Monday, March 27, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበሊጉ ያልዘመነው የተጫዋቾች የዝውውር መንገድና የአሠልጣኞች ስንብት

በሊጉ ያልዘመነው የተጫዋቾች የዝውውር መንገድና የአሠልጣኞች ስንብት

ቀን:

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከዓምና ጀምሮ በአክሲዮን ተደራጅቶ የራሱን ውድድር የማስተዳደር መብቱን ቢረከብም፣ በክለቦች ያልዘመነው የዝውውር ሥርዓት እንዲሁም ዘርፉ ላይ ቁልፍ ድርሻ ባላቸው አሠልጣኞችና ባለሙያ ሥውር እጆች ቡድኖቹን ለፋይናንስና ለውጤት ቀውስ እየዳረጋቸው መሆኑ ይገለጻል፡፡ የዚህ ችግር ሰለባ ከሆኑ ክለቦች መካከል የድሬዳዋ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ከሰሞኑ ዋና አሠልጣኙን አሰናብቷል፡፡ ቀደም ሲልም ወልቂጤ ከተማና ሌሎችም ክለቦች አሠልጣኞቻቸውን ያሰናበቱ አሉ፡፡

የዘንድሮው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጅማሮውን በሐዋሳ አድርጎ የሊጉን የመጀመርያ ዙር የጨዋታ መርሐ ግብር ባለፈው ሳምንት ድሬዳዋ ላይ ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

ክለቦች ከውጤት ጋር ተያይዞ የሚያሳልፉት ውሳኔ እውነት ለቡድኖቻቸው ውጤት መበላሸት መፍትሔ ይሆናል ወይ? በሚለው ጉዳይ ሪፖርተር ያነጋገራቸው ባለሙያዎችና ማንነታቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ ተጫዋቾች፣ ‹‹የክለብ አመራሮች በተለይ ውጤት ሲጠፋ መፍትሔ ብለው የሚወስዱት ዕርምጃ አሠልጣኝ ማሰናበትና አዲስ አሠልጣኝ መቅጠር ነው፡፡ ይህ ሒደት የሚፈጸምበት ጊዜ ደግሞ የአሠልጣኞችና የተጫዋቾች ዝውውር መስኮት ሲከፈት መሆኑ ብዙዎች ልብ ሊሉት ይገባል፡፡ ምክንያቱን በግልጽ ቋንቋ ማስቀመጥ ካስፈለገ የትኛውም አሠልጣኝም ሆነ ተጨዋች ዝውውር ሲፈጽም፣ ተጨዋች ለአሠልጣኝ፣ አሠልጣኝ ደግሞ ለክለብ አመራር ክፍያ መፈጸም ሲችል ብቻ ነው፤›› በማለት ግልጽነት የጎደለውን የክለቦች የዝውውር ሥርዓትን ይተቻሉ፡፡

ድሬዳዋ ከተማን ጨምሮ በሌሎችም ክለበች በተለይ ከተጫዋቾችና አሠልጣኞች ቅጥር ጋር ተያይዞ ያለው አሠራር በግልጽ ተፈትሾ የዕርምት ዕርምጃ እስካልተበጀለት ድረስ፣ አሠልጣኝ በማሰናበትና በመቅጠር ብቻ ኅብረተሰቡም ሆነ መንግሥት ከእግር ኳሱ የሚፈልጉትን ዕድገት አሊያም የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ማምጣት እንደማይቻል፣ በተለይ የዚህ ችግር ሰለባ የሆኑ ክለቦች እንዲሁም ወጣትና ተተኪ ተጫዋቾች  ይናገራሉ፡፡

ከሰሞኑ ድሬዳዋ ከተማ ከውጤት መጥፋት ጋር ተያይዞ አሠልጣኝ ዘማርያም ወልደ ጊዮርጊስን አሰናብቶ፣ ላለፉት በርካታ ዓመታት የተለያዩ ክለቦች በማሠልጠን የሚታወቀው አሠልጣኝ ሳምሶን አየለን የቡድኑ ዋና አሠልጣኝ አድርጎ መቅጠሩ ይፋ አድርጓል፡፡

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በበኩሉ የተቋሙን የዝውውርና የስንብት ደንብ በመጥቀስ፣ ድሬዳዋ ከተማ የአሠልጣኙን ውል እንዲያከብር ጠይቋል፡፡ ከድሬዳዋ ከተማ ቀደም ሲል ሆድያ ሆሳዕና፣ ጅማ አባ ጅፋር፣ ወልቂጤ ከተማና ሌሎችም ክለቦች በተመሳሳይ ከውጤት ማጣት ጋር በተገናኘ አሠልጣኞቻቸውን ማሰናበታቸው ይታወሳል፡፡

ፕሪሚየር ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ በ31 ነጥብ ሲመራ፣ ተከታዮቹ ወላይታ ድቻና ሐዋሳ ከተማ በ28 እና በ27 ነጥብ ሁለተኛና ሦስተኛ ደረጃ ላይ ናቸው፡፡ ወራጅ ቀጣና ውስጥ የሚገኙት ሰበታ ከተማ በዘጠኝ ነጥብ 16ኛ፣ ጅማ አባ ጅፋር በ11 ነጥብ 15ኛ፣ አዲስ አበባ ከተማ በ14 ነጥብ 14ኛ እና ድሬዳዋ ከተማ በ15 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠው የመጀመርያውን ዙር ያጠናቀቁ ናቸው፡፡

በአሁኑ ወቅት ፕሪሚየር ሊጉ ከሚቀረው የጨዋታ መርሐ ግብርና ክለቦቹ በመጀመርያው ዙር ካስመዘገቡት ውጤት በመነሳት፣ ወራጁ ቀጣና ላይ ያለው ክለብ ከመሪው ያለው የነጥብ ልዩነት በሒሳብ ሥሌት አሸናፊውና ወራጁ ቡድን ማንነት ወስኖ መናገር እንደማይቻል የሚናገሩት የሪፖርተር ምንጮች፣ ‹‹ክለቦች ከውጤት ጋር ተያይዞ የሚያቀርቡትን ምክንያት ወደ ጎን ብለው፣ ይልቅስ ዝውውርና ቅጥርን ጨምሮ የክለቦቻቸውን አሠራር ማዘመን ላይ በማተኮር በውጤት ቀውስ እዚያና እዚህ የሚባዝነውን እግር ኳስ ሊታደጉ ይገባል፤›› ይላሉ፡፡               

 

 

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...