Monday, December 4, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የአንበሳ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሹመት ፀደቀ 

ተዛማጅ ፅሁፎች

አንበሳ ባንክ አቶ ዳንኤል ተከስተ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እንዲያገለግሉት  ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያቀረበው የሹመት ጥያቄ እንደፀደቀለት አስታወቀ፡፡

ከአንበሳ ባንክ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ አቶ ዳንኤል ባለፉት ስድስት ወራት የባንኩ ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

በአንበሳ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥያቄ መሠረት ለባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚነት የታጩትን የአቶ ዳንኤል የሹመት ጥያቄ ሲመረምር የቆየው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የካቲት 10 ቀን 2014 ዓ.ም. በጻፈው ደብዳቤ የአቶ ዳንኤል ሹመትን ማፅደቁን አመልክቷል፡፡

አቶ ዳንኤል በኢንዱስትሪው ውስጥ ከ21 ዓመታት በላይ ያገለገሉና የካበተ ልምድ ያላቸው መሆኑንና በዚህ የአገልግሎት ዘመናቸው በተለይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ውስጥ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ መሥራታቸውን አንበሳ ባንክ ጠቅሷል፡፡

በአንበሳ ባንክ ውስጥ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እስከተሾሙበት ጊዜ ድረስ የባንኩ የሪስክና ኮምፕሊያንስ ማኔጅመንትና የዓለም አቀፍ ባንክ አገልግሎት ዲፓርትመንቶች ዳይሬክተር በመሆን ሠርተዋል፡፡

የቢዝነስ ስትራቴጂ ማኔጅመንትና የሞደርናይዜሽን ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን ማገልገላቸውን የሚያመለክተው የባንኩ መረጃ፣ ባንኩ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ አቶ ዳንኤል አምስተኛው ዋና ሥራ አስፈጻሚ መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡

አቶ ዳንኤል ከስድስት ወራት በፊት ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ባንኩን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ጌታቸው ሰለሞን ኃላፊነታቸውን በገዛ ፈቃዳቸው ከለቀቁ በኋላ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በአገሪቱ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከ15 ዓመታት በላይ የቆየ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የተከፈለ ካፒታሉን ወደ 2.5 ቢሊዮን ብር ማድረስ መቻሉን የባንኩ መረጃ ያመለክታል፡፡

12,346 ባለአክሲዮኖች ያሉት አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ በመላ አገሪቱ ያሉት ቅርንጫፎች ቁጥር 278 ደርሷል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች