ዕርምጃዎች መወሰዳቸውን ገልጸው፣ ከዕርምጃዎቹ መካከል የፍርድ ቤቶች በጀት በቀጥታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ እንዲፀድቅ መደረጉ አንዱ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ ይህ ዕርምጃም ሕገ መንግሥታዊርዓቱንማስጠበቅ ባሻገር የፍርድ ቤቱን ፍላጎት ለማስረዳት፣ እንዲሁም በተከታታይ ዓመታት የፍርድ ቤቱ በጀት 40 በመቶ በላይ እንዲያድግ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

የፌዴራል ርድ ቤቶች አዋጅና የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ አዋጅ ተሻሽለው መውጣታቸው፣ እንዲሁም እነዚህ ሕጎች ተፈጻሚ እንዲሆኑ የሚያደርጉ 22 ያህል ደንብና መመርያዎች እንዲፀድቁ መደረጋቸው፣ ወይም በመፅደቅደት ላይ መሆናቸው የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን የዳኝነት ነፃነት፣ ገለልተኝነትና ተጠያቂነትን ለማጠናከር ዕገዛ እንዳደረገ ወ/ሮ መዓዛ ገልጸዋል፡፡

ፕሬዚዳንቷ አክለውም፣ ‹‹የዳኞችና የፍርድ ቤቱ ገለልተኝነትና ነፃነት ባለፉት ሁለት ዓመታት በፍርድ ቤቱ በተሰጡ ውሳኔዎች የታዩ ናቸው›› ካሉ በኋላ፣ በገለልተኛ ተቋም የተጠናው የተገልጋዮች ዕርካታ ጥናትም ይኼንን ማሳየቱን ጠቅሰዋል፡፡

ጥናቱ በቀረበበት መድረክ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች በበኩላቸው፣ ግኝቱ የተገልጋዮች ዕርካታ በአማካይ ከ75 በመቶ በላይ እንደሆነ ማመላከቱ ላይ ጥያቄ አንስተዋል፡፡ የውይይቱ ተሳታፊ የሆኑ የሕግ ባለሙያ፣ የጥናቱ ውጤት 75 በመቶ የሆነው አስፈላጊ ቢሆኑም፣ የዳኝነቱን ይዘት መሠረታዊ የማያደርጉ ዘርፎች ላይ ከፍተኛ ውጤት መገኘቱ፣ አጠቃላዩን ውጤት ከፍ እንዳደረገው ጠቁመዋል፡፡ ወደ ችሎት በቀላሉ መግባት 87 በመቶ፣ ወደ ፍርድ ቤት በቀላሉ መግባት 93 በመቶና በፍርድ ቤት ሠራተኞች በትህትና መስተናገድ 83 በመቶ የሆኑ ውጤቶች መገኘታቸውን በማሳየነት አውስተዋል፡፡

በአንፃሩ ለዳኝነት ሥርዓቱ መሠረት የሆኑ ነጥቦች ላይ ዝቅተኛ ውጤት እንዳለ የጠቆሙት የሕግ ባለሙያው፣ ማስረጃና ክርክርን የሚመጥን ውሳኔ ማግኘት 56 በመቶ፣ ማስረጃና ክርክሮችን መርምሮ ውሳኔ የመስጠት ሒደት 63 በመቶ፣ እንዲሁም የአገልግሎት ቅልጥፍና 63 በመቶ መሆናቸውን ማሳያ አድርገዋል፡፡

በተጨማሪም የግል ልምዳቸውን በመጥቀስ በግልጽ ችሎት የመስተናገድ ደረጃ 86 በመቶ ደርሷል መባሉ ላይ ያላቸውን ጥርጣሬ ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአምስተኛ ዓመት ተማሪ መሆኑን የገለጸ ተሳታፊ በበኩሉ፣ የጥናቱ ተሳታፊዎች ከሦስት ዓመት በፊት የነበረውን የፍርድ ቤት አግልግሎት አሁን ካለው ጋር እንዲያነፃፅሩ መደረጋቸው ላይ ጥያቄ አንስቶ፣ ተሳታፊዎቹ ይኼንን ለመመለስ ከሦስት ዓመት በፊት ጀምሮ በፍርድ ቤት ተገኝነተው የነበሩ መሆን እንዳለባቸው አስረድቷል፡፡ ‹‹ከሦስት ዓመት በፊት በፍርድ ቤት ባለጉዳይ የነበሩ ሰዎች አሁንም አሉ ማለት ነው?›› የሚል ጥያቄ አቅርቧል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ዳኞች የፍርድ ሒደቱን በሚፈለገው መንገድ ላለማከናወናቸው ገፊ የሆኑ ምክንያቶች በጥናቱ ላይ ያልቀረቡ መሆናቸውን አስረድቷል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሰለሞን አረዳ ማስረጃና ክርክርን የሚመጥን ውሳኔ ማግኘት በሚለው 56 በመቶ የሚሆን ውጤት መገኘቱ፣ ከፍርድ ቤት ባህሪ አንፃር ሁለቱንም ተከራካሪ ወገኖችን ማስደስት የማይቻል በመሆኑ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ በአሜሪካ ፍርድ ቤቶች ላይ ያለው የተገልጋዮች ዕርካታ መጠን 40 በመቶ መሆኑን በማውሳትም፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በውጤቱ ደስተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡                                                                                                 

ጥናቱን ያደረገው የአብኮን ዳይሬክተር አቶ ሙሉ ተካ መልስ ሰጪዎች ከሦስት ዓመት በፊት የነበረውን ሁኔታ እንዲያነፃፅሩ የተደረገው፣ ከሦስት ዓመት በፊት በፍርድ ቤት በነበሩ ሰዎች ተመርጠው መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በጥናቱ በዳኞች ላይ ጫና ያሳደሩ ምክንያቶች ቢካተቱም፣ በጊዜ እጥረት ምክንያት ለማቅረብ አለመቻሉ ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...