Friday, June 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለአምስት መቶ ወጣቶች የሥራ ዕድል የሚፈጥር የሰባት ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ

ለአምስት መቶ ወጣቶች የሥራ ዕድል የሚፈጥር የሰባት ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ

ቀን:

አምስት መቶ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የሰባት ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት ይፋ ማድረጉን አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉውሽንስ አክሲዮን ማኅበር (አቴሶአ) አስታወቀ፡፡

ወጣቶች በማኅበሩ ሥር ከሚገኙ ሠራተኞች ጋር ግንኙነት ፈጥረው የተለያዩ ተቋሞች ምርትና አገልግሎታቸውን እንዲሸጡ በማድረግ አንድም ተቋሙን ተጠቃሚ የሚያደርጉበት፣ በሌላ መልኩ ደግሞ ራሳቸውን የሚቀይሩበት ፕሮጀክት መሆኑን አክሲዮን ማኅበሩ አስታውቋል፡፡

ማኅበሩ ይህንን ያስታወቀው ማክሰኞ የካቲት 8 ቀን 2014 ዓ.ም. የሰባት ሚሊዮን ፕሮጀክቱን ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው፡፡ በፕሮጀክቱ 500 ወጣቶች ኢንተርኔትን ተጠቅመው የገበያ ትስስርን የሚፈጥሩ ይሆናል ብሏል፡፡

የአቴሶአ ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳንኤል በቀለ እንደገለጹት፣ በኢትዮጵያ ኢንተርኔትን ተጠቅሞ የተለያዩ ቢዝነሶችን መሥራት የተለመደ አለመሆኑን፣ በአሁኑ ወቅትም ማኅበሩ ባደረገው ጥናት መሠረት ከ50 በላይ የሚሆኑ ፕሮጀክቶች ከፍተኛ የሆነ ገቢ የሚያስገኙ ሆነው ተገኝተዋል፡፡

በተለይም በኢትዮጵያ ኢንተርኔትን ለሥራ በማዋል ረገድ ላይ ‹‹ይበል!›› የሚያሰኝ ሥራ እንዳልተሠራ የገለጹት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ይህንንም ችግር ወደኋላ በመተውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ቦታ ላይ የሚገኙ አገሮችን ተሞክሮ በመውሰድ ዘርፉን ማሳደግ እንደሚስፈልግ ገልጸዋል፡፡

ሰዎች ባሉበት ቦታ ሆነው የራሳቸው የቢዝነስ ባለቤት መሆን እንደሚችሉ፣ ማኅበሩም በ2014 ሒሳብ ዓመት ላይ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ ወጣቶችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ የሚሆኑበት መንገድ እየፈጠረ እንደሚገኝ አቶ ዳንኤል አስረድተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም በተለያዩ ቦታዎች ላይ የዲጂታል ቴክኖሎጂ እየተስፋፋ መሆኑን፣ ይህንንም በአሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉውሽንስ ላይ ይበልጥ ለማሳለጥ ወጣቶች በስልካቸውም ሆነ በአካል አካባቢያቸው ከሚገኙ የዘርፉ ተዋናዮች በማነጋገር ማኅበሩ ላይ ምርትና አገልግሎታቸውን እንዲሸጥ በማድረግ ተጠቃሚ የሚሆኑበት መንገድ ይፈጠራል ሲሉ አብራርተዋል፡፡  

ማኅበሩም በይበልጥ የሚሠራው በአዲስ አበባ ከተማ መሆኑን የተናገሩት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ምን ያህል ሸማችና ሻጭ አለ? የሚለውን ለማወቅ ጥናት መደረጉን፣ በዚህም ክልሎች ተጠቃሚ የሚሆኑበት መንገድ እንደሚፈጥር አክለው ገልጸዋል፡፡

በአሥር ዓመታት ውስጥ በርካታ ፕሮጀክቶችን ለማሳካት ዕቅድ መያዙን፣ በ2030 ዓ.ም. ከአምስት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎችን የሥራ ዕድል እንዲያገኙ ማለሙን በመግለጽ፣ የሥራ አጥ ቁጥርን በተወሰነ መልኩ መቅረፍ ይቻላል ብለዋል፡፡

አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉውሽንስ አክሲዮን ማኅበር ከ57 በላይ ሠራተኞች፣ 12 የቦርድ አባላት ያሉት ሲሆን፣ በኢትዮጵያ በ11 የቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ለመሥራት ዕቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ