የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ(ባልደራስ) ፕሬዚደንት አቶ እስክንድር ነጋ፣ አቶ ስንታየሁ ቸኮልና ሌሎችም አባላት ዛሬ የካቲት 26 ቀን 2014 ዓም በጸጥታ ኃይሎች መያዛቸውን የፓርቲው አባላት ለሪፖርተር ገለጹ።
አመራሮቹና አባላቱ በቁጥጥር ስር የዋሉት የኢፌዴሪ አርማ የሌለውን ሰንደቅ አላማ(ባንዲራ) ይዘው የካራ ማራ የድል በአል ለማክበር በመውጣታቸው ያንን እንዳያደርጉ በጸጥታ ኃይሎች ሲገለጽላቸው ባለመስማማታቸው መሆኑም ታውቋል።
አመራሮቹና አባላቱ ባሁኑ ሰዓት በልደታ ክፍለከተማ ፖሊስ መምሪያ ናቸው።