Saturday, June 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትመተግበር የተሳነው የክለቦችና ብሔራዊ ቡድን ጥምረት

መተግበር የተሳነው የክለቦችና ብሔራዊ ቡድን ጥምረት

ቀን:

በካሜሩን አፍሪካ ዋንጫ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) ወደ አገር ቤት ከተመለሰ ሳምንታት ተቆጥሯል፡፡ ከምድቡ ማለፍ የተሳነው ብሔራዊ ቡድኑ፣ በምድብ ጨዋታው በኳስ ቁጥጥር ቁጥራዊ መረጃ የተሻለ የሚመስለው ብሔራዊ ቡድኑ የተክለ ሰውነትና ወደ ፊት አጥቅቶ የመጫወት እንዲሁም ግብ ማስቆጠር አለመቻሉ በዋነኛነት እንደ ችግር ሲነሳበት የነበረ ጉዳይ ነው፡፡

በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ገና በመጀመርያው የምድብ ጨዋታ የተሰናበተው የዋሊያዎቹ ስብስብ በጨዋታ እንቅስቃሴ ላይ የተለያዩ አስተያየቶችን ሲያስተናግድ ቆይቷል፡፡ በዚህም ምክንያት የብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ፣ የክለቦች መዋቀራዊ ችግር፣ የተጫዋቾች ልምድ ማጣት፣ የሊጉ ኋላ ቀር መሆነና በኢትዮጵያ ምድብ ላይ የነበሩ አገሮች ወቅታዊ አቋም የተሻለ መሆን ዋሊያዎቹን በውድድሩ እንዳይቆዩ ፈትኗችዋል የሚሉ ምክንያቶች ቀርበዋል፡፡

የካቲት 6 ቀን 2014 ዓ.ም. የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጅራ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ከነረዳቶቻቸው፣ ከቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ 16 ክለቦች ጋር ሆነው በካሜሩን ስለነበራቸው ቆይታ  በድሬዳዋ ውይይት አድርገዋል፡፡

የክለቦቹ ቡድን መሪዎች፣ ዋና አሠልጣኞች እንዲሁም ምክትል አሠልጣኞች በተገኙበት መድረክ የብሔራዊ ቡድን አሠልጣኙ ውበቱ አባተና የአካል ብቃት ባለሙያ ዘሩ በቀለ (ዶ/ር) እንዲሁም ሌሎች ባለሙያዎች ብሔራዊ ቡድኑ በካሜሩን ስለነበረው አጠቃላይ እንቅስቃሴ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

በሪፖርቱም ቡድኑ ስለነበረበት የአካል ብቃትና ቴክኒካዊ ችግሮች ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ ከዋና አሠልጣኙ ባሻገር ክለቦችም በጋራ መሥራት ስላለባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሸን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

እንደ ፕሬዚዳንቱ አስተያየት ከሆነ የተጫዋቾች አሠላለፍ ወሳኔ ላይ የመግባት ሥልጣን የአሠልጣኙ ቢሆንም ፌዴሬሽኑ ብሔራዊ ቡድኑ ላይ  የሚመለከተውን ችግር እንዴት መፍታት እንዳለበት መጠየቅ እንዲሁም የመፍትሔ አቅጣጫ ማስቀመጥ ሒደት ላይ መሳተፍ ይኖርበታል ሲሉ ያስረዳሉ፡፡

በመድረኩ ተጫዋቾች በየጨዋታው ላይ ስላደረጉት ሙሉ እንቅስቃሴ የሚያብራራ ቁጥራዊ መረጃዎች ለክለቦች የቀረበ ሲሆን፣ ክለቦቸም በአደረጃጀታቸው ውስጥ የተጫዋቾችን አካላዊ ብቃት እንዲሁም የአመጋገብ ሥርዓትን የሚከታተሉ ባለሙያዎች በቡድን ውስጥ ማካተት እንደሚያስፈልግ ተጠቅሷል፡፡

የብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ከዋና አሠልጣኙ ጋር ቢበዛ ለዘጠኝ ቀናት  አብረው ቆይታ ሊያደርጉ እንደሚችሉ የጠቆሙት ፕሬዚዳንቱ ክለቦች የተጫዋቾቻቸውን አቅም ከማሳደግ አንፃር የአንበሳውን ድርሻ መወሰድ እንደሚገባቸው ተነስቷል ብለዋል፡፡ በተለይ ብሔራዊ ቡድን ኳስ ሲያደራጅ ችግር እንዳለበትና ኳሶቹን ወደ ኋላ መመለስ ማብዛቱ ሲያስተቸው  ከርሟል፡፡

ከዚህም ባሻገር አሠልጣኙ የዲሲፕሊን ግድፈት ያለባቸውን ተጫዋቾች አሠልፏል በሚልና በውድድሩ ላይ በአጠቃላይ ቡድኑ የነበረውን እንቅስቃሴ ተከትሎ ፌዴሬሽኑ ሊያሰናብት ይችላል የሚሉ ወሬዎች ቢደመጡም ፌዴሬሽኑ አሠልጣኝ ማሰናበተው በምትኩ አዲስ ማምጣት ብሔራዊ ቡድን አይለውጥም ሲሉ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡

‹‹አሠልጣኝ በመቀየያር ብሔራዊ ቡድኑን ውጤታማ ማድረግ ይቻላል ብዬ አላምንም፡፡ ፌዴሬሽኑ ከአሠልጣኙ ጋር የተፈራረመውን ውል በአንዴ ቀዶ የሚያሰናብትበትም አሠራር የለም፡፡ በዚህም መሠረት አሠልጣኙ ያላቸውን ውል እየተመለከትንና እየገመገምን እንቀጥላለን፤›› ሲሎ አቶ ኢሳያስ ያክላሉ፡፡

በዚህም መሠረት አሠልጣኙ የሰባት ወር ውል እንደሚቀራቸውና ከወር በኋላ የወዳጅነት ጨዋታ እንደሚያደርጉ አልሸሸጉም፡፡

ምንም እንኳ በድሬዳዋ በተደረገው ውይይት የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር በጋራ ሆነው እየተደጋገፉ ለመሥራት ቢስማውም ክለቦቹ ግን ብሔራዊ ቡድኑ ባመጣው ውጤት ተወቃሽ መሆነ የለብንም የሚል አስተያየት ሲሰጡ ይስተዋላል፡፡

በፕሪሚየር ሊጉ እየተሳተፉ የሚገኙት ክለቦች የክለባቸውን መዋቅር መቀየር እንዳለባቸውና ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ማደራጀት እንዳለባቸው በተደጋጋሚ ቢነሳም ከመንግሥታዊ አሠራር ግን መነጠል አልቻሉም፡፡

ክለቦቹ ወጥ የሆነ አደረጃጀት ስለሌላቸውና ዘመናዊውን የክለብ አደረጃጀት አለመከተላቸውን ተከትሎ በዋና ቡድን ላይ ብቻ ተመሥርተው ተተኪዎችን ከስር ማሳደግ አለመቻላቸው ይነሳል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም በብሔራዊ ቡድኑ ላይ መፍታት ያልተቻለውን ችግርና ቡድኑ በአፍሪካ መድረክ ላይ ያሳየው የዋዠቀ አቋም ‹‹የሊጉ ነፀብራቅ ውጤት ነው›› የሚሉ በርካቶች ናቸው፡፡ በየዓመቱ ረብጣ ገንዘብ የሚያፈሱት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች የገንዘብ መጠንና አደረጃጀታቸው መመጣጠን እንዳልቻል ሲገለጽ ከርሟል፡፡ 

በአክሲዮን ማኅበር ከተደራጁ ሁለት ዓመት የሆናቸው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በቀጣይ ዘመናዊ አደረጃጀትን መከተል እንደሚገባቸው የሼር ካምፓኒው ፕሬዚዳንት መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ ከሪፖርተር ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል፡፡ እንደ መቶ አለቃ ፍቃደ አስተያየት ከሆነ ክለቦቹ በካምፓኒው ሥር ለመተዳደር የራሳቸው ቢሮ፣ ኦዲተር፣ የፋይናንስ ባለሙያና ሌሎች መሠረታዊ የተቋም መገለጫዎችን በአደረጃጀታቸው ውስጥ ማከተት እንዳለባቸው አንስተዋል፡፡ በቀጣይ ክለቦችም በአዲስ የአደረጃጀት መዋቅር እንደሚመጡ ይጠበቃል፡፡

 

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አያሌ የውኃ “ጠርሙሶች”ን በጫንቃ

መሰንበቻውን በአይቮሪ ኮስት መዲና አቢጃን የምትኖር አንዲት ሴት፣ በሚደንቅ...

ወልቃይትን ማዕከል ያደረገው የምዕራባዊያን ጫና

በትግራይ ክልል የተከሰተው የዕርዳታ እህል ዘረፋ የዓለም አቀፍ ተቋማት...

ከቀጣዩ ዓመት በጀት ውስጥ 281 ቢሊዮን ብሩ የበጀት ጉደለት ነው ተባለ

ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት...