Sunday, June 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅሕልም በየፊናው

ሕልም በየፊናው

ቀን:

ፈላስፋው ጋሊኖስ እንዲህ አለ፡- ሕልሞች እርስ በርሳቸው ከተቀላቀሉቱ ካራቱ ባሕርያት (ከነፋስና ከእሳት ከውኃና ከመሬት) ይወለዳሉ፡፡ ደም በሕዋሱ ውስጥ ሲጸና (ሲዘዋወር)  ሰውዬው በሕልሙ ያማረ ያማረ ቀያይ ነገርንና ደስ የሚያሰኘውን ዓይነት ያያል፡፡ ደም ሲጎርፍ ሲፈስ፣ እሳት ሲሞቅ አገሩ ዳሩ ገደሉ በእሳት ሲቃጠል፣ መብረቆች ሲያንፀባርቁ መብራቶች ሲብለጨለጩ፣ ይህንና ይህን የመሳሰሉትን የደም ኅብር ዓይነቶች ሲያይ ያድራል፡፡ ደም እሳታዊ ጠባይና ኅብር ነውና፡፡

‹‹ሳፍራ›› በሕዋሳቱ ውስጥ በብርታት ሲንቀሳቀስ ሰውዬው ክንፍ አውጥቶ እንደ ወፍ ሲበር፣ ሲሮጥ ሲዞር፣ ሲመለስ መሬት ሲዞርበት ይህንና ይህን የመሳሰለውን የነፋስ ዓይነት በማየት ሲባክን ያድራል፡፡ ሳፍራ ነፋሳዊ ጠባይ ነውና፡፡

‹‹በልቀም›› ሲጸና ወንዞችንና ባሕሮችን በረዶንና ዝናምን ሲያይ ያድራል፤ ከውኃ ውስጥ ገብቶ ሲዋኝ ሲራጭ ውኃን ሲጠጣ፣ ነጫጭ ነገሮችንና እነዚህን የመሳሰሉትን የውኃ ዓይነቶች ሲያይ ያድራል፡፡ በልቀም ማያዊ (ውኃዊ) ጠባይ ነው፡፡

ሰው በነዚህ በአራት ጠባዮች መንቀሳቀስና መነዋወጽ ምክንያት በሕልሙ ሲፈራ ሲደነግጥ፣ ሲንቀጠቀጥ ያድራል፡፡ የፍርሃት ዓይነቶች ሦስት ናቸው፡፡ እነሱም ፍርሃት፣ ድንጋፄ፣ ረዓድ ይባላሉ፡፡ ፍርሃት የልብ፣ ድንጋፄ የናላ፣ ረዓድ የጉልበት ናቸው፡፡

የውኃ ባሕርይ (በልቀም) ሲጸና ውኃ ስትዋኝ፣ እባሕር ውስጥ ስትጠልቅ ጎርፍ ወሰደኝ እስከ ማለት አድርሶ ያቃዣል፡፡  የነፋስ ባሕርይ (ሳፍራ) ሲጸና አሞሮች በሰማይ ሲበሩ፣ አንተ ስትሮጥ ሰዎቹም ሲሮጡ አይሮፕላኖች በሰማይ ሲያንዣብቡ ይታዩሃል፡፡ የመሬት ባሕርይ (ሳውዳ) ሲጸና ጉድጓድ ሲውጥህ መቃብር ሲቆፈር ተራራው ሲናድ አገሩ ሁሉ ሲታረስ ይህን የመሳሰለውን ቅዠት ያሳይሃል፡፡

  • ሊቀ መዘምራን ሞገስ ዕቁበ ጊዮርጊስ ‹‹አንጋፋ ፈላስፋ›› (1953)
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...