Friday, October 7, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  - Advertisement -

  ፌርማታ ፅሁፎች

  ኤካ ኮተቤ ሆስፒታልና የሴቶች ቀን

  ትኩስ ፅሁፎች

  ዓለም ሴቶች ቀን (ማርች 8) በዓለም ደረጃ ‹‹የሥርዓተ ፆታ እኩልነት ለዘላቂ ልማት›› በሚል መሪ ቃል ሲከበር፤ በኢትዮጵያ ግን ‹‹እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ በሚል በራሷ መሪ ቃል አክብራለች፡፡ የአዲስ አበባው ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ ያሬድ አግደው (ዶ/ር)፣ የካቲት 29 ቀን 2014 ዓ.ም. የተከበረውን የሴቶች ቀን አስመልክቶ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው የሚመሩትን ተቋም በተመለከተ ያስተላለፉት መልዕክት ከዓለም አቀፉ መሪ ቃል ጋር የሚገናዘብ ነው፡፡ መልዕክታቸው የሚከተለው ነው፡፡

  ‹‹ በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ከተሳካልን አንዱና ትልቁ ፕሮጀክታችን የመምራት አቅምና ፍላጎት ያላቸው ሴቶች ወደ አመራር መምጣት እንዲችሉ ማድረግ ነው። በሴትነታቸው ውስጥ የተደበቀው ብቃታቸው እንዲታይ ዕድል መፍጠር ነው። ሴቶች ከወንዶች እኩል ናቸው ብለን አናሳንሳቸው። ሴቶች ከወንዶች ልዩ ናቸው።

  የተኝቶ ሕክምና ዳይሬክተርሴት

  የተመላላሽ ሕክምና ዳይሬክተርሴት

  የአዕምሮ ሕክምና ዳይሬክተርሴት

  የፋይናንስ ዳይሬክተርሴት

  የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ዳይሬክተርሴት

  የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተርሴት

  የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክተርሴት

  የግዢ ዳይሬክተርሴት

  የነርስ ዳይሬክተር II – ሴት

  የበሽታ መከላከልና ቁጥጥር ዳይሬክተርሴት

  የህፃናት ሕክምና ክፍል ኃላፊሴት

  የውስጥ ደዌ ሕክምና ክፍል ኃላፊሴት

  የቀዶ ሕክምና ክፍል ኃላፊሴት

  የዓይን ሕክምና ክፍል ኃላፊሴት

  የራዲዮሎጂ ክፍል ኃላፊሴት

  የንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን መሪሴት

  የፅኑ ሕሙማን ክፍል አስተባባሪሴት

  የድንገተኛ ክፍል አስተባባሪሴት

  የውስጥ ደዌ ሕክምና ክፍል አስተባባሪሴት

  የላውንደሪ ክፍል ኃላፊሴት

  መልካም የሴቶች ቀን ለአናብስቱ!››

  በፎቶው ላይ የሆስፒታሉ አመራሮች ከጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) ጋር ይታያሉ፡፡

  - Advertisement -
  - Advertisement -

  ተጨማሪ ለማንበብ

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች