Saturday, June 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅድብብቆሽ

ድብብቆሽ

ቀን:

አንድ ስኮትላንዳዊና አንድ እንግሊዛዊ በባቡር ወደ ታስማንያ እየተጓዙ ነበር፡፡ መሃላቸው አንዲት ቆንጆ ሴት ተቀምጣለች፡፡ ባቡሩ በዋሻ ውስጥ ማለፍ ስለነበረበት ወደዚያ ሲገባ ድቅድቅ ጨለማ ወረሰው፡፡ የጥንት ባቡር ስለሆነም መብራት አልነበረውም፡፡ ወዲያውኑ የመሳም ድምፅ ተሰማና ጥፊ ተከተለ፡፡

ባቡሩ ከዋሻው ሲወጣ ሴቲቱና ስኮትላንዳዊው ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ ተረጋግተው ተቀምጠው ሳለ እንግሊዛዊው ግን በጥፊ የተቃጠለ ፊቱን እያሻሸ ነበር፡፡ ለርሱ የመሰለውም ስኮትላንዳዊው ሴቲቱን ስለሳማት ተቆጥታ የሰነዘረችበት ጥፊ እርሱ ላይ በስህተት ያረፈ ነው፡፡ ሴቲቱ በበኩሏ ‹‹እንግሊዛዊው ሊስመኝ ሲሞክር ተሳስቶ ስኮትላንዳዊውን ስለሳመው በጥፊ አቃጥሎታል›› ስትል ገምታለች፡፡ ስኮትላንዳዊው ደግሞ ‹‹ግሩም አጋጣሚ ነው የተፈጠረልኝ፤ ባቡሩ ከፊታችን ያለው ዋሻ ሲገባ የተለመደውን የመሳም ድምፅ አሰማና ያን ሞልፋጣ እንግሊዛዊ አጠናፍረዋለሁ›› እያለ በማሰብ ላይ ነበር፡፡

  • አረፈዓይኔ ሐጐስ ‹‹የስኮትላንዳውያን ቀልዶች›› (2005)
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አያሌ የውኃ “ጠርሙሶች”ን በጫንቃ

መሰንበቻውን በአይቮሪ ኮስት መዲና አቢጃን የምትኖር አንዲት ሴት፣ በሚደንቅ...

ወልቃይትን ማዕከል ያደረገው የምዕራባዊያን ጫና

በትግራይ ክልል የተከሰተው የዕርዳታ እህል ዘረፋ የዓለም አቀፍ ተቋማት...

ከቀጣዩ ዓመት በጀት ውስጥ 281 ቢሊዮን ብሩ የበጀት ጉደለት ነው ተባለ

ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት...