Wednesday, February 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበታላቁ የህዳሴ ግድብ የተሳካ ኃይል የማመንጨት ሙከራ ተደረገ

በታላቁ የህዳሴ ግድብ የተሳካ ኃይል የማመንጨት ሙከራ ተደረገ

ቀን:

መንግሥት በቀናት ውስጥ ለሕዝብ ይፋ ያደርጋል ተብሏል

ኢትዮጵያውን በጉጉት የሚጠብቁት የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመጀመርያ ዙር የሙከራ ኃይል ማመንጨት በተሳካ ሁኔታ መካሄዱ ታወቀ፡፡ ይህንን የኤሌክትሪክ ማመንጨት ሥራ ስኬትም መንግሥት በቀናት ውስጥ ለሕዝብ እንደሚያበስር ይጠበቃል፡፡

ታላቁ የህዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ከጀመረ ቀናት እንደተቆጠሩ የተረጋገጠ ቢሆንም ለሕዝቡ ይፋ እስኪደረግ በሚል መረጃውን ለማሠራጨት እንዳልተፈለገ  ሪፖርተር ከታማኝ ምንጮች ያገኘው መረጃ ያሳያል፡፡

ላለፉት 11 ዓመታት በግንባታ ላይ የቆየውና ለሁለት ዙሮች የውኃ ሙሌት ሥራው ደረጃ በደረጃ የተከናወነው ታላቁ የህዳሴ ግድብ፣ የሙከራ ኃይል ለማመንጨት ከተሰናዱት ሁለት ተርባይኖች በአንደኛው የሙከራ ኃይል እንዳመነጨ ምንጮቹ አረጋግጠዋል፡፡

ባለፉት ሁለት የክረምት ወቅቶች ውኃ በያዘው የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ተርባይኖችን፣ በውኃ የመሞከር ሥራ መጀመሩን ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ሲገለጽ የቆየ ሲሆን፣ ሪፖርተር ይህንኑ ጉዳይ ለማጣራት ባደረገው ጥረት፣ መንግሥት በጉዳዩ ላይ በቅርቡ መግለጫ ይሰጣል የሚል ምላሽ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት አግኝቷል፡፡

ሪፖርተር ከምንጮች እንዳረጋገጠው ከግድቡ የመነጨው ኃይል ከጣና በለስ ሰብስቴሽን ጋር እንደተገናኘ የታወቀ ሲሆን፣ ይህም ከታቀዱት ሁለት መስመሮች አንደኛው ነው፡፡ ሌላኛው መስመር በዋናነት በግንደበረት፣ ሆለታ መስመር የሚሄደው ነው፡፡ በቅርቡ መንግሥት ለሕዝብ ይፋ የሚያደርገው  ከጣና በለስ የኃይል ማከፋፈያ ሰብስቴሽን ጋር የተገናኘው የኃይል ማመንጨት ሙከራ እንደሆነ ታውቋል፡፡

ኃይል ያመነጫሉ የተባሉት ሁለት ተርባይኖች የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ዝግጁ እንደተደረጉ የታወቀ ሲሆን፣ ለጊዜው ሙከራ የተደረገበት አንደኛው ተርባይን ነው፡፡ ይህም ተርባይን 375 ሜጋ ዋት ኃይል ያመነጫል፡፡ የቀሪው ተርባይን የኃይል ሙከራ የውኃ ሙሌቱ በበቂ ሆኖ ሲከናወን የሚሞከር ይሆናል ተብሏል፡፡

‹‹የኃይል ማመንጨት ሙከራው ከተረጋገጠ በኋላ ለጊዜው ቆሟል፤››  ያሉት ምንጮች፣ ሆኖም በቀናት ውስጥ  የምርቃት ሥነ  ሥርዓት ይፋ ሲደረግ የኃይል ማመንጨት ሥራው እንደሚቀጥል፣  ለዚያም የሚሆን የዝግጅት እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል፡፡

ግድቡ 2012 .ም.  ክረምት ወራት ቁመቱ ከባህር ጠለል በላይ 565 ሜትር ላይ ደርሶ 4.9 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ውኃ መያዙ የሚታወስ ሲሆን፣ በተጠናቀቀው ዓመት በተከናወነው ሁለተኛ ዙር ሙሌት መጠን በአኃዛዊ መንገድ ባይገለጽም ሙሌቱ ግን በስኬት መከናወኑ እንደተገለጸ ይታወሳል፡፡

ኢትዮጵያ በ2003 ..  የታላቁ ህዳሴ ግድብን መገንባት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ ግብፅና ሱዳን ተቃውሞአቸውን ሲገልጹ የቆዩ ሲሆን፣ በተለይ ግብፅ ማስፈራራቷንና ሥጋቷን በተለያዩ መንገዶች እያሰማች ትገኛለች፡፡ ግብፅና ኢትዮጵያ ሱዳንን ጨምሮ ላለፉት አሥር ዓመታት ያህል በዓባይ ወንዝ ጉዳይ ላይ ከስምምነት ለመድረስ ሲደራደሩ ቢቆዩም፣ እስካሁን ድረስ ሦስቱንም አገሮች የሚያስማማ ሁሉን አቀፍ መግባባት ላይ መድረስ አልተቻለም።

ወደ ኃይል ማመንጨት ምዕራፍ በመሸጋገር ላይ የሚገኘው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያን በብዙ መንገዶች የሚቀይር ፕሮጀክት መሆኑብዙ የተነገረለት ሲሆን፣ 60 በመቶ የሚሆነው ሕዝቧ መደበኛ የኤሌክትሪክ ብርሃን በማያገኝባት ኢትዮጵያ ግድቡ የሚያመነጨው 6,000 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል ትልቅ አገልግሎት እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በወቅታዊ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የቀረበላቸውን ምክረ ሐሳብ እያደመጡ ነው]

ችግሩ ምን እንደሆነ በትክልል ለይተነዋል ግን ግን ምን? በይፋ መናገር አልነበረብንም። ለምን? ችግሩን...

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤትና እንደምታው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የትምህርትን...

ንግድ ባንክ ከቪዛና ማስተር ካርድ ጋር ተደራድሮ ያስጀመረው የገንዘብ ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂና ፋይዳው

ከውጭ ወደ አገር በሕጋዊ መንገድ የሚላክ ገንዘብ (ሬሚታንስ) መጠን...

ይኼ አመላችን የት ያደርሰን ይሆን?

እነሆ ከፒያሳ ወደ ካዛንቺስ። ‹‹አዳም ሆይ በግንባር ወዝ ትበላለህ››...