Saturday, September 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልበንባብ ሳምንቱ ጎልቶ የወጣው ‹‹ወመዘክር››

በንባብ ሳምንቱ ጎልቶ የወጣው ‹‹ወመዘክር››

ቀን:

አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ተሰብስበው በተመስጦ አስጎብኚውን ይከታተላሉ፡፡ ከመጠየቅ ይበልጥ ማዳመጥ ልባቸው የፈለገ ይመስላል፡፡ በአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ቅጥር ግቢ የሚጎበኙ ቦታዎች በብዛት ቢኖሩም የተማሪዎች ቀልብ በይበልጥ የተሳበው ግን የኢትዮጵያ ታሪካዊና ጥንታዊ ነገሮችን በያዘው አንደኛው ድርጅት ላይ ነው፡፡

የአገራቸው ታሪክ፣ ሥልጣኔ፣ ዕውቀት የሻቱት እነዚህ ታዳጊዎች አስጎብኚው የሚተረክላቸውን ያለመሰልቸት እየሰሙ መሆኑ ፊታቸው ያስታውቃል፡፡ የመጀመርያዎቹ ከተተረከላቸው በኋላ ሌሎች ተማሪዎች በብዛት እየተተኩ ማዳመጣቸውን ይቀጥላሉ፡፡ አስጎብኚውም ባለመሰልቸት ለተማሪዎች ለጉብኝት የቀረቡትን ታሪካዊ ጽሑፎች ማስረዳቱን ተያይዞታል፡፡ የብዙ ተማሪዎችንና ታዳሚዎችን ቀልብ የሳበው ተቋም በ1936 ዓ.ም. የተመሠረተው አንጋፋው ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ (ወመዘክር) ነው፡፡

ኤጀንሲው ተማሪዎቹና የታዳሚዎችን ቀልብ የተሳበው ታሪካዊ ይዘት ያላቸው የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ያቀረበው ለአራተኛ ጊዜ በተካሄደው የንባብ ሳምንት ላይ ነው፡፡ አራቱንም የንባብ ሳምንት ላይ የተሳተፈው ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ፣ በዘንድሮ ላይም የሥነ ጽሑፍ ሀብቶችንና ፎቶግራፎችን ለጎብኚዎች ክፍት አድርጓል፡፡

የኤጀንሲው የቤተ መዛግብት ባለሙያ አቶ አዛሪያስ ኃይለ ጊዮርጊስ እንደተናገሩት፣ ከሥነ ጽሑፍ ሀብቶች መካከል በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ላይ የተመዘገቡ ይገኙበታል፡፡ አሥራ ሁለቱ የሥነ ጽሑፍ ቅርሶች መካከል የኢትዮጵያ ነገሥታት ከሌሎች አገሮች መሪዎች ጋር የተጻጻፏቸው ደብዳቤዎች እንደሚገኙበት ገልጸዋል፡፡

ለሕዝብ ዕይታ ከቀረቡት የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ውስጥ የኢትዮጵያ ነገሥታት የተጻፏፏቸው ሦስቱ ደብዳቤዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ከአዲስ አበባ ከተማ መመሥረት ዋነኛ ምክንያት እንደሆነ የሚጠቀሰው ፍልውኃ አካባቢና እስከ 1942 ዓ.ም. ድረስ የመዲናቱን ገጽታ የሚያሳዩ ፎቶግራፎች ለሕዝብ እይታ መቅረባቸውን አቶ አዛሪያስ ተናግረዋል፡፡

ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ (ወመዘክር) ለንባብ ቅርብ ከሆኑ ድርጅቶች ቀዳሚው ነው፡፡ በተለይም ታሪካዊ ሁነቶች፣ ጽሑፎችና ሌሎችም እንቅስቃሴዎች ተሰንደው የተቀመጡበት ሥፍራ በመሆኑ ለንባብ ቅርብ መሆኑን ባለሙያው ይገልጻሉ፡፡

ወመዘክር ከጥንት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ የተፈጠሩ ክስተቶችን የሚያሳዩ መዛግብትን፣ መጻሕፍትን፣ ታሪካዊ ደብዳቤዎችን ለጥናትና ምርምር ሥራዎች እንዲውሉ ከሚያመቻቹ ድርጅቶች አንዱ መሆኑን ያብራራሉ፡፡

ድርጅቱ ከንባብ ጋር ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እንደሚሠራ፣ ከዚህም ውስጥ በየክልሎቹ ቤተ መጻሕፍትን በማደራጀት የተለያዩ ድጋፎች እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ለንባብ ሳምንት የቀረቡት የጽሑፍ ሀብቶች ቀደምት ታሪኮችን የሚያሳዩ በመሆኑ፣ ያለውን የታሪክ ክፍተት ለመሙላት እንደሚረዳ፣ ቀደምት አባቶች አገር ለማቆየት ያደረጉትን አስተዋጽኦና ኢትዮጵያ ከሌሎች አገሮች ጋር የነበራትን ግንኙነት የሚያሳዩ በመሆኑ ብዙዎች እየጎበኙት መሆኑን የቤተ መዛግብት ባለሙያው ያስረዳሉ፡፡

የንባብ ሳምንቱ

በአብርሆት ቤተ መጻሕፍት የካቲት 9 ቀን 2014 ዓ.ም. የተጀመረው አራተኛው የንባብ ሳምንት፣ ከ20 በላይ የመጻሕፍት ሻጮችና የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት የመጡ ተከፍለውበታል፡፡

አዘጋጁ የአዲስ አበባ ከተማ ባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ (ባኪቱ) እንደገለጸው፣ በንባብ ሳምንቱ ከ11,000 በላይ ተማሪዎችና የሚመለከታቸው አካላት ጎብኝተውታል፡፡

በንባብ ሳምንቱ መጻሕፍት በቅናሽ ዋጋ የቀረበበት፣ የክፍለ ከተሞች የሥነ ጽሑፍ ውድድር እንደተካሄደ ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትን በመወከል የዩኒቨርሲቲው የፓርትነርሺፕና ምርምር አካዴሚክስ ዘርፍ አማካሪ ሐረገወይን አሰፋ (ፕሮፌሰር) እንደተናገሩት፣ መጽሐፍ የሥነ ልቦና ግንባታን ከማነፅ ረገድ ወደር እንደሌለው፣ አገራዊ ችግሮችንም ለመፍታት ንባብ ቁልፍ ነው፡፡ ለዚህም እንደ ንባብ ሳምንት ዓይነት ንቅናቄዎችን በመፍጠር፣ ማኅበረሰቡ የንባብ ባህል እንዲያዳብር ማገዝ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ባኪቱ ቢሮ ኃላፊ ሒሩት ካሳው (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ንባብ ንቁ ዜጋን ለመፍጠርና ትውልድን ለመገንባት ትልቅ ድርሻ ያለው በመሆኑ፣ የንባብ ሳምንቱ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች በይበልጥ መስፋፋት አለበት ብለዋል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ የንባብ ሳምንት እንደሚካሄድ የገለጹት ኃላፊዋ የሚያነቡ ዜጎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥራቸው እያሻቀበ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ሁሉም ዜጎች ከንባብ ሳምንት ንቅናቄ በተጨማሪ አስገዳጅ ሕግ ማውጣት እንደሚያስፈልግ፣ ለዚህም ቢሮው ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን፣ መጻሕፍትን ማንበብ የሚያስገድድ ሕግ እንደሚወጣ ጠቁመዋል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...