Wednesday, November 30, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ ጅማሮ

  የቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ ጅማሮ

  ቀን:

  የቅድመ ልጅነት ዕድገት እንክብካቤ በኢትዮጵያ ብዙም ተግባራዊ ሲደረግ አይታይም፡፡ ከኢትዮጵያ ከአገራዊ ጥቅል ምርትም 0.01 በመቶው ብቻ ለቅድመ ልጅነት ዕድገት እንደሚውል የዓለም የጤና ድርጅት እ.ኤ.አ. በ2019 ያወጣው ጥናት ያመለክታል፡፡

  ይህም በአገር አቀፍ ደረጃ ለቅድመ ልጅነት እንክብካቤ አገልግሎት የሚደረጉ የፖሊሲ፣ የአሠራርና መሰል መንግሥታዊ ክንዋኔዎች ትኩረት እንዳልተሰጠው ማሳያ ነው፡፡

  ይህንንም ተከትሎ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ መሠረታዊ ለውጥ ያመጣል ያለውን ጥናት የካቲት 13 ቀን 2014 ዓ.ም. ይፋ አድርጓል፡፡

  የአዲስ አበባ የሴቶች፣ ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ታምራት ዘለዓለም (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ የቅድመ ልጅነት ዘመን ከፅንሰት እስከ ሰባት ዓመት ያለው የዕድገት ዘመን ነው፡፡

  በዚህ ዕድሜ ክልል ውስጥ የአካላዊ፣ የአዕምሯዊ፣ የቋንቋ፣ የሥነ ልቦና፣ ማኅበራዊና ስሜታዊ ዕድገት የሚከናወንበት እንደሆነም ምክትል ኃላፊው አስረድተዋል፡፡

  በመዲናቱ በቀዳማይ የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ሕፃናት ትኩረት መስጠትና የተሟላ እንክብካቤ እንደሚያስፈልጋቸውም ገልጸዋል፡፡ በኢትዮጵያ ከስምንት ዓመት በታች ያለው የሞት ምጣኔ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተቀመጠው ደረጃ አምስት በመቶ ይበልጣል፡፡ ከአምስት ዓመት በታች ያሉ ሕፃናት ማሟላት ከሚገባቸው ክብደት 21 በመቶዎች ከክብደት በታች መሆናቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

  hjghj

  በአሁናዊው አገራዊ ሁኔታ ምክንያትም በርካታ ሕፃናት ትምህርት፣ የጤና አገልግሎት እንዲሁም፣ የተመጣጠነ ምግብ የማግኘት ችግር ያለባቸው መሆናቸውንም ያመለክታሉ፡፡

  በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለቅድመ መጀመርያ ደረጃ ካልደረሱ ተማሪዎች 43 በመቶው የሕፃናት እንክብካቤ የሚፈልጉ ቢሆኑም፣ አገልግሎት ማግኘት ያልቻሉ መሆናቸውን አክለዋል፡፡

  በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገሮች ቅድመ ልጅነት እንክብካቤ (Early Childhood Development) ላይ ኢንቨስት ማድረግ እንዳለባቸው ጥናቱ መጠቆሙን ታምራት (ዶ/ር) ጠቅሰዋል፡፡

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር ዓባይ እንደተናገሩት፣ የቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ በከተማዋ የታቀደውን ሰፊ ሥራ በስኬት ለመፈጸም የሚያስችል መሠረታዊ መንገድ ነው፡፡

  አስተዳደሩ ለሁሉም የከተማው ሕፃናት የተሟላ የቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ አገልግሎት ለመስጠት አቅዶ እየሠራ መሆኑን፣ በዚህ መሠረት የሕፃናትን ቤተሰቦች ተጠቃሚ የሚያደርግ፣ ወላጆች ልጆቻቸውን ለማኖር ብቻ ሳይሆን ተወዳዳሪ ዜጋ እንዲሆኑ የሚያስችል ፕሮግራም መሆኑን ምክትል ከንቲባው አስረድተዋል፡፡

  ምክትል ከንቲባው እንዳመለከቱት በኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማኅበር የተከናወነው ጥናት በአዲስ አበባ ሕፃናት ለትምህርት ያላቸውን ዝግጁነትና አጠቃላይ የቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ ያለበትን ደረጃ ፈትሿል፡፡

  በጥናቱ ግኝት መሠረት ዕድሜያቸው ከሦስት ዓመት በታች ካሉ ስምንት ሕፃናት አንዱ ወይም 13 በመቶው ያህል በዕድሜያቸው ሊደርሱበት ከሚገባቸው ዕድገት ደረጃ በታች ናቸው፡፡

  ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃ ካለው አምስት በመቶ ከፍ ያለ ሲሆን፣ የኢኮኖሚ ችግር ባለባቸው ቤተሰቦች ውስጥ የሚያድጉ ሕፃናት የተሻለ ቤተሰብ ውስጥ ከሚያድጉ እኩዮቻቸው የትምህርት ቅቡልነታቸው አነስተኛ መሆኑንም ይጠቁማል፡፡

  ከኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማኅበር አቶ ስንታየሁ አባተ ስለጥናቱ እንዳስረዱት፣ የሕፃናት የትምህርት ዝግጁነት፣ ቤተሰቦች ስለቅድመ ልጅነት እንክብካቤ ያላቸው ግንዛቤና ሌሎችም መሠረታዊ ጉዳዮችን ዳሷል፡፡

  ለመረጃ ግብዓት 30 ትምህርት ቤቶችን፣ 30 የቅድመ መጀመሪያ መምህራንን፣ 450 የሚሆኑ ከአራት እስከ ስድስት ዓመት ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሕፃናት፣ እንዲሁም ከዜሮ እስከ ስድስት ዓመት የሚሆኑ የሕፃናት ቤተሰቦች ላይ ዳሰሳ ተደርጓል፡፡

  ታምራት (ዶ/ር) እንዳስረዱት፣ የቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ ዳሰሳ ጥናት የዘጠኝ የስትራቴጂ ኢኒሼቲቭን የያዘ ነው፡፡

  ከዘጠኙ መካከል ስድስቱ በፕሮግራም ደረጃ እየተተገበሩ መሆናቸውን፣ ከስድስቱ ደግሞ ከቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም ውስጥ አራቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴቶች፣ ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ የሚተገበር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

  የመጀመርያው የማኅበረሰቡ የሕፃናት ማቆያ የቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ ማዕከል፣ በማኅበረሰቡ የሚሠራ (ወጪው በማኅበረሰቡ የሆነ) የሕፃናት ማቆያ፣ የቤተሰብ ምክርና የምግብ ድጋፍ የሚሰጥበትና ሕፃናት እየተጫወቱ የሚማሩበት ፕሮግራሞች መሆናቸውን ምክትል ኃላፊው አስረድተዋል፡፡

  ፕሮግራሙ ልጆቻቸውን በሕፃናት ማቆያ ከፍለው ማቆየት የማይችሉ ቤተሰቦች ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑንና ወጪው ሙሉ በሙሉ በመንግሥት እንደሚሸፈንም ጠቁመዋል፡፡

  በየማኅበረሰብ ውስጥ የሕፃናት ማቆያ በመክፈትና ራሱ ማኅበረሰቡ እንዲያስተዳድረው ማድረግ አንደኛው የፕሮግራሙ አካል መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ ልጆች የሚያጠኑበት፣ ቤተሰቦች ስለልጆች አስተዳደግ ሙያዊ ምክር የሚያገኙበት የቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ አገልግሎት እንዳለውም አክለዋል፡፡

  ሌላኛው ፕሮግራም ደግሞ ነፍሰጡሮች፣ የሚያጠቡ እናቶችና እስከ ሦስት ዓመት የሚሆናቸው ሕፃናትን የሚያሳድጉ ቤተሰቦችን ማዕከል ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ለልጆቻቸው የተመጣጠነ ምግብ መመገብ የማይችሉ ቤተሰቦች በቀጥታ የሚደግፉበት መሆኑን፣ እስከ 10‚600 ነፍሰ ጡሮችና የሚያጠቡ እናቶች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተናግረዋል፡፡

  የቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ አገልግሎት ጥናት ከመጋቢት 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ለስምንት ወራት ያህል ጊዜ ሲከናወን ቆይቷል ብለዋል፡፡

  የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጃንጥራር በበኩላቸው፣ 6.8 ሚሊዮንዝብአዲስ አበባ የሚኖር ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 25 በመቶ በላይ የሚሆኑት ሕፃናት መሆናቸውንና የሰው ልጅ ከፅንሰት ጀምሮ በቂ ምግብ ካላገኘ አካላዊና አዕምሮአዊ ዕድገቱ ላይ ተፅዕኖ እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡

  ችግሩ በአገር ላይ የሚያስከትለው ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ጫና ቀላል አለመሆኑን በማስታወስም፣ ‹‹የነገ ተስፋ ሕፃናት ለአዲስ አበባ›› በሚል የተጀመረው ፕሮግራም ውጤታማ ሊሆን የሚችለውም ለወላጆች በማሳወቅና የግልና የመንግሥት ዘርፎችን በማሳተፍ መሆኑን አስረድተዋል።

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶችፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ የሺንጉሥ (/) በበኩላቸው፣ ሕፃናት በተለይም 0-3 ዓመት ያለው ዕድሜያቸውአዕምሮአቸው የማደግ አቅም 80 በመቶ እንደሚደርስ፣ በዚህ ዕድሜ ክልል ውስጥ ሕፃናት ላይ የሚሠራው የሚያስገኘው ውጤት ከፍተኛ እንደሆነ ተናግረዋል።

  የቀዳማይ ልጅነት ዕድገት ፕሮግራም ለአገር ዕድገት መሠረታዊ መሆኑን፣ ሕፃናት በትምህርታቸው የተሻሉ፣ በሥነ ምግባር የታነፁ እንዲሆኑም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የተናገሩት የጥናቱ አጋር የቢግ ዊን ፊላንትሮፒ ዋና አስፈጻሚ ከሰተብርሃን አድማሱ (/) ናቸው፡፡ .ኤ.አ. 2026፣ 330 ሺሕ እናቶች ሁሉን አቀፍ ተደራሽ የሆነ የቀዳማይ ልጅነት ዕድገት አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ጥናቱ እንደሚያግዝ ተጠቁሟል፡፡

   

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በችግር የተተበተበው የሲሚንቶ አቅርቦት

  ሲሚንቶን እንደ ግብዓት ተጠቅሞ ቤት ማደስ፣ መገንባት፣ የመቃብር ሐውልት...

  ‹‹የናይል ዓባይ መንፈስ›› በሜልቦርን

  አውስትራሊያ ስሟ ሲነሳ ቀድሞ የሚመጣው በተለይ በቀደመው ዘመን የባህር...

  ‹‹ልብሴን ለእህቴ››

  ለሰው ልጅ መኖር መሠረታዊ ፍላጎት ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ ልብስ...

  የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የምርመራ ውጤት እስከምን?

  በፍቅር አበበ የትምህርት ጥራትን፣ ውጤታማነትንና ሥነ ምግባርን ማረጋገጥ ዓላማ አድርጎ...