Thursday, June 8, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

አዋሽ ባንክ የሚሰጣቸውን የተለያዩ አገልግሎቶች ‹‹አዋሽ ብር›› በሚል ስያሜ መስጠት ጀመረ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

አዋሽ ባንክ የአዋሽ ብር የሞባይል ባንኪንግና የወኪል አገልግሎትን ‹‹አዋሽ ብር›› በሚል የንግድ ስያሜ መስጠት መጀመሩን ይፋ ሲያደርግ፣ የባንኩ ጠቅላላ የሀብት መጠንም ከ150 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን አመለከተ፡፡

ባንኩ ‹‹አዋሽ ብር››ን ይፋ ባደረገበት ፕሮግራም ላይ እንዳስታወቀው፣ ‹‹አዋሽ ብር›› የባንኩን የሞባይል ባንኪንግና የወኪል ባንክ አገልግሎቶችን የሚወክል የንግድ ስያሜ ነው፡፡ በዚህ የንግድ ስያሜ ሥር ለደንበኞችና ሌሎች ተጠቃሚዎች የአዋሽ ብር መተግበሪያን በመጠቀም ወይም የአዋሽ ብር ወኪሎች ጋር በመቅረብ የሒሳብ እንቅስቃሴዎችን መከታተልና ማስተላለፍ የሚያስችል መሆኑን የባንኩን ፕሬዚዳንት አቶ ፀሐይ ሽፈራው ገልጸዋል፡፡

በዚህ መተግበሪያ ከሚሰጡ አገልግሎቶች መካከል በአዋሽ ብር ወኪሎችና ኤቲኤም ገንዘብ ወጪ ማድረግና የተለያዩ ክፍያዎችን መፈጸም የሚችል መሆኑንም አክለዋል፡፡ የአዋሽ መተግበሪያን በመጠቀም እንደ የትራፊክ ቅጣት፣ የአየር መንገድ ትኬት ክፍያ፣ የዲኤስ ቲቪ፣ የካናል ፕላስ፣ የትምህርት ቤት ክፍያዎችን መክፈል የሚያስችል ሆኖ የተዘጋጀ ነው፡፡

ሞባይል ለመሙላትም በዚህ መተግበሪያ መጠቀም የሚቻል ሲሆን፣ ሌሎች ክፍያዎችንም በማካተት ‹‹አዋሽ ብር›› አገልግሎቱን የሚያሰፋ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

እንዲህ ካሉት አገልግሎቶች ሌላ ደንበኞች ወደ ቅርንጫፉ መሄድ ሳያስፈልጋቸው በአቅራቢያቸው በሚገኙ የአዋሽ ብር ወኪሎች ሒሳብ መክፈት፣ ገንዘብ ገቢና ወጪ ማድረግ የሚቻል መሆኑን አቶ ፀሐይ ተናግረዋል፡፡

‹‹አዋሽ ብር›› አጠቃቀሙ ቀላልና አመቺ ሆኖ የቀረበ መሆኑን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ በእንግሊዝኛ፣ በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ፣ በትግርኛ፣ በአፋርኛና በሶማሊኛ ቋንቋዎች አገልግሎት የጀመረ ሲሆን፣ ወደፊትም ሌሎች ቋንቋዎችን እንደሚጨምሩ አስታውቀዋል፡፡

ባንኩ ዘመናዊ የባንክ አገልግሎትን ለማስፋት የኤቲኤም ማሽኖችን ከሁለት እጥፍ በላይ ለማድረስ መዘጋጀቱንና በአሁኑ ወቅትም የአንድ ሺሕ ኤቲኤሞች ግዥ ፈጽሞ ወደ አገር በማስገባት ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡ አዋሽ ባንክ በአሁኑ ወቅት በ456 ኤትኤሞች አገልግሎት እየሰጠ ነው፡፡

አዋሽ ባንክ አጠቃላይ የሀብት መጠኑን ከ150 ቢሊዮን ብር በላይ ማድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የባንኩ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከ110 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን ያመለከቱት አቶ ፀሐይ፣ ለተለያዩ የቢዝነስ ዘርፎች የሰጠው ብድርም ከአንድ ቢሊዮን ብር መሻገሩን አመልክተዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ከ680 በላይ ቅርንጫፎች ያሉት አዋሽ ባንክ፣ የተቀማጭ ሒሳብ ደንበኞቹን ቁጥር ከ6.8 ሚሊዮን በላይ ማድረሱንም አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች