Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ኪንና ባህልየገንዘቡ ‹‹ማዕድ›› ባለውለታዎች

የገንዘቡ ‹‹ማዕድ›› ባለውለታዎች

ቀን:

የኢትዮጵያ የገንዘብ ታሪክ መንደርደርያው ከዘመነ አክሱም እንደሚቀዳ፣ የወርቅ ሳንቲምን በዋናነት ይዞ በየዓረፍተ ዘመኑ በተለያዩ መገበያያዎች ይጠቀም እንደነበር በታሪክ ተሰንዷል፡፡ የአራተኛው ምዕት ዓመት የእነ ኢዛና የወርቅ ሳንቲሞችያው ሆነው እስከዚህ ዘመን መቀመጣቸውም አንዱ ማሳያ ነው፡፡ ሰሞኑን 80 ዓመቱን ላከበረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ሆነ ለሌሎች ባንኮች ይህ የዘመነ አክሱም የገንዘብ ታሪክ መነሻቸው እንደሚሆን አይሳትም፡፡

የገንዘቡ ታሪክ አንድ አንጓ እንዳለ ሆኖ ገንዘብን የመለዋወጫ፣ የማከማቻ ሥርዓትን ያቀፈው ‹‹ባንክ›› የተሰኘውን ዓቢይ ቃል  ከውጭ ተውሰን ከመጠቀማችን በፊት ይህንን ቃል የሚተካ ነባር አገራዊ ቃል ግን አልነበረንም ወይ? ጥያቄ ሆኖ ይነሳል፡፡ መልሱም አገራዊ ቃል ነበረን፣ ሳናገናዝበው ቀርተን ነው ይላሉ ሊቃውንቱ፡፡ ቃሉንም በአራተኛው ምዕት ዓመት ከግሪክ ወደ ግእዝ ቋንቋ ከተተረጎመው አዲስ ኪዳን ውስጥ እናገኛለን፡፡ በርሱም የባንክን ጽንሰ ሐሳብ እንዲወክል የተቀመጠው ቃል ‹‹ማዕድ›› ይገኛል፡፡

በሉቃስ ወንጌል 1923 ‹‹ወለምንት ኢያግባእከ ወርቅየ ውስተ ማእድየ›› – ገንዘቤን ለገንዘብ ለዋጮች አደራ ያልሰጠኸው ለምንድን ነው?- በአማርኛ ትርጉሙ ገንዘብ ለዋጮች ብሎ የተቀመጠው ማዕድ ነው፡፡ (Then Why didn’t you deposit my money in the bank?) በማቴዎስ 2527 እንደተጻፈውም፣ ገንዘቤን ለገንዘብ ለዋጮች መስጠት ነበረብህ። ‹‹እምደለወከ ታግብእ ወርቅየ ውስተ ማእድየ›› (You ought therefore to have deposited my money with the bankers.)

- Advertisement -

የገንዘቡ ‹‹ማዕድ›› ባለውለታዎች

የገንዘቡ ማዕድ ባለውለታዎች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 80 ዓመቱን ባከበረበትና ባለ 53 ወለሉን ሕንፃ ባስመረቀበት አጋጣሚ በዘርፉ የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱ  አካላት በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ተሸልመዋል።  እነዚህም ባንኩን በስኬት በታጀበ ብቃት የመሩ አራት ታዋቂ ግለሰቦች አቶ ዓለሙ አበራ፣ አቶ ጥላሁን ዓባይ፣ ነፍስ ኄር ተፈራ ደግፌ (/) እና አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ ሲሆኑ፣ ሌላው ተሸላሚ ደግሞ የብሔራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍተኛ የኢኮኖሚ አማካሪ አቶ ግርማ ብሩ የሚመራው ኮሚቴው የተሸለመው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ከማዘመን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አጋጥሞት ከነበረው ፈተና እንዲወጣና አዲስ ፈር እንዲይዝ በማድረጉ ነው። የሌሎቹ ተሸላሚዎች  አራቱ የባንኩ ልዑላን አኩሪ የተባለላቸው ተግባራቸው በሽልማቱ ሥነ ሥርዓት ላይ ቀርቧል። ከዜና መዋዕላቸው መካከል በከፊል እዚህ ላይ በቅደም ተከተላቸው አቅርበነዋል፡፡

አቶ ዓለሙ አበራ በመስከረም 1959 .. የባንኩ ቋሚ ሠራተኛ ሆነው በኦርጋናይዜሽን እና ሜተድስ ክፍል ውስጥ ጀማሪ የባንክ ባለሙያ ሆነው በመቀጠር እስከ ፕሬዚዳንትነት ደርሰዋል፡፡ በከፍተኛ አመራርነት የባንኩን ተቀማጭ ገንዘብ ለማሳደግና የቅርንጫፎች ሥርጭት ለማስፋፋት ያደረጓቸው ጥረቶች የሚጠቀሱ ናቸው። በኃላፊነት ዘመናቸው ባንኩ ገጥሞት የነበረውን የሠለጠነ የሰው ኃይል እጥረት ለመቋቋም የተለያዩ አማራጮችን ሥራ ላይ በማዋል አገልግሎት እንዳይስተጓጎል ማድረጋቸው፣ ከእዚህም ባሻገር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የውጭ አገር የባንክና የንግድ አገልግሎቱ በተሻለ ደረጃ ውጤታማ እንዲሆን የተደረገው ጥረት ከፍተኛ ሲሆኑ ለእዚህም የተለያዩ ተቋማት ለባንኩ ዕውቅና መስጠት አስችሏቸዋል። እርሳቸው  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት በነበሩባቸው ጊዜያት ካከናወኗቸው በርካታ ሥራዎች መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ ከደርግ መንግሥት በፊት የግል ባንኮች የነበሩት በደርግ ተወርሰው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር እንዲዋሀዱ ሲደረግ የተለያዩ የሥራ ዲሲፒሊንና አሠራር ይዘው የመጡትን ሠራተኞችና የማኔጅመንት አባላት አንድ በማድረግ የባንክ ሥራ እንዲቀጥል በማስቻል በኩል ከፍተኛ የመሪነት ሚና ተጫውተዋል፡፡

የደርግ መንግሥት የሶሻሊስት ርዕዮተ ዓለም እከተላለሁ ሲል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሌሎች ዓለም አቀፍ ባንኮች ጫና ደርሶበት፣ በጥሩ ሁኔታ ላይ የነበረው የባንኮች ግንኙነት (Correspondent Banking Relation) እንዳይበላሽ ለማድረግ ልዩ ጥበብ በመጠቀም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠንካራ ይዞታ እንዲኖረው ከፍተኛ ሥራ ሠርተዋል፡፡

በርካታ የባንኩ ሠራተኞችና የማኔጅመንት አባላት በዓለም አንቱ በተባሉ የንግድ ባንኮች ኢንስትቲዩሽኖች ውስጥ የአጭርና የመካከለኛ ጊዜ ሥልጠና እንዲያገኙ እንዲሁም በሥራ ላይ ሥልጠና ጠቃሚ እንዲሆኑ አድርገዋል። እንደዚሁም ኤክስፖርትና ኢምፖርት ካለምንም እንከንና ጥርጣሬ በተቀላጠፈ መንገድ በውጭ ትልልቅ ባንኮች በኩል እንዲስተናገዱ አድርገዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሥራዎች በደርግ መንግሥት ወቅት እንደ ሌሎች የሶሻሊስት አገሮች ባንኮች ከዓለም አቀፍ ባንኮች እንዳይነጠል አድርገውታል፡፡ ከመነጠል ይልቅ የተጠናከረ ግንኙነት እንዲኖረው በማድረጋቸው ከደርግ ውድቀት በኋላ ምንም ችግር ሳይገጥመው እንዲቀጥል አስችለውታል፡፡

አቶ ጥላሁን ዓባይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የማኔጅመንት ሠልጣኝ ደረጃ 1957 .ም. የተቀጠሩ ሲሆን፣ በነበራቸው የሥራ ትጋትና ታታሪነት ከባለሙያነት እስከ ፕሬዚዳንትነት ደረጃ ደርሰዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ከመሆናቸው በፊት ባንኩ ብድሮችን በአዲስ አበባና በሌሎች ጥቂት ትልልቅ ከተሞች ለተወሰኑት ትልልቅ ነጋዴዎችና ሥራ ፈጣሪዎች ይሰጥ ነበር። እርሳቸው ግን ይህንኑ አካሄድ በመቀየር ብድሩ በሁሉም ቅርንጫፎች በኩል እንዲሰጥ ከማድረጋቸውም ባሻገር የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ፣ የመካከለኛና ከፍተኛ ኢንተርፕራይዞች፣ በአገር ውስጥና በውጭ ንግድ የተሠማሩ ነጋዴዎች የመለስተኛ፣ መካከለኛና ከፍተኛ ኮንትራክተሮች፣ ለግለሰብ የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ብድሮች እንዲሰጡ በማድረግ የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋፋት ጥረት አድርገዋል።

በወቅቱ ከነበሩት ምክትል ፕሬዚዳንቶች ጋር በመሆን፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመተካካት ፕሮግራም በመቅረፅ፣ በሺሕ የሚቆጠሩ ወጣት ምሩቃንን በመመልመል፣ አጫጭርና መካከለኛ የሥልጠና ፕሮግራሞችንና የሥራ ላይ ሥልጠና በመንደፍ ተግብረዋል።  የአሁኑና የቀድሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንቶችና አብዛኛዎቹ ምክትል ፕሬዚዳንቶች እንዲሁም የግል ባንኮች ፕሬዚዳንቶችና ምክትሎቻቸው የእኚህ ታላቅ ሰው የምልመላና ሥልጠና ፕሮግራም ውጤቶች ናቸው።

ነፍስ ኄር ተፈራ ደግፌ (/) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በረዥም ታሪኩ ውስጥ ካናዳዊና አሜሪካውያን ኃላፊዎች በበላይነት መርተውታል። ከተለያዩ አገሮች የመጡ ዜጎች (ህንዳውያን፣ አርመኖች፣ ግብፃውያንና አውሮፓውያን) ባንኩ በተቋቋመባቸው ዘመናት በባንኩ የኃላፊነት ቦታዎችና የተለያዩ የሥራ መደቦች ላይ በተዋረድ በኃላፊነት ሠርተዋል።

የባንኩን የኃላፊነት ቦታዎች ከውጭ አገር ዜጎች እጅ በማውጣት በኢትዮጵያውያን የመተካቱ ሒደት ደረጃ በደረጃ ሲከናወን ቀዳሚው ለኃላፊነት በመብቃት ተጠቃሹ ..አ. 1961 ወደ የኢትዮጵያ መንግሥት ባንክ ሥራ አስኪያጅነት የሥራ መደብ ዕድገት ያገኙት ተፈራ ደግፌ (/) ናቸው፡፡  እሳቸው ..አ. 1963 በተጠናቀቀው የባንክ ማሻሻያ ላይ በንቃት ከመሳተፍ ባለፈ፣ ይህንን ጥናት ተከትሎም በዚያው ዓመት የኢትዮጵያ መንግሥት ባንክ ወደ ብሔራዊ ባንክና ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከተከፈለ በኋላ የመጀመሪያው ተቋም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የማዕከላዊ የባንኪንግ ደንቦችንና አሠራሮችን የመቅረፅ ኃላፈነት ወሰደ። ሁለተኛው ተቋም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባንክ የንግድ ሥራ ጉዳዮች ላይ እንዲያተኩር ሲደረግ የመምራት ኃላፊነቱ የተሰጠው ለተፈራ ደግፌ (/) ነው፡፡ እ... 1974  የባንኩ ቅርንጫፍ ወደ 100 ያደገው፣ ባንኩም በአገሪቱ ውስጥ እንደ ዋና የፋይናንስ ተቋም የዓለም አቀፍ ዕውቅናን የተቸረው በእርሳቸው አመራርነት ነበር፡፡

የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ምሩቃን ባንኩን በተለያዩ የአመራር ቦታዎች ተመድበው የባንኩን አሠራር ለማዘመን የሚያስችል አቅም እንዲኖራቸው ማድረጋቸው፣
የባንኩን የሪፖርት ሥርዓት ማቋቋማቸው፣ የተለያዩ የባንኪንግ አሠራርና የሥራ ማኑዋሎች ማዘጋጀታቸው ተጠቅሶላቸዋል፡፡

እንዲሁም የባንኩን ካፒታል ማሻሻያ ከብር 20 ሚሊዮን ወደ 900 ሚሊዮን ማሳደጋቸው፣ የቅርንጫፎቹን ቁጥር 21 ወደ 100 ማሳደጋቸው፣ ለባንክ ባለሙያዎች ማሠልጠኛ ማዕከል እንዲቋቋም የበኩላቸውን ማበርከታቸው፣ የተለያዩ የባንኩ ሠራተኞች በባንኩ ማሠልጠኛ ማዕከል ሥልጠና እንዲያገኙ ማስቻላቸውም ተወስቷል፡፡ 1966 .. አብዮት በፈነዳበት ወቅትም የብሔራዊ ባንክ ገዥ ነበሩ።

አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ ከሦስት ዓመት በፊት የጠቅላይ ሚኒስትር ከፍተኛ የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ ሆነው ከመመደባቸው አስቀድሞ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ውስጥ ከረዳት የኢኮኖሚ ሪሰርች ኦፊሰርነት አንስቶ እስከ የፋይናንስ ተቋማት ሱፐርቪዥን ዳይሬክተርነት ድረስ 30 ዓመት በተለያዩ ቦታዎች አገልግለዋል። ዛሬ የፋይናንስ ተቋማት የሚተዳደሩባቸውን አብዛኛዎችን ሕግጋትና አሠራሮች ከመቅረፅ እስከ ማስፈጸም የሚያደርሰውን ተግባር ከሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን አከናውነዋል።

ለረዥም ዓመታት በጦርነትና በድርቅ ሳቢያ የደቀቀውንና በዝቅተኛ የዕድገት ደረጃ ላይ የቆየውን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እንዲያንሠራራና ፈጣን ዕድገት እንዲያስመዘግብ ለማድረግ በተካሄዱት የኢኮኖሚ ዕድገትና ልማት ዕቅዶች ከቀረፃ እስከ መፈጸም ከሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን የበኩላቸውን አስተዋጽዖ አበርክተዋል፡፡
በጣም ዝቅተኛ የሆነው አጠቃላይ የአገር ውስጥ ቁጠባ እንዲያንሠራራ ለማድረግ የሌሎች አገሮች ተሞክሮን በመቀመር በርካታ የፋይናንስ መመሪያዎች ተግባራዊ እንዲሆኑ አድርገዋል፡፡ በዚህ ረገድ ለብሔራዊ የፋይናንስ አካታችነት ስትራቴጂ ተቀርፆ ተግባራዊ መሆኑና ባንኮች ቅርንጫፎቻቸውን በየዓመቱ 25 በመቶ እንዲያሳድጉ በመደረጉ የባንክ ቅርንጫፎች በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።.

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...