የሳሊኒ ኩባንያ ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ ፔድሮ ሳሊኒ፣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጨት ማብሰሪያ ሥነ ሥርዓት ላይ የተናገሩት፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ የካቲት 13 ቀን 2014 ዓ.ም. በተበሰረው የኃይል ማመንጨት የመጀመርያው ሥርዓት ላይ የግንባታው ተቋራጭ የሆነው የሳሊኒ ኩባንያ መሪው፣ ኢትዮጵያ የተሰጣት ውኃዋንም ለታዳሽ ኃይል ማመንጫነት አውላዋለች ሲሉም አስምረውበታል፡፡ የግድቡን የኃይል ማመንጨት መጀመር ከኢትዮጵያውያን ጋር እኩል የምናከብረው የደስታ ቀን ነው ያሉት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጀመረው ‹‹ዘላቂ የልማት ግብ›› የሚለው ዕቅዱ ጉባ ላይ እውን ሆኗል ሲሉም ተናግረዋል፡፡